====================
የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ቅዱስ ወንጌል።
ቅዱስ ማቴዎስ እንደ ጻፈው።
ምዕራፍ ፬።
**
፲፮፡ ሕዝብ ዘይነብር ውስተ ጽልመት ርእየ ብርሃነ ዓቢየ።
**
**
፲፮፡ በጨለማ ላሉ ሕዝብ ታላቅ ብርሃን ወጣላቸው። ወለእለሂ ይነብሩ ውስተ ጽልመት ወጽላሎተ ሞት ብርሃን ሠረቀ ሎሙ በጨለማ በሞት ጥላ ለሚኖሩ ብርሃን ወጣላቸው ብሎ ኢሳይያስ የተናገረው ይደርስ ይፈጸም ዘንድ በቅፍርናሆም ኖረ።
አንድም በድንቁርና በቀቢጸ ተስፋ ለነበሩ ሰዎች ዕውቀት ተሰጣቸው፤ አንድ ገጽ በማለት ሞትን በመምሰል ሞት ባመጣው ምስል ለሚኖሩ ሰዎች ክርስቶስ ተወለደላቸው ወንጌል ተጻፈላቸው።
አንድም በሞተ ሥጋ በሞተ ነፍሰ ለነበሩ ልጅነት ተሰጣቸው። በኃጢአት በክህደት ለነበሩ ሃይማኖት ተገለጸላቸው።
(ሐተታ) ኃጢአትን ጽልመት ክህደትን ጽላሎተ ሞት አለው። በጨለማ ላይ የዛፍ የገደል ጥላ የተጨመረ እንደሆነ ጨለማው እንዲጠና በኃጢአትም ላይ ክህደት የተጨመረ እንደ ሆነ ፍዳው ይጸናልና።
**
፲፯፡ ወእምአሜሃ አኀዘ እግዚእ ኢየሱስ ይስብክ ወይብል ነስሑ እስመ ቀርበት መንግሥተ ሰማያት። ማር ፩፥፲፬።
**
፲፯፡ ዮሐንስ ከተጋዘበት ቀን ጀምሮ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ደጊቱ በልጅነት ልጅነት በሃይማኖት ልትሰጥ ቀርባለችና እመኑ እያለ ያስተምር ጀመረ። ዮሐንስ ከተጋዘ በኋላ ማስተማሩ ስለምን ቢሉ መምህር ሳለ በመምህር ላይ እናስተምራለን አትበሉ ለማለት።
አንድም መምህሩ አንድ ዮሐንስ ነበረ ያውም ተመተረ እንዳይሉ ትምህርቱንም አልለወጠውም የስንቱን ይሰሟል እንዳይሉ።
አንድም ዮሐንስ ቀርበት መንግሥተ ሰማያት ብሎ ያስተማረልኝ እኔ ነኝ ሲል ነው። ነያ ይሰምያ መንግሥተ ሰማያት ለአስተርእዮቱ ማዕከለ ፍቁራኒሁ እንዲል።
**
በእንተ ቀዳማውያን ሐዋርያት
፲፰፡ ወእንዘ ያንሶሱ መንገለ ባሕረ ገሊላ ርእየ ፪ተ አኃወ። ማር ፩፥፲፮።
፲፰፡ በገሊላ ባሕር ማዶ ሲመላለስ ሁለት ወንድማማቾች አገኘ።
**
ይቆየን፡፡
**********
መልካሙ በየነ
ደብረ ማርቆስ፤ ኢትዮጵያ
08/07/2011 ዓ.ም
No comments:
Post a Comment