====================
የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ቅዱስ ወንጌል።
ቅዱስ ማቴዎስ እንደ ጻፈው።
በእንተ ሃለየ ሄሮድስ ላዕለ ኢየሱስ።
ምዕራፍ ፲፬።
******
፲፭፡ ወምሴተ ከዊኖ ቀርቡ ኀቤሁ አርዳኢሁ ወይቤልዎ ገዳም ውእቱ ብሔር።
******
፲፭፡ ሲመሽ በመሸ ጊዜ ደቀ መዛሙርቱ ቀርበው አገሩ ምድረ በዳ ነው።
ወሰዓቱኒ ኃለፈ ፍትሖሙ ለሕዝብ።
ጊዜውም መሽቷል ሕዝቡን አሰናብታቸው አሉት።
ከመ ይሑሩ ውስተ አህጉር ወይሳሣየጡ ለርእሶሙ መብልዓ
ወደ ሀገር ገብተው ምግባቸውን ይገዙ ዘንድ።
(ሐተታ) በቤተ ሰብ ልማድ አለን አለን ባዮች ናቸውና አሁን ዝም ብለን ኋላ ለዚህ ሁሉ ሰው ምግብ አቅርቡ ቢለን ከወዴት እናመጣለን ብለው፡፡
******
፲፮፡ ወይቤሎሙ እግዚእ ኢየሱስ አኮ መፍትው ይሑሩ ርኁባሆሙ፡፡
******
፲፮፡ እንደ ተራቡ ሊሄዱ አይገባም አላቸው
አላ አንትሙ ሀብዎሙ ዘይበልዑ።
የሚበሉትን እናንተ ስጧቸው እንጂ
******
፲፯፡ ወይቤልዎ አልብነ ዝየ ዘእንበላ ኃምስ ኅብስት ወ፪ኤቲ ዓሣ
******
፲፯፡ ከዚህ ከሁለት ዓሣና ከአምስት እንጀራ በቀር ሌላ የለንም አሉት
******
፲፰፡ ወይቤልዎ አምጽእዎን ሊተ ዝየ።
******
፲፰፡ ይህስ ካለ ወዲህ አምጡልኝ አላቸው።
******
፲፱፡ ወአዘዞሙ ለሰብእ ይርፍቁ ዲበ ሣዕር።
******
፲፱፡ ከመስኩ ተቀመጡ አላቸው።
ወነሥአ ውእተ ኃምሰ ኅብስተ ወ፪ኤ ዓሣ ወነጸረ ሰማየ።
ሁለቱን ዓሣ አምስቱን እንጀራ ይዞ ወደ ሰማይ አየ።
(ሐተታ) ይህን ኅብስት የማበረክትበት ሥልጣን ከአንተ ጋራ አንድ ነው ሲል፡፡
አንድም ታምራት ይደረግልን ባላችሁ ጊዜ ወደ እግዚአብሔር አመልክቱ ለማለት አብነት ለመሆን።
ባረከ ገመሰ ቈረሰ
ወፈተተ አጠቃቀነ።
ወወሀቦሙ ለአርዳኢሁ።
ለደቀ መዛሙርቱ ስጡ ብሎ ሰጣቸው።
ወአርዳኢሁኒ አቅረቡ ለሕዝብ
ደቀ መዛሙርቱም ለሕዝቡ አቀረቡ በሱም እጅ በሐዋርያትም እጅ ሳለ ይበረክት ነበር በረከት መንፈሳዊ እስከ ምጽአት እንዳያቋርጥ ያጠይቃል፡፡
******
፳፡ ወበልዑ ኵሎሙ ወጸግቡ።
******
፳፡ ሁሉም በልተው ጸገቡ።
ወአግኃሡ ዘተርፈ ፍተታተ።
የተረፈውን አነሡ።
ወመልዓ አሠርተ ወ፪ተ መዛርዓ ምሉዓ፡፡
መሳይምተ አክፋረ አስፈሬዳተ ይላል ጋዘና መሶብ ቅርጫት ማለት ነው።
******
፳፩፡ ወእለሰ በልዕዎ የአክሉ ፶፻ ዕደው ዘእንበለ አንስት ወደቅ
******
፳፩፡ የበሉት ሰዎች ከሴቶችና ከሕፃናት በቀር ፭ሽ ያህል ይሆናሉ በሀገራቸው ሴትና ወንድ አቀላቅሎ መቊጠር የለምና ዘእንበለ አንስት አለ፤ ልጆችም አይበሉምና
አንድም ሴቶች ወንድ ሲያያቸው ያፍራሉና ሕፃናትም ከሚበሉት የሚያበላሹት ይበዛልና ፲፪ት ማንሳታቸው በአሥራ ሁለቱ ሥዩማን በአሥራ ሁለቱ ከዋክብት ምሳሌ፤ በልተውለት የተረፈው በዘመነ ሐዲስ የተገለጸ ምሥጢር ነው ከአራቱ ባሕርያት ከአምስተኛ ባሕርየ ነፍስ የተፈጠረ ሰው የሚቻለውን ያህል ነሥቶለት የቀረው በልበ ሐዋርያት እንደ ቀረ ያጠይቃል። አምስቱ የአምስቱ አዕማደ ምሥጢር ሁለቱ ዓሣ የፍቅረ ቢጽና የፍቅረ እግዚአብሔር አንድም የሥጋው የደሙ ምሳሌ።
የተረፈውንም ከማርያም መግደላዊት ቤት አኑረውት በዘመነ ደዌ ለፈውስ በዘመነ ቀጠና ለበረከት ይወስዱት ነበር፡፡ ሲመሽ ያደረገው ጧት ያላደረገው ስለምን ቢሉ ጧት አድርጎት ቢሆን ምሳቸውን የበሉ ምሳችንን በልተን ያልበሉ የበላነው ሳይስማማን ብንበላው በረከተ እንጂ እንዳይሉ ሁሉም በሚሹበት ጊዜ አደረገው ምሥጢሩ ግን በፍጻሜ ዘመን መንፈሳዊ ምግብ እመግባችኋለሁ ሲል ነው በገዳም ያደረገው ስለምን ቢሉ ለጊዜው ከመንደር አጠገብ አድርጎት ቢሆን ፈጣን ፈጣን ደቀ መዛሙርት አሉትና ከዚያም ከዚያም እያመጡ በላይ በላዩ እየጨመሩበት በረከተ እንዳይሉ። ፍጻሜው ግን እስራኤል በገዳም ፵ ዘመን መና የመገብሁ እኔ ነኝ ሲል፡፡
አንድም ከዚህ ዓለም አፍአ በምትሆን በመንግሥተ ሰማያት መንፈሳዊ ምግብ እመግባችኋለሁ ሲል። በመስክ ያደረገው ስለምን ቢሉ ለጊዜው ለልብሳችን ስንጠነቀቅ ባንበላው በረከተ እንጂ እንዳይሉ። ምሥጢሩ ግን በምቹ ቦታ በመንግሥተ ሰማይ አኖራችኋለሁ ሲል፡፡ በወሀ አጠገብ ያደረገው ስለምን ቢሉ ለጊዜው እጃችንን ባንታጠብ ተጸይፈን ባንበላው በረከተ እንዳይሉ። ምሥጢሩ ግን በጥምቀት በሚገኝ ክብር አከብራችኋለሁ ሲል።
******
ዘከመ ሖረ እግዚእ ኢየሱስ መልዕልተ ማይ።
፳፪፡ ወአገበሮሙ ሶቤሃ ለአርዳኢሁ ከመ ይእርጉ ውስተ ሐመር ወይቅድምዎ ኀበ ማዕዶተ ባሕር እስከ ሶበ ይፌንዎሙ ለአሕዛብ። ማር ፮፥፵፭።
******
፳፪፡ ከዚህ በኋላ ሕዝቡ ቢራቡ ያመሳል ቢታመሙ ይፈውሳል ቢሞቱ ያሥነሣል እንዲህ ያለውን ቢያነግሡት ምን ይብሳል ነገር ግን ማን ይይዝልናል ብለዋል ሐዋርያት አለን አለን ባዮች ናቸውና እኛ እያለን እኛ እንይዝላችኋለን ብለዋቸዋል ሕዝቡን እስኪያሰናብት ድረስ በመርከብ ተጭነው ባሕሩን ተሻግረው ይቆዩት ዘንድ ተሻግራችሁ ቈዩኝ አላቸው።
አንድም ሊይዙት ወደው ፈርተው ቁመዋል አውቆባቸው ሂዱ ብላችሁ አላቸው።
******
፳፫፡ ወእምዝ ፈቲሖ አሕዛበ ዓርገ ውስተ ደብር እንተ ባሕቲቱ ይጸሊ። ዮሐ ፮፥፲፭።
******
፳፫፡ ከዚህ በኋላ ሕዝቡን አሰናብቶ ለብቻው ሊጸልይ ወደ ተራራ ወጣ።
(ሐተታ) ሰውም አያነግሠኝ ልዑለ ባሕርይ ነኝ ሲል፡፡ ይጸሊ ማለቱ ታምራት ተደረገልን ብላችሁ ጸሎታችሁን አትተው ለማለት አብነት ለመሆን። ሲመሽ ብቻውን ከዚያ ነበር።
******
፳፬፡ ወሐመርሰ ናሁ ማዕከለ ባሕር ሀሎ።
******
፳፬፡ መርከቡ ግን እነሆ ከባህር መካከል ነበር።
ወርኍቅ እምሐይቅ መጠነ እስራ ወ፭ቱ ምዕራፍ።
ከወደቡ ሐያ አምስት ምዕራፍ ያህል ርቆ ነበር።
ወይትሀወክ እሞገድ።
ከማዕበሉ የተነሣ ይናወጽ ነበር
እስመ እምቅድሜሁ ውእቱ ነፋስ።
ነፋስ ከወደፊቱ ተነሥቶ ነበርና
******
፳፭፡ ወበራብዕት ሰዓተ ሌሊት መጽአ ኀቤሆሙ እግዚእ ኢየሱስ
እንዘ የሐውር ዲበ ባሕር።
******
፳፭፡ በአራተኛው ሰዓተ ሌሊት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በባሕር ላይ እየሄደ መጣ፡፡
(ሐተታ) ቀዳማይ አካች ካልዓይ አካች ሣልሳይ አካች ራብዓይ አካች አለና። ምሥጢሩ ግን በዐራተኛው ክፍለ ዘመን ጌታ ሰው መሆኑን ያጠይቃል።
******
፳፮፡ ወሶበ ርእይዎ አርዳኢሁ እንዘ የሐውር ዲበ ባሕር ደንገፁ ወተሐውኩ እንዘ ይብሉ ምትሐት ውእቱ።
******
፳፮፡ ደቀ መዛሙርቱ በባሕር ሲሄዱ ባዩት ጊዜ ምትሐት መሰሏቸው ፈሩ ደነገጡ።
(ሐተታ) ከሄሮድስ ከተማ ያስወጣነው ሰይጣን በየብስ መጣላት ባይሆንለት ነፋስ አምጥቶ ማዕበል ሞገድ አስነሥቶ ሊያሰጥመን መጣ ብለው።
ወእምግርማሁ አውየዉ።
እሱን ከመፍራታቸው የተነሣ አሰምተው ተናገሩ።
******
፳፯፡ ወበጊዜሃ ተናገሮሙ እግዚእ ኢየሱስ እንዘ ይብል አነ ውእቱ ወኢትፍርሁ።
፳፯፡ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ፈጥኖ እኔ ነኝ አትፍሩ አላቸው።
******
ይቆየን፡፡
**************
መልካሙ በየነ
ደብረ ማርቆስ፤ ኢትዮጵያ
07/09/2011 ዓ.ም
Wednesday, May 15, 2019
ወንጌል ቅዱስ ክፍል 91
Subscribe to:
Post Comments (Atom)
No comments:
Post a Comment