Friday, May 3, 2019

ወንጌል ቅዱስ ክፍል 80

====================
የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ቅዱስ ወንጌል።
ቅዱስ ማቴዎስ እንደ ጻፈው።
በከመ ተፈነዉ ሐዋርያት።
ምዕራፍ ፲፩።
                    ******     
፳፡ ወእምዝ አኀዘ እግዚእ ኢየሱስ ይኂሶን ለአህጉር እለ በውስቴቶን ገብረ ኃይለ ብዙኃ
                         ******     
፳፡ ከዚህ በኋላ ኢየሱስ ክርስቶስ ደጋግ ታምራት ያደረገባቸውን ምኵራባት ይነቅፋቸው ጀመር።
እስመ ኢነስሐ።
አላመኑምና፡፡
                    ******     
፳፩፡ ወይቤሎን አሌ ለኪ ኮራዚ
                    ******     
፳፩፡ ስመ ምኩራብ ነው ኮራዚ ወዮልሽ እያለ። ሉቃ ፲፥፲፫፡፡
አሌ ለኪ ቤተ ሳይዳ።
ቤተ ሳይዳ ወዮልሽ ።
እስመ ሶበ በጢሮስ ወበሲዶና ተገብረ ኃይል ዘተገብረ በውስቴትክን።
በናንተ የተረደገው ታምራት በጢሮስ በሲዶና ተደርጎ ቢሆን።
እምነስሐ በሐመድ።
ማቅ ለብሰው አመድ ነስንሰው ንስሐ በገቡ ነበር።
(ሐተታ) በጢሮስ ኪራም ፭፻ ዘመን ኑሮ የለምን በሲዶናስ ኤልያስ ፩ ምውት ኤልሳዕ ሁለት ምውት አስነሥቶ የለም ቢሉ በኒያ ሕፀፅ አለበት በጌታ ግን ሕፀፅ የለበትምና የኒያ የጸጋ ነው የጌታ ግን የባሕርይ ነውና፡፡
                    ******     
፳፪፡ ወባሕቱ እብለክሙ ጤሮስ ወሲዶና ይረክባ ሳሕተ ፈድፋደ እምኔክን አመ ዕለተ ደይን።
                    ******     
፳፪፡ ነገር ግን ጠሮስ ሲዶና በፍርድ ቀን ከናንተ ይልቅ ዕረፍትን ያገኛሉ ብዬ እነግራችኋለሁ
                    ******     
፳፫፡ ወአንቲኒ ቅፍርናሆም ለእመ እስከ ሰማይ ትትሌዓሊ እስከ ሲኦል ትወርዲ።.
                    ******     
፳፫፡  አንቺም ቅፍርናሆም እስከ ሰማይ ብትደርሺ እስከ ሲኦል ትወርጂ ዘንድ አለሽ። አንቺም ቤተ አይሁድ ክርስቶስን ዕሩቅ ብእሲ እስከ ማለት ብትደርሺ ገሃነም ትወርጂ ዘንድ አለሽ።
እስመ ሶበሁ ተገብረ ኃይል ዘተገብረ በውስቴትኪ እምሀለወት እስከ ዮም
ባንቺ የተደረገ ታምራት በሰዶም ተደርጎ ቢሆን ንስሐ ገብታ ከተፈረደባት ፍርድ ድና እስከሁን በሕይወት በኖረች ነበር።
(ሐተታ) በሰዶም ሎጥ በእንባው ደረቅ እንጨት አለምልሟል መላእክትንስ እንግድነት ተቀብሎ የለም ቢሉ የሱ የጸጋ ነው የጌታ ግን የባሕርይ ነውና፤ በሱ ሕፀፅ አለበት በጌታ ግን ሕፀፅ የለበትምና።
                    ******     
፳፬፡ ወባሕቱ እብለክሙ ከመ ምድረ ሰዶም ሳሕተ ትረክብ ፈድፋደ እምኔኪ አመ ዕለተ ደይን
                    ******     
፳፬፡ ነገር ግን በፍርድ ቀን ካንቺ ይልቅ ሰዶም ዕረፍትን ታገኛለች ብዬ እነግራችኋለሁ።
                    ******     
፳፭፡ ወይእተ ጊዜ አውሥአ እግዚእ ኢየሱስ ወይቤ አአምነከ አባ እግዚአ ሰማያት ወምድር። ሉቃ ፲፩፥፩፡፡
                    ******     
፳፭፡ በዚህ ያልተያዘ በሉቃስ የተያዘ ነው። ሰብዓ አርድእት መጥተው አጋንንት ገረሩ ለነ በስምከ ብለውታል እነሱ ማመስገን ባይቻላችው በሳቸው ተገብቶ ያመሰግንላቸዋል። ያንጊዜ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሰማዩን ምድሩን የፈጠርህ አባቴ አመሰግንሃለሁ አለ ወልድየ እመኖ እንዲል አእኩቶ ሲል።
ዘኃባዕኮ ለዝንቱ እምጠቢባን ወማእምራን ወከሠትኮ ለሕፃናት
የኔን አምላክነት አዋቆች ነን ከሚሉ ከጸሐፍት ከፈሪሳውያን ሠውረህ ለሕፃናተ አእምሮ ለሐዋርያት የገለጥኸው፡፡
                    ******     
፳፮፡ እወ አባ እስመ ከመዝ ኮነ ሥምረትከ በቅድሜከ።
                    ******     
፳፮፡ አዎን አባቴ አዋቂ ነን ከሚሉ መሠወር አላዋቂ ነን ለሚሉ መግለጥ ቀድሞም ልማድህ ነው ምሥጢረ ደኅነትን ከሰብአ ትካት ሰውረህ ለኖኅ ከሰብአ ሰዶም ሰውረህ ለሎጥ እንደገለጥህ።
                    ******     
፳፯፡ ኵሉ ተውሀበኒ እምኀበ አቡየ። ዮሐንስ ፮፥፵፮። ፯፥፳፰-፳፱። ፰፥፲፱፡፡ ፲፥፲፭፡፡
                    ******     
፳፯፡ ሁሉ ካባቴ ዘንድ ተሰጠኝ። የተሰጠውስ በማኅፀን ሲዋሐድ ነው
ወለዘፈቀደ ወልድ ይከሥት ሎቱ ለማለት ነው እንጂ፡፡
ወአልቦ  ዘየምሮ ለወልድ ዘእንበለ አብ።
አብን ወላዲ ካላለ ወልድን ተወላዲ ብሎ የሚያምን የለም።
ወአልቦ ዘየአምሮ ለአብ ዘእንበለ ወልድ ወልድን ተወላዲ ከላለ አብን ወላዲ ብሎ የሚያምን የለም፡፡
አንድም አብ ዝንቱ ውእቱ ወልድየ ብሎ ሳይመሰክርለት ወልድን የሚያውቀው አልነበረም።
ወአልቦ ወጸአኩ እም ኀበ አብ ወመጻእኩ አቡየ ፈነወኒ ዘርእየ ኪያየ ርእዮ ለአቡየ አነ ወአብ አሐዱ ንሕነ ብሎ  ሳይመሰክር አብን የሚያውቀው አልነበረም፤
አንድም ከአብ በቀር አብ ያውቀዋል እንጂ ያለ አብ ወልድን በባሕርዩ የሚያውቀው የለም።
ወአልቦ
ከወልድ በቀር ወልድ ያውቀዋል እንጂ ያለ ወልድ አብን በባሕርዩ የሚያውቀው የለም።
ወለዘፈቀደ ወልድ ይከሥት ሎቱ።
ወልድ ሊገልጽለት ለወደደው ይገልጽለታል ፈቀደ ለሁለቱም
                    ******     
፳፰፡ ንዑ ኀቤየ ኵልክሙ ስሩሃን ወክቡዳነ ፆር።
                    ******     
፳፰፡ ሸክም የከበዳችሁና የደከማችሁ ሁሉ ወደኔ ኑ ማለት በፃማ ኦሪት በፃማ ኃጢአት የደከማችሁ ፆረ ገሃነም የረበናት ትብትብ ያለባችሁ በኔ እመኑ፣
                    ******     
፳፱፡ ወአነ አዓርፈክሙ። ኤር ፮፥፲፪፡፡ ዮሐንስ ፭፥፫።
                    ******     
፳፱፡ ዕረፍተ ነፍስ ሰጥቼ አሳርፋችኋለሁ፡፡ አብነት ንሥኡ ፁሩ ይላል። ቀንበሬን ተሸከሙ ማለት ሕጌን ያዙ።
(ሐተታ) ቀንበር አላት ወንጌልን ቀንበር ሁለቱን በሮች አንድ እንድታደርግ ወንጌልም ሕዝብና አሕዛብን አንድ ታደርጋለችና።
ተመሀሩ ወአእምሩ እምኔየ ከመ የዋህ አነ ወትሑት ልብየ
የዋህ ትሑት እንደሆንኩ መጠን ከኔ ተምራችሁ ዕወቁ
ወትረክቡ ዕረፍተ ለነፍስክሙ
ዕረፍተ ነፍስ ታገኛላችሁ።
                    ******     
፴፡ እስመ አርዑትየኒ ሠናይ።
                    ******     
፴፡ ቀንበሬ ልዝብ ነውና።
ወፆርየኒ ቀሊል።
ሸክሜ ቀሊል ነውና። ሕጌ ወንጌል ደግ ሕግ ናትና። ትእዛዜም ቀሊል ነውና። ከዚህ የከበደን አለ ለዘሂ ጸፍአከ መልታሕቴከ ዘየማን ሚጥ ሎቱ ከልዕታሂ ወለዘሂ አበጠከ አሐደ ምዕራፈ ሑር ምስሌሁ ፪ተ ወለዘሂ ይፈቅድ ይትዓገልከ መልበሰከ ኅድግ ሎቱ ክዳነከሂ ትላለች ከዚህ የከበደ ምን አለና እንዲህ አለ ቢሉ አደርጋዋለሁ በሚል ዘንድ ቀሊል ነውና።
አንድም ለወጣንያን ክቡድ ቢሆን ለፍጹማን ቀሊል ነውና።
አንድም ከሕገ ኦሪት ሲለይ ነው። ኦሪት ውገሩ ስቀሉ ብላ ካሰናበተች በኋላ ምላሽ የላትም ወንጌል ግን በንስሐ ትላለችና ንስሐውን ቅሉ ስብዓ በበስብዕ ትላለችና። ሕግሰ መሢሐዊት ተራኅርኃት እንዲል፡፡
አንድም ኦሪት ፈጽማችሁ ጽደቁ ትላለች። ወንጌል ግን በክርስቶስ ፈጻሚነት ትላለችና።
አንድም ከሕገ አረሚ ሲለይ ሕገ አረሚ ላህምሰ ኅልቀ ሡዕ ሰብአ ትላለች በወንጌል ግን ይህ ሁሉ የለምና። ከሕገ አሕዛብ ሲለይ። አሕዛብ ከዱር ገብተው ዛፉን ቈርጠው እጅ እግር ሲያወጡ ቀለሙን ንድፉን ሲያከናውኑ ድካም አለበትና፡፡
                    ******     
ምዕራፍ ፲፪።
በእንተ ሰዊት።
፩፡ ወበውእቱ መዋዕል ወፈረ እግዚእ ኢየሱስ በሰንበት እንተ ማዕከለ ገራውህ። ማር ፪፥፳፫፡፡ ሉቃ ፮፥፩።
፩፡ በዚያ ወራት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ቅዳሜ በእርሻ መካከል ሄደ።
                    ******     
   ይቆየን፡፡
**************
መልካሙ በየነ
ደብረ ማርቆስ፤ ኢትዮጵያ
25/08/2011 ዓ.ም

No comments:

Post a Comment