==================
የአበውን ውለታ የአበውን ደም መፍሰስ፤
የአበው የቀደሙት አጥንት መከስከስ፤
******
በባንዲራ ደምቀህ ሽብረቅርቅ ብለህ፤
ዐድዋ ዐድዋ ዐድዋ ትላለህ፤
ሰው ማክበር ተስኖህ ቦታን ታከብራለህ፤
የሰውን ስም ወስደህ ለአፈር ትሰጣለህ፤
******
በርግጥ ተምረሃል ከምርም ሰምተሃል፤
‹‹ስትኖር ኢትዮጵያዊ ስትሞት ኢትዮጵያ ነህ››
ስትባል ከርመሃል፤
******
ታዲያ እንዲህ ከኾነ…..
******
አበው አፈር ሆነው ከአፈር ጋር አንድ ኾነው
ኢትዮጵያ ይባሉ፤
ዐድዋ ዐድዋ ዐድዋ ለምን ይባላሉ?
ታዲያ ድላቸውን ዐድዋ ነው ልለው እንዴት እደፍራለሁ?
የሀገር ድል እንጂ የዐድዋ ድል የለም፤
የኸው ነው እውነታው ብታምኑም ባታምኑም!
የኸው ነው እውነታው ብታምኑም ባታምኑም፡፡
****
ተጽሕፈ እምመልካሙ በየነ አመ እሥራ ወሰኑዩ
ለየካቲት፡፡
ደብረ ማርቆስ ኾኜ የዐድዋ ድል ሲባል ገርሞኝ
ይህንን ጻፍኩ፡፡
የካቲት 22/2011 ዓ.ም
No comments:
Post a Comment