Tuesday, March 19, 2019

ወንጌል ቅዱስ ክፍል 40


 ====================
የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ቅዱስ ወንጌል።
ቅዱስ ማቴዎስ እንደ ጻፈው።
ምዕራፍ ፭።
                  ******
በእንተ ብፁዓን።
፩፡ ወርአዮ ብዙኃነ አሕዛበ ዓርገ ውስተ ደብር ወነበረ።
                  ******
፩፡ ወሶበ ርእየ ይላል ብዙ ሰዎችን ባየ ጊዜ ከተራራ ላይ ወጥቶ ተቀመጠ።
(ሐተታ) ምነው አሕዛብ አላቸው እስራኤል አይደሉም ቢሉ ብዛታቸውን ሲያይ። አንድም ግብረ አሕዛብን ይሠራሉና። በጸያፍ የገባ ሰው ሲበዛ ከመርከብ ከተራራ ሁኖ ማስተማር ልማድ ነው መምር ከፍ ካለ ቦታ ሰማዕያን ዝቅ ካለ ቦታ የሆኑ እንደሆነ ትምህርት ለሰማዕያን ይረዳልና። ወይረድ ከመ ጠል ነቢብየ እንዲል።
አንድም በደብረ ሲና ሕገ ኦሪትን የሠራሁ እኔ ነኝ ሲል።
አንድም ልዑለ ባሕርይ ነኝ ሲል።
አንድም የሠራሁላችሁ ሕግ ልዕልት ናት። እናንተም ሉዓላውያን ናችሁ ሲል።
ወቀርቡ ኀቤሁ አርዳኢሁ።
ደቀ መዛሙርቱ ወደሱ ቀረቡ። የቀረው ግን የራቀውም ርቆ የቀረበውም ቀርቦ ይሰማል እኒህ ግን መደበኞች ናቸውና ትምህርት የሚቀር በኒህ ነውና።
አንድም ለጉባኤው ስፍራ አለውና። ጥንተ ቀራቦች ናቸውና ቀረቡ።
                  ******
፪፡ ወከሠተ አፉሁ፡፡
                  ******
፪፡ ነገር ጀመረ። ወከሠተ አፉሁ ኢዮብ ወረገማ ለዕለት እንተ ባቲ ተወልደ። ወከሠተ አፉሁ ጴጥሮስ ወአኀዘ ይንግሮሙ እምጥንቱ እስከ ተፍጻሜቱ ወከሠተ አፉሁ ፊልጶስ ወአኀዘ ይንግሮሙ በውእቱ መጽሐፍ እንዲል።
ወመሀሮሙ እንዘ ይብል።
እንዲህ ብሎ አስተማራቸው።
(ሐተታ) እስከ አሁን የአምስት ገበያ ሰው ይከተለው ነበር ከእንግዲህ ወዲህ በብፁዓን አዋጅ ይለያቸዋል። ንጉሥ መንግሥቱ እስኪደላደልለት ድረስ ሌባ ወምበዴ ይከተለዋል። መንግሥቱ ግን ከተደላደለ በኋላ ሌባ ወንበዴ ተለይ ብሎ ዓዋድ እንዲነግር፤ በብፁዓን ዓዋጅ ይለያቸዋል።
                  ******
፫፡ ብፁዓን ነዳያን በመንፈስ። ሉቃ ፮፥፭፡፡
                  ******
፫፡ ብፁዓን እለ ያነድዩ ርእሶሙ ይላል። አውቀው ከብዕል ነዳያን ነን የሚሉ ንዑዳን ክቡራን ናቸው፡፡ ብዕል እንጂ የእግዚአብሔር የባሕርይ ገንዘቡ ነው ለኛስ ባሕርይ የሚስማማው ንዴት ነው ብለው ብዕሉም እንደ ኢዮብ እንደ አብርሃም ነው፡፡
አንድም ከጥበብ ነዳያን ነን የሚሉ ንዑዳን ክቡራን ናቸው ጥበብ እንጂ የእግዚአብሔር ገንዘብ ነው። ለኛስ ባሕርይ የሚሰማማው ድንቁርና ነው ብለው ጥበቡም እንደ ሲራክ እንደ ሰሎሞን ነው።
አንድም ከአእምሮ ነዳያን ነን የሚሉ ንዑዳን ክቡራን ናቸው። መኰንነ ተሰሎንቄ አፈ ወርቅን እንደጠየቀው፡፡ ቅዱሳን ከበቁ በኋላ ከአእምሮ ነዳያን ነን ማለታቸው እንደ ምነው አለው። አንተ በሀገርህ እንደምን ትኖራለህ አለው፡፡ ከሁሉ በላይ ነኝ አለው። እልፍ ብለህ በቂሳርያሳ አለው፡፡ የምበልጣቸውም አሉ የሚተካከሉኝም አሉ አለው። እልፍ ብለሀሳ ቊስጥንጥንያ አለው። የሚበልጡኝም አሉ የምተካከላቸውም አሉ አለው። ዝቅ እያለ ሄደ። እልፍ ብለህ በአንፆኪያሳ አለው። ከዚያስ እንዳለሁም እንደ ሌለሁም የሚያውቀኝ የለም አለው። ቅዱሳንም ከአእምሮ ነዳያን ነን ማለታቸው በበላያቸው ያለውን እያዩ ነው ብሎታል።
አንድም በመማር በማስተማር በምናኔ በንስሐ በሃይማኖት ነዳያን ነን የሚሉ ንዑዳን ክቡራን ናቸው፡፡
እስመ ሎሙ ይእቲ መንግሥተ ሰማያት፡፡
መንግሥተ ሰማያት የሳቸው ናትና ማለት መንግሥተ ሰማያትን ይወርሳሉና፡፡
                  ******
፬፡ ብፁዓን እለ ይላህው ይእዜ። መዝ ፴፯፥፲፩፡፡
                  ******
፬፡ ዛሬ የሚያዝኑ የሚያለቅሱ ንዑዳን ክቡራን ናቸው።
(ሐተታ) የሚገባ ኃዘን የማይገባ ኃዘን አለ። የማይገባ ኃዘን እናት አባት ሞተብኝ እኅት ወንድም ዘመድ የለኝ ርስት ጉልት ሄደብኝ ብሎ ማዘን አይገባም። እንዳባት እንደናት ሥላሴ እንደ ወንድም እንደ እህት መላእክት አሉና። እንደ ርስት እንደ ጉልት የማታልፍ ርስት ጉልት መንግሥተ ሰማይ አለችና። የሚገባ ኃዘን የራሱን ኃጢአት አስቦ የባልንጀራውን ኃጢእት አይቶ ግፍዓ ሰማዕታትን ሞተ ወልደ እግዚአብሔርን አስቦ ማዘን ይገባል፡፡
የራስን ኃጢአት እያሰቡ ማዘን እንደ አዳም እንደ ቅዱስ ጴጥሮስ እንደ ዳዊት ነው፡፡ መልካቸው ሳይለወጠጥ ሳይሰቀቁ እንባቸው እንደ ሰን ወሀ ይወርድ ነበር።
የባልንጀራውን ኃጢአት እያሰቡ ማዘን እንደ ሳሙኤል ነው እስከ ማዕዜኑ ትላህዎ ሳሙኤል ለሳኦል እስመ አነ መነንክዎ ወገደፍክዎ። ወሶበ ርእያ ለሀገር በከየ ላዕሌሃ ወሶበ ርእዮ ለዘያገብኦ ተሀውከ በመንፈሱ እንዲል።
ግፍዓ ሰማዕታትን አስቦ ማዘን እንደ አስጢፋኖስ፡፡ ወለእስጢፋኖስሰ ነሥዕዎ ዕደው ጻድቃን ወቀበርዎ ወለሀውዎ ዓቢየ ላሀ እንዲል።
ሞተ ወልደ እግዚአብሔርን አስቦ ማዘን እንደ ዮሐንስ ነው የዕለተ ዓርብ መከራውን እያሰበ ሰባ ዘመን ቊጹረ ገጽ ሁኖ ኑሯል።
አንድም ዛሬ በንስሐ የሚያለቅሱ ንዑዳን ክቡራን ናቸው፡፡
እስመ እሙንቱ ይትፌሥሑ።
የኃዘን አጸፋው ደስታ ነውና ይትፌሥሑ አለ እንጂ መንግሥተ ሰማይን ይወርሳሉና ሲል ነው፡፡
                  ******
፭፡ ብፁዓን የዋሀን፡፡ ኢሳ ፲፩፥፪፡፡
፭፡ ኃዳግያነ በቀል የሆኑ ከየውሃት ጠባይዓዊ የደረሱ ንዑዳን ክቡራን ናቸው።
                  ******
ይቆየን፡፡
**************
መልካሙ በየነ
ደብረ ማርቆስ፤ ኢትዮጵያ
10/07/2011 ዓ.ም

No comments:

Post a Comment