Sunday, May 19, 2019

ወንጌል ቅዱስ ክፍል 95

====================
የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ቅዱስ ወንጌል።
ቅዱስ ማቴዎስ እንደ ጻፈው።
በእንተ ፈሪሳውያን ወሥርዓቶሙ።
ምዕራፍ ፲፭።
                    ******     
ዘከመ ተፈወሱ ካልአን ሕሙማን።
፳፱፡ ወኃሊፎ እግዚአ ኢየሱስ እምህየ በጽሐ ኀበ ሐይቀ ባሕር ዘገሊላ፤
                    ******     

፳፱፡ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከዚያ አልፎ ከገሊላ ባሕር ወደብ ደረሰ።
ወዓሪጎ ደብረ ነበረ ህየ፤
ከዚያ ከተራራ ላይ ወጥቶ ተቀመጠ።
                    ******     
፴፡ ወቀርቡ ኀቤሁ አሕዛብ ብዙኃን እንዘቦ ምስሌሆሙ ሐንካሳን ወዕውራን ወፅሙማን ወፅውሳን። ኢሳ ፴፭፥፭።
                    ******     
፴፡ ብዙ ሰዎች ዕውራንን ሐንካሳንን ደንቆሮዎችን ልምሾ የሆኑትንም ይዘው መጡ።
ወባዕዳነሂ ብዙኃነ ድውያነ
ሌሎችን ብዙ ድውያንን አመጡ።
ወገደፍዎሙ ታሕተ እገሪሁ ለእግዚእ ኢየሱስ።
ከእግሩ አፈሰሷቸው።
ወፈወሶሙ።
አዳናቸው።
                    ******     
፴፩፡ እስከ ሶበ አሕዛብ ያነክሩ እንዘ ይሬእዩ ከመ በሐማን ይትናገሩ።
                    ******     
፴፩፡ በሐማነ ሥጋ በተአምራት በሐማነ ነፍስ በትምህርት ሲናገሩ።
ወሐንካሳን የሐውሩ።
ሐንካሳነ ነፍስ በትምህርት ሲሂዱ ወዕውራን ይሬእዩ።
ዕውራነ ሥጋ በተአምራት ዕውራነ ነፍስ በትምህርት ሲያዩ አይተው አሕዛብ እስኪያደንቁ ድረስ ፣
ወሰብሕዎ ለአምላከ እስራኤል
ዘወሀበ ዘከመዝ ሥልጣነ ለሰብእ
ለሰው እንዲህ ያለ ሥልጣን የሰጠ ማለት አላመኑም ቢሉ ደግ ነቢይ ያስነሣልን ብለው፡፡ አምነዋል ቢሉ ለራሱ ድኅነት ይሻ የነበረ ሥጋን ከባሕርይ ልጅህ ጋራ አዋህደህ ድኅነትን እንዲያድል ያደረግኸው ብለው የእስራኤልን አምላክ አመሰገኑ።
                    ******     
በእንተ ካልዕ አብዝኆተ ኅብስት።
፴፪፡ ወጸውዖሙ እግዚእ ኢየሱስ ለአርዳኢሁ ወይቤሎሙ ያምህሩኒ እሉ ሕዝብ፡፡ ማር ፰፥፩።
                    ******     
፴፪፡ ደቀ መዛሙርቱን ጠርቶ እሊህ ሰዎች ያሳዝኑኛል አላቸው።
እስመ ናሁ ሠሉስ መዋዕል እምዘ በልቡ እክለ
እህል ከበሉ ሦስት ቀናቸው ነውና።
ወአልቦሙ ዘይበልዑ።
የሚበሉት የላቸውምና።
ወኢይቅድ እፈንዎሙ ርኁባኒሆሙ
እንደተራቡ ላሰናብታቸው አልወድም።
ከመ ኢይመጽልዉ በፍናት።
ከጐዳና በስልት እንዳይወድቁ
                    ******     
፴፫፡ ወይቤልዎ አርዳኢሁ አምአይቴ እንከ ለነ በገዳም ኅብስት ዘያጸግብ ለዘመጠነዝ ሕዝብ።
                    ******     
፴፫፡  ለዚህን ያህል ሰው የሚበቃ እንጀራ ከወዴት እናገኛለን አሉት።
                    ******     
፴፬፡ ወይቤሎሙ ሚመጠን ሓባውዝ ብክሙ።
                    ******     
፴፬፡  ምን ያህል እንጀራ አላችሁ አላቸው።
ወይቤልዎ ሰብዑ።
ሰባት እንጀራ
ወኅዳጥ ዓሣ
አንድ ዓሣ ሎምቢ ዓሣ አለ አሉት። ወገባሩ ኅዳጥ እንዲል።
                    ******     
፴፭፡ ወአዘዞሙ ለሕዝብ ይርፍቁ ዲበ ምድር፡፡
                    ******     
፴፭፡ ሕዝቡን ከምድር ተቀመጡ አላቸው።
                    ******     
፴፮፡ ወነሥአ ሰቡዓ ኅብስተ ወዓሣኒ
                    ******     
፴፮፡ ሰባቱን ኅብስት ዓሣውንም ያዘ።
ወይእተ ጊዜ አእኰተ።
ያን ጊዜ አመሰገነ
ባረከ።
ገመሰ።
ወፈተተ።
ቈረሰ።
ወወሀቦሙ ለአርዳኢሁ።
ስጡ ብሎ ለደቀ መዛሙርቱ ሰጣቸው።
                    ******     
፴፯፡ ወበልዑ ኵሎሙ ወጸግቡ።
                    ******     
፴፯፡ ሁሉም በልተው ጠገቡ።
ወዘተርፈ ፍተታተ አግኃሡ ሰብዓተ አስፈሬዳተ ምሉዓ። መሳይምተ መዛርዓ አክፋረ አስፈሬዳተ ይላል። የተረፈውን ፯ መሶብ እንቅብ ቅርጫት ማለት ነው መልተው አነሱ።
                    ******     
፴፰፡ ወእለሰ በልዕዎ የአክሉ ጣሃ እንበለ አንስት ወደቅ።
                    ******     
፴፰፡ የበሉት ሰዎች ከሴቶችና ከሕፃናት በቀር አራት ሽህ ያህል ይሆናሉ፣
(ሐተታ) እንዳለፈው ምዕራፍ ፲፬ ቊ ፳፩ ሰባት ማንሳታቸው በሰባቱ ዕለታት በ፯ ልዑካን ምሳሌ ፬ ሽህ ሰዎች በልተውለት የተረፈው በዘመነ ብሉይ ከተገለጸው ምሥጢር ከአራቱ ባሕርያት የተፈጠረ ሰው የተቻለውን ያህል ነሥቶለት የተረፈው በልበ ነቢያት እንደቀረ ያጠይቃል፡፡ አምስተኛ አልጨመረላቸውም በግዕዘ እንስሳ ናችሁ ሲል እንጀራውም ገብስ ነው ገብስ ምግበ እንስሳ ነው በግዕዘ እንስሳ አላችሁ ሲል።
አንድም ገዳም በሄዳችሁ ጊዜ ምግብ አታሻሽሉ ለማለት። ከአምስቱ አስራ ሁለት ከሰባቱ ሰባት አነሡ አለ ጥቂቱን ብዙ ብዙውን ጥቂት የማደርግ እኔ ነኝ ሲል።
                    ******     
፴፱፡ ወፈቲሖ አሕዛበ ዓርገ ውስተ ሐመር ወሖረ ውስተ ደወለ መጌዶል።
                    ******     
፴፱፡ ሕዝቡን አሰናብቶ በመርከብ ተጭኖ ወደ መጌዶል ሄደ።
                    ******     
ዘከመ ኀሠሠ ትእምርተ እምሰማይ።
ምዕራፍ ፲፮።
፩፡ ወመጽኡ ኀቤሁ ፈሪሳውያን ወሰዱቃውያን እንዘ ያሜክርዎ ወይሴእልዎ ትእምርተ እምሰማይ ያርእዮሙ፡፡ ማር ፰፥፲፮።
                    ******     
፩፡ ከዚህ በኋላ ሰዱቃውያንና ፈሪሳውያን ሲፈትኑት ከሰማይ ምልክት አሳየን ሊሉት መጡ፡፡
                    ******     
   ይቆየን፡፡
**************
መልካሙ በየነ
ደብረ ማርቆስ፤ ኢትዮጵያ
11/09/2011 ዓ.ም

No comments:

Post a Comment