====================
የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ቅዱስ ወንጌል።
ቅዱስ ማቴዎስ እንደ ጻፈው።
ከመ ተወለጠ ኢየሱስ በደብረ ታቦር።
ምዕራፍ ፲፯።
******
፩፡ ወእምድኅረ ስሱ መዋዕል ነሥኦሙ እግዚእ ኢየሱስ ለጴጥሮስ ወለያዕቆብ ወለዮሐንስ እኁሁ ወአዕረጎሙ ደብረ ነዋኃ እንተ ባሕቲቶሙ። ማር ፱፥፩፡፡ ሉቃ ፱፥፳፰
******
፩፡ ስለ ሦስት ነገር ያመጣዋል። አማን እብለክሙ ቦ እምእለ ሀለዉ ይቀውሙ ዝየ አለ ኢይጥዕምዎ ለሞት እስከ አመ ይሬእይዎ ለወልደ እጓለ እመሕያው እንዘ ይመጽእ በመንግሥቱ ብሎ ነበርና ከዚያ ለማያያዝ፡፡ እሞታለሁ ቢለው ቅዱስ ጴጥሮስ ሐሰ ለከ ብሎት ነበርና ሎቱ ስምዕዎ ለማለት በባሪያ ቃል የተነገረውን በጌታ ቃል ለማስመስከር። ከመ ፩ዱ እምነቢያት ብለውታልና እግዚአ ነቢያት እንደሆነ ለማጠየቅ፡፡ የስድስተኛው ድኅር ሰባት ነው። በቂሳርያ መነ ይብልዎ ሰብእ ለወልደ እጓለ እመሕያው ባላቸው በሰባተኛው ቀን ሦስቱን ባለሟሎቹን ለብቻቸው ወደ ተራራ ይዟቸው ወጣ።
(ሐተታ) ዝቅ ብሎ ቢሆን በነቁ ነበር። ከፍ ብሎ ቢሆን በዘነጉ ነበርና አመሀይ ቀን ሽቶ። ባለሟሎቹስ እነማናቸው ቢሉ ጌታ እንደ ሰው ወረተኛ ነውን ጥንተ ባለሟሎቹ ናቸው። እኒህንስ ባለሟል ያደረገበት ምንድ ነው ቢሉ አልታወቀም ሙሴን ለምስፍና አሮንን ለክህነት የመረጠበት ግብር እንዳልታወቀ።
አንድም ታውቋል ክህደት በኒህ ጸንቷልና ጴጥሮስ እሞታለሁ ቢለው ሐሰ ማለቱ ሹመት ሽልማት ሽቶ አይደለምን እኒያስ አሐድነ በየማንከ ወአሐድነ በፀጋምከ ማለታቸው ሹመት ሽልማት ሸተው አይደለምን።
አንድም ለፍቅሩ ይሳሳሉና በፍቅሩ ይናደዳሉና ጴጥሮስ እመውት ቢለው ሐሰ ማለቱ ቢናደድ አይደለምን እኒያስ ትክሉኑ ሰትየ ፅዋዕ ዚአነ እሰቲ ቢላቸው እወ ንክል ማለታቸው ቢናደዱ አይደለም ለፍቅሩ ይሳሳሉና በፍቅሩ ይናደዳሉና ስምንቱን ከእግረ ደብር ትቶ ሦስቱን ይዟቸው ወጥቷል። ስለምን ቢሉ በይሁዳ ምክንያት። ይዞት እንዳይወጣ ያአትትዎ ለኃጥእ ከመ ኢይርአይ ስብሐተ እግዚአብሔር ተብሎ ትንቢት ተነግሮበታል፡፡ ለይቶም እንዳይተወው ከምሥጢረ መንግሥቱ ቢለየኝ ከሞቱ ገባሁበት ባለ ነበርና ነገር ግን በርእሰ ደብር ለሦስቱ የተገለጠ ምሥጢር በእግረ ደብር ላሉ ለስምንቱም ተገልጧል። በደብረ ሲና ለሰባ ሊቃናት የተገለጸ ምሥጢር በከተማ ላሉ ለኤልዳድ ለሙዳድ እንደተገለጸ። ተራራ የወንጌል ምሳሌ ተራራ ሲወጡት ያጥራል ከወጡት በኋላ ግን ጭንጫውን ግጫውን ሲያሳይ ደስ ያሰኛል። ወንጌልም ሲማሯት ታጽራለች። ከተማሯት በኋላ ግን ጽድቅና ኃጢአት ለይታ ስታሳውቅ ደስ ታሰኛለችና።
አንድም ተራራ የመንግሥተ ሰማያት ተራራን በብዙ ፃእር እንዲወጡት መንግሥተ ሰማይንም በብዙ መከራ ያገኛታልና። እስመ በብዙኅ ፃማ ሀለወነ ንባእ ለመንግሥተ እግዚአብሔር እንዲል፡፡ ተራራውንም ሐዋርያት በሲኖዶስ ታቦር ብለው አንሥተውታል። በታቦር ያደረገው በሌላ ያላደረገው ስለምን ቢሉ ትንቢቱ ምሳሌው ሊፈጸም ትንቢት ታቦር ወአርሞንዔም በስመ ዚአከ ይትንፌሥሑ ተብሎ ተነግሯራል። ምሳሌ ባርቅ ሲሳራን ድል ነሥቶበታል። ጌታም በልበ ሐዋርያት ያደረ ሰይጣንን ድል ይነሣበታልና። በተራራ ያደረገው በመንደር ያላደረገው ስለምን ቢሉ በመካከል አድርጎት ቢሆን ምሥጢር አፈሳ በሆነ ነበርና። ስለዚህ በተራራ አደረገው።
******
፪፡ ወተወለጠ አርአያሁ በቅድሜሆሙ።
******
፪፡ መልኩ በፊታቸው ተለወጠ። ወእምድኅረ ውላጤ ይመጽእ ካልዕ ውላጤ እንዳለው ያለ አይደለም ሦስቱ ክንድ ከስንዝር አካል ምሉዕ ብርሃን ሁኑዋል ጽጌያት ከአዕፁቃቸው እንዲፈነዱ።
ወአብርሃ ገጹ ከመ ፀሐይ።
እንደ ፀሐይ ብሩህ ሆነ።
ወአልባሲሁኒ ኮነ ፀዓዳ ከመ በረድ።
ልብሱ እንደ 'በረድ ፀዓዳ ሆነ።
ይህ ሁሉ ጌትነቱን ገለጸ ማለት ነው።
******
፫፡ ወናሁ አስተርአዩ ሙሴ ወኤልያስ እንዘ ይትናገሩ ምስሌሁ።
******
፫፡ ሙሴ ኤልያስ ከእሱ ጋራ ሲናገሩ ተሰሙ። ሙሴ ኤልያስ መሆናቸው በምን ታውቋል ቢሉ ሙሴ በልቱትነቱ ኤልያስም በፀጓርነቱ። በነፍስስ ልቱትነት የለም ካባ ዕንጦንስ ዘንድ እንኳ ሲላክ ዘፍንው በነፍሱ ይለዋል በአካለ ነፍስ መጥቶ ተርጉሞላቸዋል ብሎ ብሩህ ሆኖ ተወልዷል ይህ ጸጋው ነው አይነሣውምና ኤልያስን ዘጥብሉል በአጽርቅተ እሳት ይለዋል ይህ ጸጋው ነው አይነሣውምና በዚህ ታውቋል።
አንድም ባነጋገራቸው ታውቋል። ሙሴ የኔን የሙሴን ጌታ ማን ሙሴ ይልሃል እግዚአ ይበሉህ እንጂ። ኤልያስም የኔን የኤልያስን ጌታ ማን ኤልያስ ይልሃል እግዚአ ኤልያስ ይበሉህ እንጂ ሲሉ ተሰምተዋል።
አንድም ሙሴ እኔ ባሕር ብከፍል ጠላት ብገድል ደመና ብጋርድ መና ባወርድ እስራኤልን ከክፋታቸው መልሶ ማዳን አልተቻለኝም ላንተ ግን መልሶ ማዳን ይቻልሃል። ኤልያስም እኔ ሰማይ ብለጉም እሳት ባዘንም እስራኤልን ከክፋታቸው መልሶ ማዳን አልተቻለኝም ላንተ ግን መልሶ ማዳን ይቻልሃል ሲሉ ተሰምተዋል።
አንድም ምውቱ ለሕያው ሕያው ለምውት ሲጸልዩ ተሰምተዋል። ምውቱ ለሕያው አቤቱ ሁሉን ለንስሐ ሳታበቃ በሞት ባትጠራው የሚሻል ይመስለኛል ሲል ሕያው ለምውት የሰው ፍቅር አገብሮህ ልትሞት ወደዚህ ዓለም መጣህን ሲል።
እነዚህንስ ያመጣበት ምክንያት ምንድነው ቢሉ ሙሴ ፊትህን ላየው እወዳለሁ ቢለው ገጽየሰ ኢያስተርኢ ለከ ወድኅረሰ ትሬኢ። መሥዋዕት ሆኜ በምቀርብበት ጊዜ በደብረ ታቦር እገለጽልሃለሁ ብሎት ነበርና። ኤልያስንም አንተሰ ትከውነሂ ስምዓ በደኃሪ መዋዕል ብሎት ነበርና።
ስለምን ሁለቱን ከነቢያት ሦስቱን ከሐዋርያት አመጣ ቢሉ ተራራ የቤተ ክርስቲያን ምሳሌ። በቤተ ክርስቲያን ብሉይ ሐዲስ እንዲነገሩ ለማጠየቅ፤
አንድም የመንግሥተ ሰማያት ምሳሌ። ነቢያትም ሐዋርያትም አንድ ሁነው እንዲወርሷት ለማጠየቅ።
ከመዓስባን ሙሴን ከደናግል ኤልያስን አመጣ። ደናግል እንጂ መዓስባን አይወርሷትም ባሉ ነበርና ደናግልም መዓስባንም አንድ ሁነው እንዲወርሷት ለማጠየቅ።
ከምውታን ሙሴን ከሕያዋን ኤልያስን አመጣ። ንሕነ ሕያዋን የተባሉና ኢንበጽሖሙ ለምውታን የተባሉ አንድ ሁነው እንዲወርሷት ለማጠየቅ።
******
፬፡ ወአውሥአ ጴጥሮስ ወይቤሎ ለአግዚአ ኢየሱስ እግዚኦ ሠናይ ለነ ሀልዎ ዝየ።
******
፬፡ ቅዱስ ጴጥሮስ ከዚህ መኖር ለኛ በጓችን ነው አለው። አንተ የወትሮ ሥራህን እየሠራህ ብንራብ እያመሳኸን ብንታመም እየፈወስኸን ብንሞት እያነሣኸን። ሙሴ የወትሮ ሥራውን እየሠራ ደመና እየጋረደ መና እያወረደ ባሕር እየከፈለ ጠላት እየገደለ። ኤልያስ የወትሮ ሥራውን እየሠራ ሰማይ እየለጐመ እሳት እያዘነመ ዝናም እያቆመ በዚህ መኖር ለኛ በጎአችን ነው
ወእመሰ ትፈቅድ ንግበር በዝየ ፫ተ ማኅደረ።
ሐሰ ለከ ቢለው ገሥፆት ነበርና ቢሆንስ የእኔን ነገር አትወድልኝም እንጂ ብትወድልኝስ ከዚህ ሦስት አዳራሽ እንሥራ።
አሐደ ለከ።
አንዱን ላንተ።
ወአሐደ ለሙሴ።
አንዱን ለሙሴ።
ወአሐደ ለኤልያስ።
አንዱን ለኤልያስ።
(ሐተታ) እነዚህን ቀኛዝማችነት ግራዝማችነት ይሾሙ ያለ ይመስላል። የእሱን አልተናገረም ቢትወደድነት የለመነ ይመስላል።
******
፭፡ ወእንዘ ይትናገሩ መጽአ ደመና ብሩህ ወጸለሎሙ፡፡ ማቴ ፫፥፲፯፡፡ ፪፡ጴጥ ፩፥፲፯፡፡
******
፭፡ ይኸን ሲናገሩ ብሩህ ደመና መጥቶ ጋረዳቸው ወሶበ ቦኡ ውስተ ደመና ይላል በሉቃስ ንጉሥ በትርሽማ ድንኳን ሳለ በላይ መላጃ ድንኳን ቢተክሉበት ንጉሥ ከድንኳን ገባ እንዲባል።
ወናሁ መጽአ ቃል እምውስተ ደመና ዘይብል ዝንቱ ውእቱ ወልድየ ዘአፈቅር ዘቦቱ ሠመርኩ።
ከደመናው ልመለክበት የወደድሁት ለተዋሕዶ የመረጥሁት ልጄ ይህ ነው የሚል ቃልተሰማ።
ወሎቱ ስምዕዎ
እሞታለሁ ቢላችሁ አትሞትም አትበሉት ተቀበሉት።
******
፮፡ ወሰሚዖሙ አርዳኢሁ ወድቁ በገጾሙ።
******
፮፡ ደቀ መዛሙርቱ ይኸን ሰምተው ደነገጹ።
ወፈርሁ ጥቀ፡፡
ፈጽመው ፈሩ።
(ሐተታ) ዮሐንስን ደነገጠ አላለውም እኒህን ደነገፁ አለ እንደምነው ቢሉ። ዮሐንስ አልተጠራጠረምና ደንገፀ አላለውም እኒህን ተጠራጥረዋልና ደነገጡ አለ።
አንድም አታስደንግጥ ያለው አያስደነግጥምና ዮሐንስ አልደነገፀም አለ። አታስደንግፅ ያላለው ያስደነግጻልና እኒህን ደነገጹ አለ።
******
፯፡ ወቀርበ እግዚእ ኢየሱስ ወገሠሦሙ
******
፯፡ ጌታ ቀርቦ ያዛቸው።
ወይቤሎሙ ተንሥኡ ወኢትፍርሁ።
አይዟችሁ ተነሡ አላቸው።
******
ወአንሥኡ አዕይቲሆሙ።
******
፰፡ ዓይናቸውን አቅንተው አዩ።
ወአልቦ ዘርእዩ ወኢመነሂ ዘእንበለ እግዚእ ኢየሱስ ባሕቲቱ
ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስን አዩ እንጂ ማነንም ማን አላዩም።
******
፱፡ ወእንዘ ይወርዱ እምደብር አዘዞሙ እግዚእ ኢየሱስ እንዘ ይብል ኢትንግሩ ወኢለመኑሂ ዘርኢክሙ እስከ አመ ወልደ አጓለ እመሕያው እሙታን ይትነሣእ።
******
፱፡ ጌታም ከተራራው ሲወርዱ ወልደ እጓለ እመሕያው ክርስቶስ ከሙታን እስኪነሣ ድረስ ያያችሁትን የሰማችሁትን አትናገሩ አላቸው።
(ሐተታ) ውዳሴ ከንቱ አይሻምና የሚያምኑበት ጊዜ አልደረሰምና እስከ ትንሣኤ።
አንድም መከራን ወደኋላ አድርጎ ክብርን መናገር አይገባምና፡፡
አንድም ሰውን ሁሉ እየሰበሰበ መንግሥቴን ላሳያችሁ እያለ ምትሐት ያሳያል ሆነ ባሉት ነበርና።
******
፲፡ ወተስእልዎ አርዳኢሁ እንዘ ይብሉ እፎ ይብሉ ጸሐፍት ኤልያስ ሀለዎ ይምጻእ ቅድመ
******
፲፡ መውደቃቸው ሞት መነሣታቸው ትንሣኤ መስሏቸው ጸሐፍት ኤልያስ አስቀድሞ ይመጣ ዘንድ እንዳለው የሚናገሩት እንደምን ነው አሉት።
******
፲፩፡ ወአውሥአ እግዚእ ኢየሱስ።
******
፲፩፡ ጌታም መለሰ።
ወይቤሎሙ እወ ኤልያስ ይቀድም መጺአ።
አዎን ኤልያስ አስቀድሞ ይመጣል።
ወያስተራትዕ ኵሎ።
ሁሉን ያከናውናል።
******
፲፪፡ ወባሕቱ እብለክሙ ከመ ኤልያስ ወድአ መጽአ።
******
፲፪፡ ነገር ግን ኤልያስ ፈጽሞ መጥቶ እንዳለ።
ወኢያእመርዎ።
እንዳላወቁት ማለት እንዳልተቀበሉት እነግራችኋለሁ።
ወባሕቱ ገብሩ ላዕሌሁ ኵሎ ዘከመ ፈቀዱ ።
የወደዱትን አደረጉበት እንጂ ማለት ዓስበ ዘማ አደረጉበት እንጂ
ወከማሁ ለወልደ እጓለ እመሕያውኒ ሀለዎ ይሕምም እምኔሆሙ።
ወልደ እጓለ እመሕያው ክርስቶስም እንደሱ ከሳቸው መከራ ይቀበል ዘንድ አለው።
******
ወእምዝ አእመሩ አርዳኢሁ ከመ በንእ ዮሐንስ ይቤሎሙ
******
፲፫፡ ከዚህ በኋላ ደቀ መዛሙርቱ ገብሩ ላዕሌሁ ያለውን ሰምተው የነገራቸው ስለ ዮሐንስ መጥምቅ እንደሆነ አወቁ ዮሐንስ መጥምቅ ነው አሉ።
******
በእንተ ወርኃዊ ዘይፄአር።
፲፬፡ ወበጺሖ ኀበ አሕዛብ ይቤሎሙ ምንትኑ ትትኀሠሥዎሙ፡፡ ማር ፪፥፲፮፡፡ ሉቃ ፱፥፴፰።
፲፬፡ ከሕዝቡ በደረሰ ጊዜ ለምን ታዳክሟቸዋላችሁ አላቸው።
******
ይቆየን፡፡
**************
መልካሙ በየነ
ደብረ ማርቆስ፤ ኢትዮጵያ
14/09/2011 ዓ.ም
Wednesday, May 22, 2019
ወንጌል ቅዱስ ክፍል 98
Subscribe to:
Post Comments (Atom)
No comments:
Post a Comment