Thursday, March 21, 2019

ወንጌል ቅዱስ ክፍል 42


 ====================
የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ቅዱስ ወንጌል።
ቅዱስ ማቴዎስ እንደ ጻፈው።
ምዕራፍ ፭።
                  ******
፰፡ ብፁዓን ንጹሐነ ልብ። መዝ ፳፫፥፬፡፡
                  ******
፰፡ ከንጽሐ ልቡና የደረሱ።
አንድም በንስሐ ከኃጢአት ንጹሐን የሆኑ፡፡
አንድም ከቂም ከበቀል ንጹሐን የሆኑ ንዑዳን ክቡራን ናቸው፡፡
እስመ ዘያነብር ቂመ ውስተ ልቡ ኢውክፍት ጸሎቱ ቅድመ እግዚአብሔር ጸሎቱ ለመስተቀይም ከመ ዘርዕ ዘወድቀ ማዕከለ አስዋክ እንዲል።
እስመ እሙንቱ ይሬእይዎ ለእግዚአብሔር።
ሰውነታቸው ጸርቶላቸው እግዚአብሔርን ያዩታልና፡፡ እስመ በአንጽሖ መንፈስ ርእይዎ ነቢያት ለእግዚአብሔር ወተናጸሩ ገጸ በገጽ እንዲል። እስካሁን ይሬእይዎ አላለ አሁን ይሬእይዎ አለ ምነው ቢሉ በኒህ ማየት የሁሉን መናገር ነው።
                  ******
፱፡ ብፁዓን ገባርያነ ሰላም።
                  ******
፱፡ አብነት እለ ይገብሩ ሰላመ ይላል፡፡ አቀበቱን ወጥተውልቁለቱን ወርደው ሰውን ከሰው ጋራ የሚያስታርቁ ንዑዳን ክቡራን ናቸው። እንደ መልከዴቅ እንደ ሊቀ ሀገር፡፡
የመልከ ጼዴቅ በጳውሎስ ታውቋል፡፡ ሊቀ ሀገር ሦስት ልጆች ነበሩት። አንተ ይኸን ሥራ አንተ ይኸን ሥራ ብሎ አዝዞ ማን ከማን ተጣልቷል እያለ እየዞረ ሲያስታርቅ ይውል ነበር።
አንድም ሰው ሰርቆ ቀምቶ ከፈጣሪው ጋራ የሚጣላ የሚበላው የሚለብሰው እንጂ ቢያጣ ነው ብለው የሚበላውን የሚለብሰውን ሰጥተው ከእግዚአብሔር ጋራ የሚያስታርቁ ባለጠጎች ንዑዳን ክቡራን ናቸው።
አንድም ሰውን በንስሐ ከእግዚአብሔር ጋራ የሚያስታርቁ ቀሳውስት ንዑዳን ክቡራን ናቸው።
እስመ እሙንቱ ውሉደ እግዚአብሔር ይሰመዩ፡፡
የእግዚአብሔር ልጆች ይባላሉና፡ እስከሁን ውሉደ እግዚአብሔር አላለም፡፡ አሁን እንዲህ ማለቱ ስለምን ቢሉ በመሰሉት። ጌታ በመስቀል ተሰቅሎ ወደ መቃብር ወርዶ ሰውን ከእግዚአብሔር እንዳስታረቀ እሳቸውም አቀበቱን ወጥተው ቁልቁለቱን ወርደው በማስታረቃቸው ይመስሉታልና፡፡ በኒህ መምሰል የሁሉንም መምሰል መናገር ነው።
                  ******
ብፁዓን አለ ይሰደዱ በእንተ ጽድቅ። ፩፡ጴጥ ፪፥፳፡፡ ፫፥፲፬፡፡ ፬፥፲፬፡፡
                  ******
፲፡ በመማር በማስተማር በምናኔ በንስሐ በሃይማኖት አገራቸውን ጥለው የሚሰደዱ ንዑዳን ክቡራን ናቸው።
እስመ ሎሙ ይእቲ መንግሥተ ሰማያት፡፡
መንግሥተ ሰማያትን ይወርሳሉና። በመጀመሪያ  ተናግሯት ውስጥ ለውስጥ ሲናገራት መጥቶ ነበርና በስምንተኛው አነሣት፡፡ በመጀመሪያ ማንሣቱ ለአዳም እንደ ተሰጠች ለማጠየቅ በስምንተኛው ማንሣቱ በስምንተኛው ሽህ ለሁሉ እንድትሰጥ ለማጠየቅ።
                  ******
፲፩፡ ብፁዓን አንትሙ ሶበ ይሰድዱክሙ።
                  ******
፲፩፡ ከሀገራችሁ አስወጥተው ቢሰዷችሁ ንዑዳን ክቡራን ናችሁ፡፡
ወይዘነጕጉክሙ።
ዓብዳን ዝንጉዓን ጊጉያን ርጉማን ስሑታን ቢሏችሁ።
ወይነቡ ኵሎ እኩየ ላዕሌክሙ እንዘ ይሔስው በእንቲአየ።
በኔ ስም ስላመናችሁ በኔ ስም ስለተጠራችሁ በኔ ስም ስላስተማራችሁ በሐሰት ክፉውን ነገር ቢናገሩባችሁ።
                  ******
፲፪፡ ተፈሥሑ ወተኀሠዩ።
                  ******
፲፪፡ ፈጽሞ ደስ ይበላችሁ።
እስመ ብዙኀ እሤትክሙ በሰማያት።
ዋጋችሁ በኔ ዘንድ ፍጹም ነውናአሥሩ ቃላት አነፃጽሮ አሥሩን ብፁዓን ተናገረ፡፡ አሥረኛውን በዮሐንስ ያመጣዋል። ሙሴ ዘጠኙን ቃላት በኦሪት ዘፀአት ተናግሮ አሥረኛውን በኦሪት ዘሌዋውያን እንዳመጣው።
እስመ ከማሁ ሰደድዎሙ ለነቢያት እለ እምቅድሜክሙ።
ከናንተ አስቀድሞ የነበሩ ነቢያትን ከሀገራቸው አስወጥተው ይሰዷቸው ነበርና፡፡ ይሰድዱክሙ ላለው።
አንድም መከራስ እንቀበል ብንል ማን አብነት ይሆነናል ትሉኝ እንደሆነ ከናንተ አስቀድሞ የነበሩ ነቢያትንም አንጂ ነቢያትንም እኮን ከሀገራቸው  አስወጥተው ይሰዷቸው ነበር። እኒያ አብነት ይሁኑዋችሁ።
                  ******
 በእንተ ሐዲስ ኪዳን።
ተአርዮታ ምስለ ብሊት።
፲፫፡ አንትሙ ውእቱ ፄዉ ለምድር፡፡ ማር ፱፥፵፱፡፡ ሉቃ ፲፬፥፳፬።
፲፫፡ በዘያውም ላይ የሰው አብነት እናንተ ናችሁ።
                  ******
ይቆየን፡፡
**************
መልካሙ በየነ
ደብረ ማርቆስ፤ ኢትዮጵያ
12/07/2011 ዓ.ም

No comments:

Post a Comment