====================
የጌታችን
የኢየሱስ ክርስቶስ ቅዱስ ወንጌል።
ቅዱስ
ማቴዎስ እንደ ጻፈው ።
ምዕራፍ
፪።
******
፲፪፡ ወነገሮሙ በህልም ከመ ኢይግ ብኡ ኅበ ሄሮድስ።
******
፲፪፡ በሄሮድስ በኵል አንዳይመለሱ በራእይ ነገራቸው።
ከነገ ከሠልስት ይመጣሉ ሲል እመቤታችን መንገድ እንድትገፋ ሃይማኖት እንዲሰፋ። በመጡበት የተመለሱ እንደ ሆነ ሃይማኖት ይጸናል እንጂ። አይሰፋም
ባልመጡበት ቢመለሱ ግን ያልሰማው እየሰማ ይሰፋልና።
አንድ መንገድ እንዲቀርባቸው
ሁለት ዓመት የመጡትን በአርባ
ቀን ገቡ የሚል ነውና።
ወእንተ ከልዕ ፍኖት ገብኡ ወአተዉ ብሔሮሙ። በሌላ ጎዳና በሌላ ኃይለ ቃል በሌላ ሃይማኖት ወደ ሀገራቸው
ተመልሰው ገቡ። በሌላ ጎዳና ሁለት ዓመት የሄዱትን በአርባ
ቀን ገብተዋል።
በሌላ ኃይለ ቃል አይቴ ሀሎ እያሉ መጥተው
ነበር። ረከብናሁ እያሉ ተመልሰዋል በሌላ ሃይማኖት ንጉሥ እያሉ መጥተው ነበር አምላክ እያሉ ተመልሰዋል።
******
፲፫፡ ዘከመ ጐየ ውስተ ምድረ ግብፅ ወእምድኅረ ኃለፉ እሉ ናሁ መልአከ እግዚአብሔር አስተርአዮ በሕልም ለዮሴፍ።
******
፲፫፡ ወእንተ ካልዕ ፍኖት ገብኡ
ወአተዉ ብሔሮሙ ብሎ ነበርና
ሰብአ ሰገል ከሄዱ በኋላ ከእግዚአብሔር የታዘዘ መልአክ
ለዮሴፍ በሕልም ነገረው።
ሳሉ አለመንገሩ ከሄዱ በኋላ መንገሩ ስለምን ነው ቢሉ። ሰብአ ሰገል ሳሉ ነግሮት ቢሆን
ሲሰደድ አይተው አምላክነቱን
በተጠራጠሩ ነበርና።
አንድም ከልቀረስ ይዘነው እንሂድ ባሉ ነበርና። ይዘውትም እንዳይሄዱ የጌታ ስደቱ ወደ ግብፅ ነው እንጂ
ወደ ባቢሎን አይደለምና።
እንዘ ይብል ተንሥእ ወንሣእ ሕፃነ ወእሞ ወጉየይ ውስተ
ምድረ ግብፅ። ተነሥተህ
እናቱን ብላቴናውን ይዘህ ወደ ግብፅ ሂድ ብሎ ነገረው፡፡ (ሐተታ)
ሕፃነ ወእሞ አለ ሕፃነ ብሎ እሞን ቢተው ብላቴናውን አለኝ እንጂ እናቱን አለኝ? ባለ ነበርና፡፡
እሞ ብሎ ሕፃነ ባይል
እናቱን አለኝ እንጂ ብላቴናውን አለኝ? ባለ ነበርና ሕፃነ
ወእሞ አለ።
አንድም ሰይጣን የሆነ የሆነ እንደሆነ አመልክቶ ይተዋል
ለመልአክ ግን አካቶ መናገር
ልማድ ነውና ሕፃነ ወእሞ አለ።
ወሀሉ ህየ እስከ አመ እነግረከ ተመለስ ብዬ እስክነግርህ ከዚያ ኑር አለው።
እስመ ሀለዎ ለሄሮድስ ይኅሥሦ ለሕፃን ከመ ይቅትሎ። ሄሮድስ ብላቴናውን ሊገድለው ይሻው ዘንድ አለውና።
******
፲፬፡ ወተንሢኦ ነሥአ ሕፃነ ወእሞ በሌሊት ወሖረ ውስተ ብሔረ ግብፅ።
******
፲፬፡ ተነሥቶ ብላቴናውን እናቱን ይዞ በሌሊት ወደ ግብፅ ሄደ፡፡ ኮብላይ ለልማዱ መንገዱ ሌሊት ነውና።
አንድም ወዲያው እንደ ነገረው ሳያንተላክስ ሄደ ሲል ሖረ በሌሊት አለ፡፡
******
፲፭፡ ወነበረ ህየ እስከ አመ ሞቱ ለሄሮድስ። ሆሴዕ ፲፩፥፩፡፡
******
፲፭፡ ሄሮድስ እስኪሞት ድረስ ፫ት ዓመት ከመንፈቅ በግብፅ ኖረ። ከመ ይትፈጸም ዘተብህለ እም ኀበ እግዚአብሔር
በነቢይ እንዘ ይብል እምግብፅ ጸዋዕክዎ ለወልድየ እግዚአብሔር በነቢይ አድሮ ነቢይ ከእግዚአብሔር ተገልጾለት በነቢዩ ቃል ልጄን
ከግብፅ ጠራሁት ተብሎ የተነገረው ይደርስ ይፈጸም ዘንድ።
(ሐተታ) ይህማ መውጣቱን ያስረዳል እንጂ መውረዱን ያስረዳልን ቢሉ ካልወረደ መውጣትን አለ አንድም እም
ቅሉ ወደ ሲሆን ነው፡፡ ተጸውዑ እምቴዎፍሎስ ጽውዓን እምሰማይ እንዲል ልጄን ወደ ግብፅ ጠራሁት ተብሎ የተነገረው ይደርስ ይፈጸም
ዘንድ ወደ ግብፅ ያደረገው ስለምን ቢሉ ትንቢቱ ምሳሌው ሊደርስ ሊፈጸም፡፡
ትንቢት ናሁ እወዲ እዴየ ውስተ ምድረ ግብፅ ወትከውን አሐቲ ሀገር ምሥዋዖ ለእግዚአብሔር ይላል ደብረ ቊስቋምም
እስክንድርያም ቢሉ ወይወርድ እግዚእነ ውስተ ምድረ ግብጽ እንዘ ይጼዓን ዲበ ደመና ቀሊል፤ እምግብጽ ጸዋዕክዎ ለወልድየ ተብሎ ተነግሯል።
ይህማ የተነገረ ለያዕቆብ አይደለም ቢሉ ለጊዜው ለያዕቆብ ቢሆን ፍጻሜው ለጌታ ነውና፡፡ ነቢየ ያነሥእ ለክሙ እምአኃዊክሙ ያለው
ለኢያሱ ቢሆን ፍጻሜው ለጌታ እንደሆነ።
ምሳሌም አባቶቹ ወደ ግብፅ ተሰደዋል ትንቢቱን አውቆ አናግሯል። ምሳሌውንም እንጂ ባወቀ አስመስሏል ፍጻሜው
እንደምነው ቢሉ ግብፅ ታቀርበዋለችና ይሹታልና ለፍቆሩ ይሳሳሉና። ክህደት በነዚህ ጸንቶ ነበርና። ወደ ጸናበትም መሄድ ልማድ ነው።
አሁን በመዋዕለ ስብከቱ ደዌ ወደ ጸናባቸው ወደ ጌርጌሴኖን ሄደ ብሎ እንዲያመጣው።
አንድም ገዳማተ ግብፅን ለመባረክ ደጋጉ ገዳማት እነሲሐት እነ አስቄጥስ ከዚያ አሉና።
አንድም መልኩን አይተው የሚያምኑ አሉና። ወተበሀላ አዋልደ ሴሐት ንዑ ንርአዮ ለወልደ መንክራት እንዲል፡፡
አንድም ኪዳነ መልከ ጼዴቅን ለመፈጸም ዘመዶቼን ማርልኝ ቢለው ልጄን በሥጋ ሰድጄ እምርልሃለሁ ብሎት ነበርና።
አንድም ሃይማኖት ከሁሉ ሲጠፋ በግብፅ አይጠፋምና፡፡ እስከ ምጽአት ድረስ ወልድ ዋሕድ ስትል ትኖራለችና።
በዚያውስ ላይ መሰደዱ ስለምነው ቢሉ እንዳይሞት፡፡ ጊዜው አልደረሰምና ከዚያ ሳለ ድኖም ቢሆን ምትሐት ነው
ባሉ ነበርና።
አንድም አዳም ከዚሀ ዓለም አፍአ ከምትሆን ከገነት ተሰዶ ነበርና ለዚያ እንደ ካሰ ለማጠየቅ።
አንድም ለሰማዕታት ስደትን ለመባረክ ሰማዕትነት ብቻ በእሳት በስለት አይደለም። አገርንም ጥሎ መሰደድ ስማዕትነት
ነውና።
አንድም ጒየተ ሕፃን አጒየዮ ለዲያብሎስ እንዲል። አጋንንትን ከሰው ልቡና አስወጥቶ ለመስደድ፡፡
******
በእንተ ሚጠት እምነ ግብፅ፡፡
፲፮፡ ወሶበ ርእየ ሄሮድስ ከመ ተሣለቁ ላዕሌሁ ሰብአ ሰገል ተምን ጥቀ።
፲፮፡ ሄሮድስ እንደዘበቱበት በየ ጊዜ ማለት በአንተ በኩል እንመለሳለን ብለው ብሌላ ጎዳና እንደሄዱ በሰማ
ጊዜ ፈጽሞ ተበሳጨ።
******
ይቆየን፡፡
**************
መልካሙ
በየነ
ደብረ
ማርቆስ፤ ኢትዮጵያ
27/06/2011
ዓ.ም
No comments:
Post a Comment