Thursday, March 7, 2019

ወንጌል ቅዱስ ክፍል 28


====================
የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ቅዱስ ወንጌል።
ቅዱስ ማቴዎስ እንደ ጻፈው ።
ምዕራፍ ፪።
             ******
በእንተ ሚጠት እምነ ግብፅ፡፡
፲፮፡ ወሶበ ርእየ ሄሮድስ ከመ ተሣለቁ ላዕሌሁ ሰብአ ሰገል ተምን ጥቀ።
                  ******

፲፮፡ ሄሮድስ እንደዘበቱበት ባየ ጊዜ ማለት በአንተ በኩል እንመለሳለን ብለው በሌላ ጎዳና እንደሄዱ በሰማ ጊዜ ፈጽሞ ተበሳጨ። በማን ይበሳጫል ቢሉ ብስጩ ለልማዱ በአልጋው በመከዳው በቤተ ሰቡ የጨለማ ገልማጭ እንዲሉ። -
ወአዘዘ ሐራሁ ወፈነወ ይቅትሉ ኵሎ ሕፃናተ በቤተ ልሔም ወዘኵሉ አድያሚሃ። በቤተ ልሔም በአውራጃዋ ያሉ ሕፃናትን ሁሉ ግደሉ ብሎ አዝዞ ሰደደ። ዘ፪ኤ ዓመት፤ ወዘይንዕስሂ እምኔሁ ዓመት ከመንፈቅ ዓመት የሆነውንም፡፡
በከመ ሐሳበ መዋዕል ዘተጠየቀ እምኀበ ሰብአ ሰገል፤ ከሰብአ ሰገል ጠይቆ በተረዳው ዘመን ልክ፡፡
                  ******
፲፯፡ አሜሃ ተፈጸመ  ዘተብሀለ በ ኤርምያስ ነቢይ እንዘ ይብል ቃል ተስምዓ በራማ፡፡
                  ******
፲፯፡ ያን ጊዜ ኤርምያስ ቃል በራማ ተሰማ ብሎ የተናገረው ትንቢት ደረሰ ተፈጸመ ይደርስ ይፈጸም ዘንድ አዘዘ፤ ራማ በቁሙ ሰማይ፡፡ አንድም ከፍ ባለ ቦታ፡፡ አንድም በመላእክት ዘንድ፡፡ አንድም በእግዚአብሔር ዘንድ፡፡
ብካይ፤ የልጆቻቸው ከእናቶቻቸው ሲለይዋቸው፣
ወሰቆቃው፤ የናቶቻቸው፡
ወገዓርየልጆቹ ጠምዘው ሲያርዷቸው፡፡ ወሕማም ብዙኅ ይላል ዘጠኝ ወር ከአምስት ቀን የፀነሰ ማሕፀን አይችልምና፡፡
                  ******
፲፰፡ ራሄል እንዘ ትበኪ በእንተ ውሉዳ፡፡ ኤር ፴፩፥፲፭፡፡
                  ******
፲፰፡ ራሄል ለልጆችዋ ስታለቅስ ተሰማ ያለው ይደርስ ይፈጸም ዘንድ አዘዘ። አንድም ደረሰ ተፈጸመ፡፡
(ሐተታ) ልያን አላነሣ ራሄል አለ ምነው ቢሉ የልያ ዕዳዋ ነው ጌታ ከሷ ወገን ተወልዷልና፡፡ የራሄል ግን ያለዕዳዋ ነው ጌታ ከሷ ወገን አይወለድምናንድም የልያ በርኅቀተ ሀገር በብዛት ድነውላታል የራሄል ግን በማነስ በቅርብ አልቀውባታልና።
አንድም በራሄል ልያን መናገር ነው።
አንድም እናታችን ራሄል ኑራልን መከራችነን አይታ አልቅሳልን ብለው ስላለቀሱ፡፡
አንድም እንድናለን መስሏቸው ከመቃብረ ራሄል ገብተዋል ከዚያ እየገቡ ፈጅተዋቸዋልና።
አንድም በራሄል ሁሉን መናገር ነው፡፡ ይህማ እከፍሎ ውስተ ያዕቆብ ወእዘርዎ ውስተ እስራኤል እንዲል፤ ሁሉን በሚያገናኝ በያዕቆብ ባልተናገረውም ነበር ቢሉ ወንድ ልጅ ለፈረስ ሴት ልጅ ለበርኖስ ከደረሱ በኋላ የሞቱ እንደሆነ ኃዘን በአባት ይጸናል በሕፃንነት የሞቱ እንደሆነ ግን ኃዘን በእናት ይጸናልና በሚጸናው ተናገረ፡፡
አንድም ግፍ ለግፍ ሲያነጻጽር የቀደመችቱ ራሄል የምትባል ሴት ባሏ ሮቤልም ስምዖንም ይባላል ባሏ ሙቶ በባሏ ስፍራ ኖራ እርገጭ ብለዋት ስትረግጥ መንታ ፀንሳ ኑራ ወጥተው ወጥተው ወደቁ ደንግጣ ቆመች የሰው ሥጋ ያጸናዋል እንጂ ምን ይለዋል እርገጭ አሏት፡፡ ኢሀሎኑ በዝ ሰማይ አምላከ እስራኤል ብላ እንባዋን በእጁዋ ተቀብላ ወደ ላይ ረጭተዋለች፡፡ ሰማዕኩ ገዓሮሙ ለሕዝብየ ወወረድኩ ከመ አድኅኖሙ ያሰኘው ይህ ነው።
አንድም ራሄል መንግሥተ ሰማይ የሚገባባት አጥታ ታዝናለች ታለቅሳለች።
ወዓበየት ተናዝዞ ወነጊረ ላሀ ራሄል ልቅሶ መተውን መጽናናትን እምቢ አለች። ግፉሳዝናልና የፆር ሞት ነውና ኀዘን በየደጁ ሁኑአልና።
እስመ ኢኮንዋ ውሉዳ ውሉደ ልጆቹአ ልጆች አልሆኑአትምና ሙተዋልና ማለት ነው። አንድም እስመ ኢኮኑ ውሉደ። ልጆቹአ አይደሉምና የተውሶ ናቸውና።
ወኢሀለዉ ። በሕይወተ ሥጋም የሉምና።
(ሐተታ) እነዚህንስ እንደምን አድርጎ ይሰበስባቸዋል ቢሉ ቄሣር ሕፃናትን ሰብስበህ ልብስ ምግብ እየሰጠህማር በወተት አሳድገህ ለእናት ለአባታቸው ርስትልት እየሰጠህ ጭፍራ ስራልኝ ብሎኛል ብሎ አዋጅ ነገረ፡፡ ያላት ልጁዋን የሌላት ልብስ ምግብ ልቀበልበት ብላ ተዋሰች ይዛ ሂዳለች እንዲሀ አድርጎ ሰብስቦ ፈጅቷቸዋል፡፡ ይህስ ዕዳው በማን ይሆናል ቢሉ በሱ፡፡ በዳዊት ምክንያት ፫፻፹፭ ሌዋውያን ቢያልቁ ፩፡ሳሙ ፳፪፥፲፰፡፡ በጴጥሮስ ምክንያት ፲፮ት ሰገራት ቢያልቁ ግብረ፡ሐዋ ፲፪፡-፲፱፡፡ ዕዳው በሳኦል በሄሮድስ ሆነ እንጂ በዳዊት በጴጥሮስ ሆነን እሊያስ ባያውቁ ነው እሱማ እያወቀ ቢሉ ያውቃልማ ካሉ ሁሉንም ያውቃል መጠቀማቸውንም ያውቃል። ለኒህስ ክብር አላቸው ቢሉ የላቸውም ይሏል። ይህማ እንዳይሆን ስንክሳር ተጽፎላቸው ታቦት ተቀርጾላቸው አብያተ ክርቲያናት ታንጾላቸው የለም ቢሉ ሳያውቁ በሠሩት ሥራ መጠቀም እንደሌለ ለማጠየቅ ነው እንጂ ክብር አላቸው፡፡
                  ******
፲፱፡ ወመዊቶ ሄሮድስ ናሁ መልአከ እግዚአብሕር አስተርአየ በሕልም ለዮሴፍ በብሔረ ግብፅ፡፡
                  ******
፲፱፡ ሄሮድስ ከሞተ በኋላ በግብፅ ሳለ ከእግዚአብሔር የታዘዘ መልአክ ለዮሴፍ በህልም ነገረው፡፡
                  ******
፳፡ እንዘ ይብል ተንሥአ ንሣእ  ሕፃነ ወእሞ ወሑር ውስተ ምድረ እስራኤል።
                  ******
፳፡ ተነሥተህ ብላቴናውን እናቱን ይዘህ ወደ ምድረ እስራኤል ተመለስ ብሎ ነገረው።
እስመ ሞቱ እለ የኃሥሥዋ ለነፍሰ ዝ ሕፃን።
የዚህን ብላቴና ሰውነት ለጥፋት የሚሹዋት ሰዎች ሙተዋልና። ኢትቀትል ነፍሰ እንዲል።
አንድም ነፍስ እንደነሣ ለማጠየቅ ለነፍሰ ዝ ሕፃን አለ።
(ሐተታ) ምነው የሞተ አንድ ሄሮድስ አይደለም ሞቱ ብሎ አበዛ ቢሉ። የምክር ጋናቸው እሱ ነው እሱ ከሞተ ያነሡታልን ብሎ።
አንድም በሦስት ዓመት ከመንፈቅ ስንኳን በዓላውያን ከተማ በምዕመናን ከተማስ እንኳ ብዙ ሰዎች ይሞታሉና። እሱንም የመሰሉ ሰዎች ሙተዋልና ሞቱ አለ።
                  ****** .
፳፩፡ ወተንሢኦ ነሥአ ሕፃነ ወእሞ ወቦዓ ውስተ ምድረ እስራኤል፡፡
                  ******
፳፩፡ ተነሥቶ ብላቴናውን እናቱን ይዞ ወደ ምድረ እስራኤል ተመለሰ።
                  ******
፳፪፡ ወሰሚኦ ከመ አርኬላዖስ ነግሠ ለይሁዳ ህየንተ አቡሁ ሄሮድስ ፈርሃ ሐዊረ ህየ።
፳፪፡ በአባቱ በሄሮድስ ፈንታ ይሁዳን ለመግዛት አርኬላኦስ እንደ ነገሠ ሰምቶ ወደ ኢየሩሳሌም መሄድ ፈራ።
                  ******
(ሐተታ)
                  ******
ይቆየን፡፡
**************
መልካሙ በየነ
ደብረ ማርቆስ፤ ኢትዮጵያ
28/06/2011 ዓ.ም

No comments:

Post a Comment