====================
የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ቅዱስ ወንጌል።
ቅዱስ ማቴዎስ እንደ ጻፈው።
በእንተ ፈሪሳውያን ወሥርዓቶሙ።
ምዕራፍ ፲፭።
******
፲፯፡ ኢተአምሩኑ ከመ ኵሉ ዘይበውዕ ውስተ አፍ ውስተ ከርሥ ይትገመር፡፡
******
፲፯፡ በአፍ የሚገባው ሁሉ በሆድ እንዲወሰን አታውቁምን።
መጽመ ይትከአው።
ጥቂት ቈይቶም እንዲፈስ ወጽቡ ይትከዓው ይላል በማርቆስ። አሠር አሠሩ እንዲፈስ፡፡
(ሐተታ) የበላነውን የጠጣነውን መሬት ይሸከማል ውሀ ያረጥባል። እሳት እንደ ገና ያበስላል ነፋስ አረቂ አረቂውን ወደ ላይ ይዞ ይወጣል የሰው አስራው ፮፻፷፮ ነው ፮ቱ ለስሳው ስሳው ለስድስት መቶው ያቀብላሉ በዚህ ጊዜ አሠር አሠሩ ቊልቊል ይወርዳልና
******
፲፰፡ ወዘሰ ይወፅእ እምውስተ አፍ እምልብ ይወፅእ።
******
፲፰፡ በአፍ የሚያወጣው ግን ከልብ ይወጣል።
ወውእቱ ያረኵሶ ለሰብእ።
ይህ ሰውን ይጐዳዋል ሰውን የሚጐዳው ይህ ነው።
******
፲፱፡ እስመ እምውስተ ልብ ይወፅእ ሕሊና እኵይ።
******
፲፱፡ ከልብ ክፉ አሳብ ይነቃልና።.
ዘውእቱ ቀቲል።
እኩይ ያለውን ይተረትራል ያውም ነፍስ መግደል ነው
ወዝሙት ።
ዝሙት ነው ።
ስርቅ።
መስረቅ
ስምዕ በሐሰት።
በሐሰት መመስከር ነው።
******
፳፡ ወፅርፈት
******
፳፡ ስድብ ነው።
እሉኬ ዘያረኵስዎ ለሰብእ።
ሰውን የሚጎዱት እሊህ ናቸው፡፡ እሊህ ሰውን ይጐዱታል።
ወዘእንበለ ተሐፅቦ እድሰ በሊዕ ኢያረኵሶ ለሰብእ።
እጅ ሳይታጠቡ መብላትስ ሰውን አይጐዳውም በዪውም መሬት ተበዪውም መሬት ምን ይጐዳል።
******
፳፩፡ ወወፂኦ እግዚእ ኢየሱስ እምህየ ተግኅሠ ውስተ ደወለ ጢሮስ ወሲዶና።
******
፳፩፡ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከዚያ ወጥቶ ወደ ጢሮስና ወደ ሲዶና አውራጃ ገባ።
******
በእንተ ከነናዊት።
፳፪፡ ወናሁ መጽአት ብእሲት ከነናዊት እምውእቱ አድዋል፡፡ ማር ፯፥፳፭።
******
፳፪፡ ከነናዊት ከነዓናዊት ይላል ከነናዊት ቢል የከናኔዎን ወገን ከነዓናዊት ቢል የከነዓን ወገን የምትሆን ሴት ከዚያ አውራጃ መጣች፡፡
እንዘ ትጸርኅ ወትብል መሀረኒ ወልደ ዳዊት
ወልደ ዳዊት አቤቱ እዘንልኝ እያለች እየጮኸች።
እስመ ለወለትየ እኵይ ጋኔን አኃዛ።
ልጄን ቢስ ጋኔን አድሮባታልና።
ወየዓብዳ
አእምሮዋን ያሳጣታልና፤
******
፳፫፡ ወኢያውሥአ እግዚእ ኢየሱስ ቃለ
******
፳፫፡ ጌታም ነገር አልመለሰላትም
ወቀሪቦሙ አርዳኢሁ አስተብቊዕዎ እንዘ ይብሉ ፈንዋ ለዛቲ ብእሲት።
ደቀ መዛሙርቱ ቀርበው ይህቺን ሴት አሰናብታት ብለው ማለዱት።
እስመ ትጸርኅ በድኅሬነ።
በኋላ በኋላችን ትጮሃለችና
(ሐተታ) ትምህርት ታስፈታለች ብለው። አንድም ወይ ተናግረው አያስደርጉ ወይ አያሰናብቱ ትላለች ብለው ብታሳዝናቸው፡፡
******
፳፬፡ ወአውሥአ ወይቤሎሙ ኢተፈኖኩ ዘእንበለ ኀበ አባግዕ ዘተኃጕላ ለቤተ እስራኤል። ማቴ ፲፥፮።
******
፳፬፡ ትምህርት መምህር አጥተው የተጐዱ እስራኤልን ላስተምር ሰው ሁኘአለሁ እንጂ። ያለዚያ ሰው አልሆንኩም ብሎ መለሰላቸው።
******
፳፭፡ ወቀሪባ ስገደት ሎቱ። ማር ፯፥፳፮፡፡
******
፳፭፡ ቀርባ ሰገደችለት
እንዘ ትብል እግዚእየ ርድዓኒ
አቤቱ ጌታዬ እዘንልኝ ብላ
******
፳፮፡ ወአውሥአ ወይቤላ ኢኮነ ሠናየ ነሢአ ኅብስተ ውሉድ ወውሂብ ለከለባት።
******
፳፮፡ የልጆችን ዳቦ ለውሻ መስጠት አይገባም ማለት ለእስራኤል የማደርገውን ተአምራት ለአሕዛብ አላደርገውም አላት።
******
፳፯፡ ወትቤሎ እወ እግዚኦ።
******
፳፯፡ አቤቱ አዎን ውሻ ነኝ አለችው፡፡
ከለባትኒ ጓ ይበልዑ እምፍርፋራት ዘይወድቅ እማዕደ አጋዕዝቲሆሙ፡፡
ውሾችም እንጂ ውሾችም እኮን ከጌታቸው ማዕድ የወደቀ ፍርፋሪን ይመገባሉ። እንደዚህስ ሁሉ ለእስራኤል ደጋጉን ተአምራት ብታደርግላቸው ለእኔ ጥቃቅኑን ተአምራት አታደርግልኝም አለችው።
******
፳፰፡ ወእምዝ አውሥአ።
******
፳፰፡ ከዚህ በኋላ መለሰ።
ወይቤላ ብእሲቶ ዓቢይ ሃይማኖትኪ።
አንቺ ሆይ ሃይማኖትሽ ታላቅ ነው ማለት ፍጹም ነው።
ይኩንኪ በከመ ተአመንኪ።
እንዳመንሽ ይደረግልሽ አላት
(ሐተታ) ሶስት ነገር አግኝቶላታል ሃይማኖት ትሕትና ጥበብ። ሃይማኖት ያድንልኛል ብሎ መምጣት። ትሕትና በውሻ ቢመስላት አዎን ውሻ ነኝ ማለት፡፡ ጥበብ መስሎ ቢነግራት መስሎ መናገር ነው።
ወሐይወት ወለታ እምይእቲ ጊዜ።
በዚያን ጊዜ ልጅዋ ዳነች።
******
ዘከመ ተፈወሱ ካልአን ሕሙማን።
፳፱፡ ወኃሊፎ እግዚአ ኢየሱስ እምህየ በጽሐ ኀበ ሐይቀ ባሕር ዘገሊላ፤
፳፱፡ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከዚያ አልፎ ከገሊላ ባሕር ወደብ ደረሰ።
******
ይቆየን፡፡
**************
መልካሙ በየነ
ደብረ ማርቆስ፤ ኢትዮጵያ
10/09/2011 ዓ.ም
Friday, May 17, 2019
ወንጌል ቅዱስ ክፍል 94
Subscribe to:
Post Comments (Atom)
No comments:
Post a Comment