====================
የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ቅዱስ ወንጌል።
ቅዱስ ማቴዎስ እንደ ጻፈው።
በእንተ ሰዊት።
ምዕራፍ ፲፫።
******
******
በእንተ ፍካሬ ዘምሳሌ ክርዳድ።
፴፮፡ ወእምዝ ኀደጎሙ ለአሕዛብ ወቦአ ውስተ ቤት።
******
፴፮፡ ከዚህ በኋላ ሕዝቡን በአፍአ ትቶ ከቤት ገባ
ወቀርቡ ኀቤሁ አርዳኢሁ ።
ደቀመዛሙርቱም ወደሱ ቀረቡ
ወይቤልዎ ፈክር ለነ ምሳሌ ዘክርዳድ ወዘገራህት ።
በክርዳድ በገራህት የመሰልከውን ተርጉጕመህ ገልጸህ ንገረን አሉት እንደ ከተማ ደቀመዝሙር አይደሉምና የከተማ ደቀ መዝሙር ቢያየውም ባያየውም ዝም ብሎ ይሄዳል።
******
፴፯፡ ወአውሥአ ወይቤሎሙ ዘይዘርዕሰ ሠናየ ዘርዓ ወልደ እጓለ እመሕያው ውእቱ።
******
፴፯፡ ያ መልካም ዘር የዘራው የሰው ልጅ ነው ብሎ መለሰላቸው
******
፴፰፡ ወገራህትኒ ዓለም ውእቱ
******
፴፰፡ እርሻውም ዓለም ነው።
ወሠናይኒ ዘርዕ ውሉደ መንግሥት እሙንቱ።
መልካም ዘር የመንግሥት ልጆች ናቸው።
ወክርዳድኒ ውሉዱ ለእኩይ።
ክርዳዱም የክፉ ልጆች ናቸው
******
፴፱፡ ወፀራዊኒ ዘዘርዖ ዲያብሎስ ውእቱ። ራዕ ፲፬፥፲፭።
******
፴፱፡ የዘራውም ጠላት ዲያብሎስ ነው።
ወማዕረርኒ ኅልቀተ ዓለም ውእቱ
መከሩም የዓለም ፍጻሜ ነው
ወዓፀድኒ መላእክት እሙንቱ
አጫጆችም መላእክት ናችው።
******
፵፡ ከመኬ የዓርይዎ ለክርዳድ ቅድመ ወያውዕይዎ በእሳት።
******
፵፡ ክርዳዱን አስቀድመው መርጠው በእሳት እንዲያቃጥሉት።
ከማሁ ይከውን በኅልቀተ ዝንቱ ዓለም።
በዚህ ዓለም ፍጻሜ እንዲህ ይሆናል።
******
፵፩፡ ይፌንዎሙ ወልደ እጓለ እመሕያው ለመላእክቲሁ።
******
፵፩፡ የሰው ልጅ መላእክትን ያዛቸዋል፡፡
ወየዓርዩ እመንግሥቱ ኵሎ ዓላውያነ ወእለ ይገብሩ አበሳ
በደል የሚያደርጉትንና ወንጀለኞችን ከመንግሥቱ ላይ ለይተው።
******
፵፪፡ ወይወድይዎሙ ውስተ እቶነ እሳት ኀበ ሀሉ ብካይ ወሐቅየ ስነን።
******
፵፪፡ ልቅሶ ጥርስ ቊርጥማት ወዳለበት ዕቶነ እሳት ይጨምሯቸዋል።
******
፵፫፡ አሜሃ ይበርሁ ጻድቃን ምስብዒተ እደ እምብርሃነ ፀሐይ በመንግሥተ አቡሆሙ፡፡ ጥበ ፫፥፯፡፡ ዳን ፲፪፥፯።
******
፵፫፡ ያን ጊዜ ጻድቃን ሰማያዊ አባታቸው በሚያወርሳቸው በመንግሥተ ሰማይ ከፀሐይ ሰባት እጅ ያበራሉ።
ዘቦ ዕዝን ሰሚዓ ለይስማዕ።
ሰሚ ጆሮ ያለው ይስማ ማለት ዕዝነ ልቡና ያለው ያስተውል።
******
በእንተ መድፍን ወባሕርይ ወገሪፍ።
፵፬፡ ወካዕበ ትመስል መንግሥተ ሰማያት መድፍነ ዘኅቡዕ ውስተ ገራህት።
******
፵፬፡ ለቀረበው ካዕበ ይላል ሁለተኛ መንግሥተ ሰማይ ሕገ ወንጌል ሕገ ወንጌል ተስፋ፣ ተስፋ ኢየሱስ ክርስቶስ፤ ዘኅቡዕ ዝጉበ ይላል በእርሻ ውስጥ የተቀበረች ወርቅን ትመስላለች።
ወረኪቦ ብእሲ ኀብዓ።
ሰው አግኝቶ የሰወራትን።
ወእምፍሥሐሁ ሖረ ወሤጠ ኵሎ ዘቦ ወተሣየጣ ለይእቲ ገራህት፡፡
ከደስታው የተነሣ ሂዶ ያለ ገንዘቡን ሽጦ ያቺን እርሻ የገዛላትን፡፡
(ሐተታ) ምድሩን ከአልገዛሁ ወርቁን አላገኝም ብሎ ባልሆነ ምሳሌ አያስተምርምና የኤዶምያስ ሰዎች የቀበሩት ወርቅ ነው።
አንድም ካዕበ ትመስል መድፍነ ብለህ መልስ ብእሲ ጌታ መድፍን አዳም ገራህት ይህ ዓለም ነው፤ ወረኪቦ ጌታ አዳምን በዚህ ዓለም ንስሐ ገብቶ ባገኘው ጊዜ ባሕርየ አዳምን ባሕርይ አድርጎ አዳምን ማዳኑን መናገር ነው። ኢነሥኦ ለዘነሥኦ እመላአክት ዘአንበለ ዳዕሙ እምዘርአ አብርሃም እንዲል።
አንድም ብእሲ ዮሴፍ መድፍን ጌታ ገራህት እመቤታችን። ዮሴፍ ጌታን እመቤታችንን ባገኛቸው ጊዜ ቤቱን ንብረቱን ትቶ ተከትሎ ግብፅ መውረዱን መናገር ነው።
አንድም ብእሲ ሐዋርያት መድፍን ጌታ ገራህት ይህ ዓለም። ወረኪቦ ሐዋርያት ጌታን በዚህ ዓለም ባገኙት ጊዜ መረባቸውን መርከባቸውን ትተው ጌታን መከተላቸውን መናገር ነው።
አንድም አምስቱን ግብራት በአምስቱ ግብራት ተሰውረው ባገኛቸው ጊዜ ትፍሥሕትን በኃዘን ኃይልን በድካም ብዕልን በንዴት ልዕልናን በትሕትና ግዕዛንን በግብርናት ተሰውረው ባገኛቸው ጊዜ ትፍሥሕቱን ለኃዘን ኃይሉን ለድካም ብዕሉን ለንዴት ልዕልናውን ለትሕትና ግዕዛኑን ለግብርናት ሰጥቶ አዳምን ማዳኑን መናገር ነው።
አንድም ምዕመናን አምስቱን ግብራት ገንዘብ ማድረጋቸውን መናገር ነው። አምስቱ ግብራት የተባሉ ዓለም ተውላጠ ዓለም ምግባር መንፈሳዊ ቃለ መጻሕፍት ቃለ መምህራን ናቸው።
ዓለም ይህ ዓለም ነው ሁሉ የሚገኝ ከአለም ነውና።
ተውላጠ ዓለም እንደ የዋህ ጳውሊ፡፡ ባለጸጋ አባት ነበረው አባቱ ሙቶ በገንዘብ ከወንድሙ ጋራ ተጣልቶ ወደ ዳኛ ሲሄድ እንደአባቱ ያለ ባለጸጋ ሙቶ ወደ መቃብር ሲወስዱት አገኘ ይህ ምንድነው ብሎ ጠየቀ ባለጸጋ ነበር ሙቶ ሊቀብሩ ይወስዱታል አሉት። ለዚህ ብዬ ከወንድሜ ተጣላሁን አንተን ይምሰል ብሎ ጥሎለት ሄዷል።
ምግባር መንፈሳዊ እንደ አብርሃም መርዓዊ ነው፡፡ እድ ብርህት ከጫጕላው አውጥታ እየመራች ገዳም ወስዳዋለች።
ቃለ መጻሕፍት እንደ አባ ዕንጦንስ፡፡ ምንት ይበቊዖ ለሰብእ ለእመ ኵሎ ዓለመ ረብሐ ወነፍሶ ኃጕለ ያለውን ይዞ መንኖ ሄዷል።
ቃለ መምህራን እንደ አትናስያ፡፡ ምዕመናንን የምትረዳ ደግ ሴት ነበረች ሰይጣን በዝሙት ድል ነሣት ምዕመናንን የማትጠይቃቸው ሆነ ሰይጣን ልጃችንን ቀማን በተቻለህ እርዳን ብለው ከዮሐንስ ሐጺር ላኩ ሂዶ ንገሩልኝ አለ ነገሩለት ግባ በሉት አለች ገባ አስነጥፋ ና ከአጠገቤ ተቀመጥ አለችው በወንበር ከፊቷ ተቀምጦ እያያት ያለቅስ ጀመር ምነው ታለቅሳለህ አለችው መልከ መልካም ነሽና ብታሳዝኚኝ ነው አላት ይህማ ደስ ያሰኛል እንጂ ያሳዝናል አለችው መፍረስ መበስበስ አለና ምን ይሆናል አላት ለዚህ ምን ይበጃል አለችው ብትተዪው አላት ብተወው ጌታዬ ይምረኛል አለችው ይምርሻል አላት፡፡
አንድም እሱ በገባ ጊዜ ሲያሰስንዋት የነበሩ አጋንንት መብራት እንደ አበሩባቸው አርጋብ ሲወድቁባት ሲነሱባት አየ እንዲህ ሲሆኑብሽ አየሁ አላት ለዚህ ምን ይበጀኛል አለችው ብትተዪው፤ ብተወው ጌታዬ ይምረኛልን አለችው፤ አዎን ይምርሻል። ተከተዪኝ ብሏት ወጣ አብራው ወጣች አባቴ ቆየኝ ትለዋለች ድረሽብኝ ይላታል እግሯ አልችል ቢል ከልብሷ እየቀደደች እንደ ጫማ እያደረገች ትከተለዋለች። አባቴ ቆየኝ ትለዋለች ድረሺ ይላታል ከቦታው ደረሱ እሳቱን አንድዶላት ተቀመጠች እሱ እልፍ ብሎ ጸሎቱን ያዘ በዚያ ሌሊት አረፈች ሰዋስወ ብርሃን ተተክሎ መላእክት ሲወጡ ሲወርዱ ያያል ማዕርጉ ጽማዌ ነውና የተላኩበትን ግን አያውቅም ሲነጋ መልአክ መጥቶ ያች ያመጣሃት ሴት አርፋለች መቃብሯን አንበሳ ይቈፍርልሃልና ቅበራት አለው ይህስ ይሁን ዛሬ ሌሊት ስትወጡ ስትወርዱ ያየኋችሁ ምንድር ነው አለው ነፍሷን ስናሳርግ ነው አለው ተቀበላትን አለው አዎን ተከተዪኝ ብለሃት ተከትላህ በወጣች ጊዜ ተኃድገ ለኪ ብሏታል ብሎ ነግሮታል።
******
፵፭፡ ካዕበ ትመስል መንግሥተ ሰማያት ብእሴ ሠያጤ ዘየኃሥሥ ባሕርየ ሠናየ።
፵፭፡ መንግሥተ ሰማያት ሕገ ወንጌል፤ ሕገ ወንጌል ተስፋ፤ ተስፋ ኢየሱስ ክርስቶስ ብሩሃ ሲል ነው ዕንቊን የሚሻ ነጋዴን ትመስላለች።
******
ይቆየን፡፡
**************
መልካሙ በየነ
ደብረ ማርቆስ፤ ኢትዮጵያ
04/09/2011 ዓ.ም
No comments:
Post a Comment