====================
የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ቅዱስ ወንጌል።
ቅዱስ ማቴዎስ እንደ ጻፈው።
በእንተ ሰዊት።
ምዕራፍ ፲፪።
******
፩፡ ወበውእቱ መዋዕል ወፈረ እግዚእ ኢየሱስ በሰንበት እንተ ማዕከለ ገራውህ። ማር ፪፥፳፫፡፡ ሉቃ ፮፥፩።
******
፩፡ በዚያ ወራት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ቅዳሜ በእርሻ መካከል ሄደ።
አርዳኢሁሰ ርኅቡ ወአኃዙ ይምሀዉ ሰዊተ ወይብልዑ፡፡
ደቀ መዛሙርቱ ግን ተርበው ነበርና እሸት እያሹ ይበሉ ጀመር።
******
፪፡ ወርእዮሙ ፈሪሳውያን ይቤልዎ ርኢ ዘይገብሩ አርዳኢክ ዘኢይከውን ገቢረ በሰንበት።
******
፪፡ ፈሪሳውያን ሰምተው ደቀ መዛሙርትህ በሰንበት ሊሠሩት የማይገባ ሥራ ሲሠሩ አስተ ውል አሉት።
******
፫፡ ወይቤሎሙ ኢያንበብክሙኑ ዘገብረ ዳዊት አመ ርኅበ።
******
፫፡ ዳዊት በተራበ ጊዜ ያደረገውን አልተመለከታችሁም አላቸው።
ውእቱኒ። ወእለ ምስሌሁ።
እሱም ከሱ ጋራ ያሉ ብላቴኖቹ ያደረጉትን።
******
፬፡ ዘከመ ቦአ ቤቶ ለእግዚአብሔር ወበልዓ ሐባውዘ ቊርባን ዘኢይከውኖ ለበሊዕ።
******
፬፡ ከቤተ እግዚአብሔር ገብቶ ሊበላው የማይገባውን መሥዋቱን እንደበላ።
ወኢ ለእለ ምስሌሁ።
ከሱም ጋራ ያሉ ሊበሉት የማይገባውን።
ዘእንበለ ለካህናት ለባሕቲቶሙ
ለካህናት ብቻ ይገባቸዋል እንጂ።
******
፭፡ ወካዕበ ኢያንበብክሙኑ ዘሀሎ ውስተ ኦሪት ከመ ካህናት እለ ውስተ ቤተ መቅደስ ያረኵስዋ ለሰንበት። ዘሌ ፳፬፥፰፡፡ ዘኍ ፳፰፥፱።
******
፭፡ ይስዕርዋ ሲል ነው። በቤተ መቅደስ ያሉ ካህናት ቅዳሜን እንዲሽሯት በኦሪት የተጻፈውን አልተመለከታችሁምን ይሥዕርዋ ማለቱ ላሙን ሲያርዱ ሥጋውን ሲያወራርዱ መሬቱ ይዳሳል ሥሩ ይበጠሳልና።
ወኢይከውኖሙ ጌጋየ።
ዕዳ እንዳይሆንባቸው።
******
፮፡ እብለክሙ ከመ ዘየዓቢ እምቤተ መቅደስ ሀሎ ዝየ።
******
፮፡ እኒያማ የታዘዘውን ቢያደርጉ ምን ዕዳ ይሆናል ትሉኝ እንደሆነ ከቤተ መቅደስ የሚበልጥ በዚህ አለ ማለት ምሳሌየን ሲያገለግሉ ሰንበትን ቢሽሩ ዕዳ ካልሆነባቸው አማናዊ ቤተ መቅደስ እኔን ሲያገለግሉ ቢበሉ ዕዳ አይሆንባቸውም ብዬ እነግራችኋለሁ።
******
፯፡ ሶበሰ ተአምሩ ምንት ውእቱ ዘይቤ ምጽዋተ አበድር እመሥዋዕት እምኢኮነንክምዎሙ ለእለ ኢይኤብሱ። ሆሌ ፮፥፯።
******
፯፡ ምጽዋተ አበድር እመሥዋዕት ያለውን ምንም እንደሆነ ብታውቁስ ማለት እኒህን መንቀፍ መሥዋዕት እኒህን አለመንቀፍ ምጽዋት እንደሆነ ብታውቁስ ባልበደሉ በሐዋርያት ባልፈረዳችሁም ነበር።
አንድም ይኤብሱ ይላል ሳይበድሉ በድለዋል በምትሏቸው በሐዋርያት ባልፈረዳችሁባቸውም ነበር።
እምኢያቊሰልክምዎሙ።
በበትረ ረሀብ ይመቱ ባላላችኋቸውም ነበር እምኢያቊጸልክምዎሙ በረኃብ እንደ ቅጠል ይርገፉ ባላላችኋቸውም ነበር።
******
፰፡ እስመ እግዚኣ ውእቱ ለሰንበት ወልደ እጓለ እመሕያው ክርስቶስ።
******
፰፡ የሰንበት ጌታዋ ወልደ እጓኅለእመሕያው ክርስቶስ ነውና
እብለክሙ ዘየዓቢ እምቤተ መቅደሱ ሀሎ ዝየ።
አንድም ሰንበትሰ በእንተ ሰብእ ተፈጥረት ወአኮ ሰብእ በእንተ ሰንበት ይላል በማርቆስ። ሰንበት ስለሰው ተፈጥራለች እንጂ፡፡ ሰው ስለ ሰንበት አልተፈጠረም ማለት ሰንበት ሰው ከፃማ ረኃብ ሊያርፍባት ተፈጥራለችና እምኢኰነንክምዎሙ በል።
******
፱፡ ወፈለሰ እግዚእ ኢየሱስ እምህየ ወቦአ ውስተ ምኵራቦሙ። ማር ፫፥፩፡፡ ሉቃ ፮፥፯።
******
፱፡ ጌታችን ከዚያ አልፎ ከምኵራባቸው ገባ።
******
በእንተ ዘየብሰት እዴሁ።
፲፡ ወናሁ ሀሎ ብእሲ ዘየብሰት እዴሁ።
******
፲፡ እጁ ልምሾ የሆነች ሰው አለ
ወተስእልዎ እንዘ ይብሉ ይከውንኑ በሰንበት ፈውሶ።
ቅዳሜ ድውይ መፈወስ ይገባልን አይገባም ብለው ጠየቁት፤
ከመ ያስተዋድይዎ ።
ሊያጣሉት ሊያካስሱት።
(ሐተታ) አይገባም ቢላቸው የእግዚአሔር ወገን ነኝ ይላል የሰው ጥፋት አያሳዝነውም ለማለት ይገባል ቢላቸው የሙሴን ሕግ አፈረሰ ብለን እንጣላዋለን ብለው።
******
፲፩፡ ወይቤሎሙ መኑ እምውስቴትክሙ ዘቦቱ አሐዱ በግዕ ወእመ ወድቆ ውስተ ግብ በሰንበት ዘኢይእኅዞ ወኢያነሥኦ ዘዳ ፳፪፥፬።
******
፲፩፡ ከናንተ ወገን አንድ በግ ያለው ሰው በሰንበት ከፈረፈር የገባበት መሬቱን ድሶ ስሩን በጥሶ የማያወጣው ማነው።
ኢይእኅዞኑ
አያወጣውምን
አኮኑ ይእኅዞ ያወጣው የለምን፡፡
******
፲፪፡ እፎ እንከ ፈድፋደ ይኄይስ ሰብእ እምነ በግዕ።
******
፲፪፡ ያማ እንዴታ ትሉኝ እንደሆነ ከተፈጥሮተ በግዕ ተፈጥሮተ ሰብእ እንደምን ይበልጥ።
******
፲፫፡ ይከውንኬ በሰንበት ገቢረ ሠናይ።
******
፲፫፡ እንኪያስ ቅዳሜ ድውይ መፈወስ ይገባል።
******
፲፬፡ ወእምዝ ይቤሎ ለውእቱ ብእሲ ስፋሕ እዴከ።
******
፲፬፡ በኋላ ያን ሰው እጅህን ዘርጋ አለው።
ወሰፍሐ እዴሁ።.
እጁን ዘረጋ።
ወሐይወት ሶቤሃ።
ፈጥና ዳነች።
ወኮነት ከመ ካልዕታ።
ቀኚቱ ናት ቢሉ እንደ ግራይቱ ግራዪቱ ናት ቢሉ እንደ ቀኚቱ ሆነች። እንተ የማን ይላል በሉቃስ እንደ ግራዪቱ ሆነች።
ወወፂኦሙ ፈሪሳውያን ተማከሩ በእንቲአሁ ከመ ይቅትልዎ
ፈሪሳውያን ወጥተው ሊገድሉት እንግደለው ብለው ተማከሩ።
******
በአንተ ርኅራኄሁ ለእግዚእ ኢየሱስ።
፲፭፡ ወአእሚሮ እግዚእ ኢየሱስ ተግኅሠ እምህየ።
******
፲፭፡ ጌታም ሊገድሉት እንደመከሩ አውቆ ከዚያ ወጥቶ ሄደ። እንዳይሞት ጊዜው አልደረሰምና ከዚያው ሳለ ድኖም ቢሆን ምትሐት ነው ባሉት ነበርና።
ወተለውዎ ብዙኃን ሰብእ።
ብዙ ሰዎች ተከተሉት።
ወአሕየዎሙ ለኵሎሙ።
ሁሉንም አዳናቸው።
******
፲፮፡ ወገሠፆሙ ከመ ኢያግኅድዎ
******
፲፮፡ አትንገሩ አላቸው
(ሐተታ) ውዳሴ ከንቱ አይሻምና የሚያምኑበት ጊዜ አልደረሰምና። እስከ ትንሣኤ።
******
፲፯፡ ከመ ይትፈጸም ዘተብህለ በኢሳይያስ ነቢይ እንዘ ይብል።
******
፲፯፡ በነቢዩ በኢሳይያስ እንዲሀ ተብሎ የተነገረው ይደርስ ይፈጸም ዘንድ።
******
፲፰፡ ወናሁ ወልድየ ዘኃረይኩ። ኢሳ ፵፪፥፩።
******
፲፰፡ ለተዋሕዶ የመረጥኵት ልጄ።
ወፍቁርየ ዘሠምረቶ ነፍስየ።
ሕይወቴ መንፈስ ቅዱስ ለህልውና የመረጠችው ወዳጄ።
ወአነብር መንፈስየ ላዕሌሁ።
ሕይወቴ መንፈስ ቅዱስን ሕይወት የማደርግለት።
******
፲፱፡ ውእቱ ይሜህር ፍትሕየ ለአሕዛብ ወኵነኔየ ለሕዝብ።
******
፲፱፡ እሱ ሃይማኖተ ወንጌልን ለአሕዛብ ሃይማኖተ ኦሪትን ለእስራኤል ሲያስተምር።
ኢይደምፅ ወኢይጸርኅ።
አይሰማም።
ወአልቦ ዘይሰምዕ ቃሎ በምኵራባት።
በምኵራባት ሲያስተምር የሚሰማው የለም ተብሎ በኢሳይያስ የተነገረው ትንቢት ይደርስ ይፈጸም ዘንድ።
(ሐተታ) በዮሐንስ ወዓልዓለ ቃሎ በምኵራብ ይላል በዚህ እንዲህ አለ አይጣላም ቢሉ አይጣላም ነገር እንደ ዮሐንስ ነው አሰምቶ ነው የሚያስተምር። ከዚህ እንዲህ ማለቱ ውዳሴ ከንቱ አይሰማበትም ሲል ነው፡፡
******
፳፡ ብርዕ ቅጥቁጥ ኢይሰበር።
******
፳፡ ከእግሩ ጭምትነት የተነሣ አስኳሉ የወጣለት የዕንቊላል ቅርፍት አይደቅበትም።
ወሡዕኒ ዘይጠይስ ኢይጠፍዕ
ከቃሉ ልዝብነት የተነሣ የሚጤያጢያስ የጧፍ ኩስታሪ አይጠፋበትም።
እስከ ይገብዕ ፍትሐ መዊዖቱ
አሸናፊ ፍርዱ በአይሁድ በአጋንንት እስኪመለስ ድረስ።
******
፳፩፡ ወበስመ ዚአሁ ይትአመኑ አሕዛብ።
፳፩፡ አሕዛብም በስሙ እስኪያምኑ ድረስ ያለው ይደርስ ይፈጸም ዘንድ።
******
ይቆየን፡፡
**************
መልካሙ በየነ
ደብረ ማርቆስ፤ ኢትዮጵያ
26/08/2011 ዓ.ም
Saturday, May 4, 2019
ወንጌል ቅዱስ ክፍል 81
Subscribe to:
Post Comments (Atom)
No comments:
Post a Comment