====================
የጌታችን
የኢየሱስ ክርስቶስ ቅዱስ ወንጌል።
ቅዱስ ማቴዎስ እንደ ጻፈው።
ምዕራፍ ፬።
******
በእንተ ቀዳማውያን ሐዋርያት
፲፰፡ ወእንዘ ያንሶሱ መንገለ ባሕረ ገሊላ ርእየ ፪ተ አኃወ።
ማር ፩፥፲፮።
******
፲፰፡ በገሊላ ባሕር ማዶ ሲመላለስ ሁለት ወንድማማቾች አገኘ።
ስምዖንሃ ዘተሰምየ ጴጥሮስ።
ጴጥሮስ የተባለ ስምዖንን፡፡
ወእንድርያስሃ እኅዋሁ
ወንድሙን እንድርያስን።
እንዘ ይወድዩ መርበብቶሙ ውስተ ባሕር፡፡
መረባቸውን ከባሕር ሲጥሉ።
እስመ መሠግራን እሙንቱ ዓሣ ወጋሮች ነበሩና።
******
፲፱፡ ወይቤሎሙ እግዚእ ኢየሱስ
ንዑ ትልዉኒ ድኅሬየ።
******
፲፱፡ ለጊዜው በእግር ተከተሉኝ ፍጻሜው በግብር ምሰሉኝ አላቸው፡፡
ወእሬስየክሙ መሠግራነ ሰብእ ሰውን እንደ ዓሣ ወንጌልን እንደ መረብ ይህን ዓለም እንደ ባሕር አድርጋችሁ እንድታስተምሩ አደርጋችኋለሁ
አላቸው፡፡
******
፳፡ ወበጊዜሃ ኅደጉ መሣግሪሆሙ ወተለውዎ።
******
፳፡ ያን ጊዜ ፈጥነው መርከባቸውን መረባቸውን ትተው ተከተሉት ለጊዜው በእግር ተከተሉት ፍጻሜው በግብር መሰሉት፡፡
******
፳፩፡ ወተዓዲዎ ሕቀ እምህየ ርእየ ካልዓነ ፪ተ አኃወ።
******
፳፩፡ ከዚያ ጥቂት እልፍ ብሎ ሁለት ወንድማማች አገኘ።
ያዕቆብሃ ወልደ ዘብዴዎስ ወዮሐንስሃ እኅዋሁ የዘብዴዎስ ልጅ ያዕቆብን ወንድሙ ዮሐንስን፡፡
ውስተ ሐመር ምስለ ዘብዴዎስ አቡሆሙ።
ከአባታቸው ከዘብዴዎስ ጋራ እንዘ ይሠርዑ ወያስተሣንዩ መሣግሪሆሙ፡፡ መረባቸውን ያደፈውን ሲያጥቡ
የተቆረጠውን ሲቀጥሉ፡፡
ወጸውዖሙ ለጊዜው በእግር ተከተሉኝ ፍጻሜው በግብር
ምሰሉኝ አላቸው።
******
፳፪፡ ወበጊዜሃ ኀደጉ ሐመሮሙ ወዘብዴዎስሃ አባሆሙ ወተለውዎ፡፡
******
፳፪፡ ያን ጊዜ ፈጥነው መረባቸውን መርከባቸውን ዘብዴዎስ አባታቸውን ትተው ተከተሉት፡፡
(ሐተታ) አክብር አባከ ወእመከ ይል የለም ቢሉ። ይህን ቅሉ ካልተማሩ አያውቁትምና። አንድም ከአክብሮተ
አብ ወእም አክብሮተ እግዚአብሔር እንዲበልጥ ለማጠየቅ። አባትን የሚረዳው ልጅ የሚረዳበት ገንዘብ ያለ እንደሆነ ትቶ መሄድ ይገባል።
የሚረዳው ልጅ የሚረዳበት ገንዘብ የሌለው አንደሆነ ትቶ መሄድ አይገባም እሱን ግን ምስለ አሳቡ በማርቆስ ያቀናዋል ገንዘብ ያለው
ነው።
******
በእንተ ቀዳማዊ ስብከቱ ወመንክራቲሁ ለእግዚእ ኢየሱስ።
፳፫፡ ወአንሶሰወ እግዚእ ኢየሱስ ውስተ ኩሉ ገሊላ እንዘ ይሜህር በምኵራባቲሆሙ፡፡
******
፳፫፡ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በምኵራብ ገብቶ ሲያስተምር በገሊላ ሲመላለስ ኖረ።
ወይሰብክ ወንጌለ መንግሥት።
ጌትነቱን የምትናገር ወንጌልን እያስተማረ ኖረ።
(ሐተታ) ወልደ እግዚአብሔር እንደነገሠ ዲያብሎስ እንደተሻረ ሞተ ሥጋ ሞተ ነፍስ እንደጠፋ ትናገራለችና
ወንጌለ መንግሥት ይላታል፡፡
ወይፌውስ ኵሎ ድውያነ ወኵሎ ሕሙማነ ዘውስተ ሕዝብ ለዚህም ምልክት በሕዝቡ ዘንድ ያሉ ድውያንን ሁሉ ይፈውስ
ነበረ።
******
፳፬፡ ወወፅአ ስሙዓተ ነገሩ ውስተ ኵሉ ሶርያ።
******
፳፬፡ የተአምራቱ ዜና በሶርያ በ፬ቱ መዓዝን ተነገረ።
ወአምጽኡ ኀቤሁ ኵሎ ድውያነ ወኵሎ ሕሙማነ ዘለለዚአሁ ሕማሞሙ፡፡
ደዌያቸው ልዩ ልዩ የሚሆን ድውያንን ወደሱ ይዘው መጡ፡፡
ወፅዑራነ ወእለሂ ቦሙ አጋንንት።
የተጨነቁን። አጋንንት ያደሩባቸውን።
ወወርኃውያነ
ሠርቀ ወርኅ እያየ የሚጥላቸውን ጨረቃ እንጂ ባታመልኩ ነው ለማለት። አንድም ምልዓተ ወርኅ ሲሆን ደም ይመላል
ብርድ ብርድ ይላል ደዌ ይቀሰቀሳልና።
ወእለሂ ነገርጋር።
ድልስጣ የሚባል ጋኔን አለ አንድ እግሩን ወደ ላይ አንድ እግሩን ወደ ታች አድርጎ ሲታያቸው ይጥላቸዋልና።
ወመፃጕዓነ።
የጸናባቸውን።
ወአሕየዎሙ፡፡
እነዚህን ሁሉ አዳናቸው።
******
፳፭፡ ወተለውዎ ብዙኃን አሕዛብ እምገሊላ ወእምዓሠርቱ አህጉር ወእምኢየሩሳሌም ወእምይሁዳ ወእማዕዶተ ዮርዳኖስ።
ማር ፫፥፯፪፡፡ ሉቃ ፮፥፲፯።
******
፳፭፡ ከዐሥር አህጉር ከብዙ መንደር ተወጻጽተው አምስት ገበያ ያህል ሰዎች ተከተሉት፤ ላንድ ሽማግሌ አሥር
ልጆች ነበሩት እኒህ እየራሳቸው አንድ አንድ አገር አቅንተው ይኖሩ ነበርና። አንድም ጲላጦስ ለቀረጥ ይመቸኝ ብሎ አንዱን ከተማ
ከዐሥር ከፍሎታል፡፡ ከዚህ ተወጸጽተው ተከትለውታል እነዚህም ስለ አምስት ነገር ይከተሉታል፡፡ አንዱ ገበያ መልኩን እናያለን ብለው፤
አንዱ ገበያ ኅብስት አበርክቶ ያበላናል ብለው። አንዱ ገበያ ትምርቱን እንሰማለን ብለው። አንዱ ገበያ ከደዌያችን ይፈውሰናል ብለው።
አንዱ ገበያ የኦሪትን መፍረሻ የወንጌልን መታነጫ እናያለን ብለው ነው። ለኒህም ትንቢት ተነግሮላቸዋል ተነግሮባቸዋል። መልኩን እናያለን
ላሉት ይሤኒ ላህዩ እምውሉደ አጓለ እመሕያው ተብሎ። ኅብስት አበርክቶ ይመግበናል ላሉት ወኢያኅጥኦሙ እምዘፈቀዱ ተብሎ። ያስተምረናል
ላሉት ጥዑም ለጕርዔየ ነቢብከ ተብሎ። ከደዌያችን ይፈውሰናል ላሉት ነሥአ ደዌነ ወፆረ ሕማመነ ተብሎ። የኦሪትን መፍረሻ የወንጌልን
መታነጫ እናያለን ላሉት ቅንዓት አሀዞሙ ለሕዝብ አብዳን ተብሎ ተነግሮባቸዋል። እኒህንም ባምስት ነገር ይፈውሳቸዋል በሐልዮ በነቢብ
በገሢሥ በዘፈረ ልብስ በወሪቀ ምራቅ ገቢር ከሁሉ ይገባል።
******
በእንተ ብፁዓን።
ምዕራፍ ፭።
፩፡ ወርአዮ ብዙኃነ አሕዛበ ዓርገ ውስተ ደብር ወነበረ።
፩፡ ወሶበ ርእየ ይላል ብዙ ሰዎችን ባየ ጊዜ ከተራራ ላይ ወጥቶ ተቀመጠ።
******
ይቆየን፡፡
**************
መልካሙ
በየነ
ደብረ
ማርቆስ፤ ኢትዮጵያ
09/07/2011
ዓ.ም
No comments:
Post a Comment