***ወንጌል
ቅዱስ ክፍል 45***
====================
የጌታችን
የኢየሱስ ክርስቶስ ቅዱስ ወንጌል።
ቅዱስ ማቴዎስ እንደ ጻፈው።
ምዕራፍ ፭።
******
፳፩፡ ሰማዕክሙ ዘተብሀለ ለቀደምትክሙ ኢትቅትል ነፍሰ።
******
፳፩፡ ለቀደሙ ሰዎች ነፍስ አትግደል የተባለውን፡፡ ዘፀ ፳፥፲፫፡፡
ዘከመ ተብሀለ ሎሙ
እንደተባለላቸው፡፡
ዘይቤልዎሙ
ያሏቸውን፡፡
ዘከመ ይቤልዎሙ
እንዳሏቸው ሰምታችኋል።
ወዘሰ ቀተለ ረስሐ ውእቱ ለኵነኔ።
ነፍስ የገይለ ኃጥእ ተብሎ ይፈረድበታል የተባለውን ሰምታችኋል።
******
፳፪፡ ወአንሰ እብለክሙ ኵሉ ዘያምዕዕ አኅዋሁ በከንቱ ረስሐ ውእቱ ለኵነኔ።
******
፳፪፡ እኔ ግን ወንድሙን በከንቱ ያሳዘነ ሁሉ ኃጥእ ተብሎ ይፈረድበታል ብዬ እነግራችኋለሁ።
(ሐተታ) ኦሪትንስ ወንጌልንስ የሠራ እሱ አይደለም?
እኔ ግን ማለቱ ስለምን ቢሉ ጌታ ሁን እንዳሻህ ሁን እንዲሉ ይህስ በጌታ የለበትም
ብሎ ኦሪትን በሙሴ በኢያሱ
አድሮ ሰርቷታል ወንጌልን ግን እሱ ሰው ሁኖ ሠርቷታልና።
አንድም ለቀደሙ ሰዎች እንዲህ ብዬ ነበር ዛሬ ግን እንዲህ አልኩ።
አንድም አሜሃኒ ዮምኒ ያን ጊዜ እንዲህ ብዬ ነበር ዛሬም እንዲህ አልኩ። በከንቱ አለ ቦ መዓት ዘበርትዕ እንዲል። የሚገባ
ቊጣ አለና ሕፃናት ያልተማሩትን እንዲማሩ የተማሩትን እንዳይገድፉ፡፡ መናፍቃን እንዳይሠለጥኑ ሃይማኖት እንዳይጠፋ ክህደት እንዳይሰፋ፡፡
አንድም በከንቱ ያለውን መፍቀርያነ መዓት የጨመሩት ነው፡፡
በሐጌ መጽሐፍ ፪፥፰ ዝወርቅ ወዝ ብሩር ዘዚአየ ባለው መፍቀርያነ ብሩር ወለዘፈቀድኩ እሁቦ ብለው እንደጨመሩበት፡፡
ወዘሂ ይቤሎ ኅሡር ዘፀርቅ ረስሐ።
ወንድሙን ጨርቅ ለባሽ አባተ ታናሽ ብሎ የሰደበ በደለ።
ወይትኴነን በዓውድ።
በአደባባይ ይፈረድበታል።
ወዘሂ ይቤሎ ለእኁሁ ዓብድ ረስሐ ውእቱ።
ወንድሙን ድዳ ደንቆሮ ያለው እሱ በደለ።
ወይትኴነን በእሳተ ገሃነም።
በእሳተ ገሃነም ይፈረድበታል፡፡
(ሐተታ) ወንድሙን ጨርቅ ለባሽ አባተ ታናሽ ቢለው ባደባባይ። ድዳ ደንቆሮ ቢለው በገሃነም ይፈረድበታል አለ ምነው ቢሉ፡፡ ከተፈጥሮተ ሥጋ ተፈጥሮተ ነፍስ እንዲበልጥ ከስድቡም ስድብ ይበልጣልና፡፡
ከፍዳውም ፍዳውን አበለጠ።
አንድም በዓውድ ገሃነም በገሃነም ዓውድ ያለ ነው። በአክብርዎ ፍርህዎ በፍርህዎ
አክብርዎ እንዳለ። ይህንም ሊቁ ዘሰ ጸረፈ ላዕለ ሰብእ ጸረፈኬ ላዕለ እግዚአብሔር ብሎ ወስዶታል። መጽሐፉን አይቶ መንቀፍ ጸሐፊውን
ሕንፃውን አይቶ መንቀፍ ሐናጺውን መንቀፍ እንደሆነ፡፡ ፍጥረቱንም አይቶ መንቀፍ እግዚአብሔርን መንቀፍ ነውና።
******
፳፫፡ ወእምከመኬ ታበውዕ መባዓከ ውስተ ምሥዋዕ ወበህየ ተዘከርከ
ከመ ቦ እኁከ ዘተኀየስከ።
******
፳፫፡ መባህን ለቤተ እግዚአብሔር በምትሰጥበት ጊዜ አንተ ወንድምህን
የነቀፍህበት። ዘተኃየሰከ እሱ አንተን የነቀፈበት ነገር እንዳለ ብታስብ።
******
፳፬፡ ኅድግ ህየ መባዓከ ቅድመ ምሥዋዕ።
******
፳፬፡ መባውን ከደጀ ሰላም አኑረህ ወሑር ቅድመ ተኳነን ምስለ
እኁከ።
አስቀድመህ ከወንደምህ ተወቃቅሰህ ታረቅ።
ወእምዝ ገቢዓከ አብዕ መባዓከ፡፡
ከዚህ በኋላ ተመልሰህ መባህን ስጥ። ሰጥቶ ቢሄድ መባው እንኳን
የገባልኝ አንጂ ብሎ ዕርቁ በቀረ ነበርና። ይዞ ወደ ቤቱ ተመልሶ ቢሆን ዕርቁም መባውም በቀረ ነበርና ልብ እንዲቀረው ከእዳሪ አኑሯለሁ
ብሎ ፈጥኖ ታርቆ እንዲመለስ እንዲህ አለ፡፡
አንድም ወእምከመኬ ብለህ መልስ፡፡
ጸሎት በምትጸልይበት ጊዜ የነቀፈህ ወንድምህ የነቀፍከው ወንድምህ እንዳለ ብታስብ ጸሎቱን ትተህ ሂድ፡፡ አስቀድመህ
ከወንድምህ ተወቃቅሰህ ታረቅ ከዚህ በኋላ ተመልሰህ ጸሎትህን ጸልይ። በቂም በበቀል ሁኖ የጸለዩት አይረባም
አይጠቅምምና፡፡ እስመ ዘያነብር ቂመ ውስተ ልቡ ኢውክፍት
ጸሎቱ ቅድመ እግዚአብሔር
ጸሎቱ ለመስተቀይም ከመ ዘርእ ዘወድቀ ማእከለ አስዋክ
አንዲል።
******
፳፭፡ ኩን ጠቢበ ለዕድውከ ፍጡነ እንዘ ሀሎከ ምስሌሁ ውስተ ፍኖት፡፡
******
፳፭፡ በመንገድ ከሱ ጋራ ሳለህ በባላጋራህ ፈጥነህ ዕወቅበት ተዓረቅ በፍኖት ብሎ በሉቃስ ያቀናዋል፡፡
ከመ ኢይመጡከ ዕድውከ ለመኰንን፡፡
ባላጋራህ ለዳኛ አሳልፎ እንዳይሰጥህ።
ወመኰንን ይሜጥወከ ለወዓሊሁ።
ዳኛውም አሳልፎ ለሎሌው ይሰጥሃል።
ወወአሊሁ ይሞቅሐከ።
ሎሌውም ያግዝሃል።
******
፳፮፡ አማን እብለከ ከመ ኢትወፅእ እምህየ እስከ ሶበ ትሤልጥ
ደኃሪተ ገመስ ዘላዕሌከ።
******
፳፮፡ ሌላው ገንዘብህስ ይቅርና ሰንኪቶ የምትባል ቀለበትህን እስከመስጠት ደርሰህ።
አንድም ገመሰ ደኃሪት ይላል። የታናሽ ጣትህን ቀለበት እስከ መስጠት
ደርሰህ ከግዞት ቤት አትወጣም ብዬ እንዳትወጣ በእውነት
እነግርሃለሁ።
አንድም ኩን ጠቢበ ብለህ መልስ፡፡
በዚህ ዓለም ሳለህ በባለጋራህ በዲያብሎስ ዕወቅበት። ይህን ዓለም ፍኖት አለው፡፡ በመንገድ አንዱ ሲያልፍ አንዱ ሲተርፍ እንደሆነ፡፡
በዚህም ዓለም አንድ
ሲያልፍ አንዱ ሲተርፍ ነውና።
በላጋራሀ ዲያብሎስ ለጌታ አሳልፎ እንዳይሰጥህ። ጌታም
አሳልፎ ለዲያብሎስ ይሰጥሃል።
ዲያብሎስ ያግዝሃል። ወዓሊሁ
አለ የግድ ነው የፈቃድ አይደለም። ሥራ ሠርተህ ያገኘኸው ጸጋ ክብር ይቅርና በዐርባ
ቀን ያገኘኸውን ልጅነት እስከ ማጣት ደርሰህ ከገሃነም አትወጣም ብዬ እንዳትወጣ
በእውነት እነግርሃለሁ።
አንድም በዚህ ዓለም ሳለህ በባለጋራህ በፈቃደ ሥጋህ ፈጥነህ ዕወቅበት። ባለጋራህ ፈቃደ ሥጋ አስፈርዶ ለጌታ እንዳይሰጥህ። ጌታም አሳልፎ ለዲያብሎስ ይሰጥሃል።
ዲያብሎስያግዝሃል። አማን እብለከ ። በነቢብ በገቢር በሠራኸው ኃጢአት ቀርቶ በሐልዮ በሠራኸው ኃጢአት ተፈርዶብህ ከገሃነመ እሳት አትወጣም ብዬ እንዳትወጣ በእውነት እነግርሃለሁ። ከሐልዮ ኃጢአት የሚነጻ አለን ቢሉ የሚያሲዝ
ሐልዮ የማያሲዝ ሐልዮ አለ።
የሚያሲዝ ሐልዮ እሰርቃለሁ እቀማለሁ ብሎ ሂዶ ሰው ነቅቶበት ውሻ ጩኾበት
አጥር ጠንቶበት ቢመለስ ያሲዛል። የማያሲዝ ሐልዮ እሰርቃለሁ እቀማለሁ ብሎ ይሄዳል ከመንገድ ሲደርስ ፈጣሪዬ ቢፈርድብኝሳ ብሎ የተመለሰ እንደሆነ ይህ አያሲዝም።
አንድም ሁሉም ያሲዛል፡፡ ለዚህ ቅሉ ጥቂት ቀኖና ያሻዋል በሰይጣን ፆር ተወግቷልና።
ሁለት ሰዎች ከሰልፍ
ይገባሉ ሁለቱ ሁሉ ተወግተው ይመለሳሉ አንዱ ይሞታል
አንዱ ይድናል ከዳነው ላይ እትራት ይጠፋልን።
ይህም በአቡነ እንጦንስ ታውቋል በሚሞቱበት ጊዜ መላእክተ ጽልመት ቀረቡ መላእክተ ብርሃን መጥተው ከዚህ ሰው ምን አላችሁ አሏቸው።
ምነው ያስ የሐልዮው አሏቸው
ከቆብ በኋላ ነው ከቆብ በፊት አሏላቸው፡፡
ከቆብ በፊት ነው እንጂ ከቆብ
በኋላማ በዕንጦንስ ምን ተገኝቶበት አሉ።
ያማ በቆብ ታርቆበት የለም ወግዱ ብለዋቸዋል።
******
፳፯፡ ሰማዕክሙ ዘተብሀለ ለቀደምትክሙ ኢትዘምው።
ዘፀ ፳፥፲፬።
፳፯፡ ለቀደሙ ሰዎች አትሰስኑ የተባለውን ሰምታችኋል።
******
ይቆየን፡፡
**************
መልካሙ
በየነ
ደብረ
ማርቆስ፤ ኢትዮጵያ
17/07/2011
ዓ.ም
No comments:
Post a Comment