※※※※※※※※³ ※※※※※※※※
© መልካሙ በየነ
መስከረም ፮/፳፻፲፩ ዓ.ም
ደብረ ማርቆስ፣ ኢትዮጵያ
※※※※※※※※³ ※※※※※※※※
ቤተክርስቲያንን እንዳንዳፈር እግዚአብሔርንም እንዳናስቀይም አድርጉ የተባልነውን በማድረግ፤ አታድርጉ የተባልነውንም ባለማድረግ ሥርዓተ ቤተክርስቲያንን ልንጠብቅ ያስፈልጋል። አንድን ሥራ ለመሥራት ከመነሣት በፊት ስለሥራው ሥርዓት ማወቅ ይኖርብናል። ከመጾም፣ ከመጸለይ፣ ከመስገድ፣ ከመመጽወት፣ ከማስቀደስ፣ ኪዳን ከማስደረስ ወዘተ በፊት ሥርዓቱን ማወቅ ግድ ይለናል። የደከምነው ድካም በእግዚአብሔር ዘንድ የተወደደ ኾኖ ፍሬ አፍርቶ ከፍሬው እንበላ ዘንድ ሥርዓቱን ማወቅ ግድ ነው። ይህንንም በተመለከተ የሥርዓት መጻሕፍትን መመልከት አባቶችን መጠየቅ ያስፈልጋል። ስምንቱ የሕግና የሥርዓት መጻሕፍት የሚባሉት ሥርዓተ ጽዮን፣ ትእዛዝ፣ ግጽው፣ አብጥሊስ፣ መጽሐፈ ኪዳን አንድ እና ኹለት፣ ቀሌምንጦስ፣ ዲድስቅልያ ናቸው። ከእነዚህ የሥርዓት መጻሕፍት ሕግ እና ትእዛዝ ልንወጣ አይገባንም። በዚህ ጊዜ የምናየው ነገር እጅጉን የተቀየረ ነገር ነው። ሰው ከማስቀደስ ይልቅ ፀበሉ ሊታደል ሲል መምጣት ይመርጣል። ሲጀመር የቅዳሴ ፀበል እኮ ላልቆረበ ሰው አይሰጥም፤ ያልቆረበ ሰውም አይጠጣውም ነበር። ዛሬ ዛሬ ግን ከቅዳሴው ይልቅ ፀበሉን ፍለጋ ነው ብዙዎቻችን የምንሄደው። ልጆቻችንን ለማቁረብ (እኛማ መቼም ትተነዋል) ስናስብ በራሱ ቅዳሴ ከመዠመሩ በፊት ቤተክርስቲያን ገብተን በምቅዋማችን ጸንተን የምንገኝ ስንቶቻችን ነን። ቅዳሴው ሲያልቅ ዘው ብለን ገብተን እኮ ነው እንደ ምድራዊ መዓድ የምንሳተፈው። ይህ አካሄድ በእውነቱ ለቅስፈት እንጂ ለበረከት፣ ለድኅነት አይኾነንምና በጊዜ ልናርመው ይገባል። ቅዳሴውን ሳናስቀድስ ድርገት ሊወርዱ ሲሉ እየሮጥን ገብተን የምናስቆርብ ብዙዎች ነን። ይህ በእውነት ድፍረት ካልኾነ በቀር ምን ልንለው እንችላለን። እምነ በሀ፣ መስቀል አብርሃ፣ ኩሉ ዘገብራ ከመባሉ አስቀድሞ ቤተክርስቲያን ውስጥ ገብተን በየምቅዋማችን ቤተክርስቲያን እንድንቆምበት በሰጠችን ቦታ ላይ ቅድስት ላይ መቆም ይኖርብናል። ለቆራቢ ሰው መቆሚያው ቅድስት የተሰኘው የቤተክርስቲያን ክፍል ነውና በዚያ መቆም አለብን። ቅዳሴውን ከመዠመሪያው ጀምሮ ቆሞ ያስቀደሰ ሰው ሳይቆርብ አይሄድም፤ ያንጊዜ ባይችል እንኳ በሌላ ቀን ለመቁረብ ይወስናል። ምክንያቱም ገና ቅዳሴው እንደተጀመረ ከትንሣኤ እስከ በዓለ ሃምሳ ካልኾነ በቀር ራሱነአስቀዳሹ «ሃሌ ሉያ» ብሎ በሚጀምረው የቅዳሴው የመዠመሪያ ክፍል ላይ በሚማርክ ዜማ በራሱ ላይ እንዲፈርድ አድርጋ ቤተክርስቲያን ሥርዓት ሠርታለታለችና። ምእመኑ በራሱ ላይ የሚፈርደው የቅዳሴው ቃል እንዲህ ይላል፡-

«ሃሌ ሉያ እመቦ ብእሲ እምእመናን ዘቦአ ቤተ ክርስቲያን በጊዜ ቅዳሴ ወኢሰምዐ
መጻሕፍተ ቅዱሳተ ወኢተአገሠ እስከ ይፌጽሙ ጸሎተ ቅዳሴ ወኢተመጠወ እምቊርባን ይሰደድ እምቤተ ክርስቲያን። እስመ አማሰነ ሕገ እግዚአብሔር፤
ወአስተሐቀረ ቁመተ ቅድመ ንጉሥ ሰማያዊ ንጉሠ ሥጋ ወመንፈስ ከመዝ መሐሩነ ሐዋርያት በአብጥሊሶሙ - ሃሌ ሉያ በቅዳሴ ጊዜ ከምእመናን
ወገን ወደ ቤተ ክርስቲያን የገባ ሰው ቢኖር ቅዱሳት መጻሕፍትን ሰምቶ የቅዳሴውን ጸሎት እስኪጨርሱ ባይታገሥ፤ ከቊርባንም ባይቀበል
ከቤተ ክርስቲያን ይለይ። የእግዚአብሔርን ሕግ አፍርሷልና፤ የነፍስና የሥጋ ንጉሥ በሚኾን በሰማያዊ ንጉሥ ፊት መቆምንም አቃሏልና።
ሐዋርያት በሲኖዶሳቸው እንዲህ አስተማሩን» የሚል ነው።
በዚህ ራሳችን በምናዜመው የቅዳሴ ክፍል መሠረት ቅዳሴውን ከመዠመሪያው እስከ
መጨረሻው ካላስቀደስን፣ መጻሕፍት ሲነበቡ ካልሰማን፣ ሥጋና ደሙን ካልተቀበልን ከቤተ ክርስቲያን በራሳችን ፈቃድ ተለይተናል ማለት
ነው። ቅዳሴ አስቀድሶ የማይቆርብ ሰው ከትንሣኤ እስከ በዓለ ሃምሳ ድረስ ባሉ ሃምሳ ቀናት ብቻ ነው ራሱን የማያወግዝ እንጂ ከዓመት
እስከ ዓመት ቅዳሴው እስኪያልቅ ባላስቀድስ፤ መጻሕፍት ሲነበቡ ባልሰማ፤ ቅዳሴው ሲያልቅም ባልቆርብ ከቤተክርስቲያን አንድነት ይለየኝ
እያለ ራሱን ሲያወግዝ ይኖራል ማለት ነው። ከትንሣኤ እስከ በዓለ ሃምሳ ድረስ በዚህ ራሳችንን በምናወግዝበት ቃል ፈንታ «ሃሌ ሉያ
ዮሴፍ ወኒቆዲሞስ ገነዝዎ ለኢየሱስ በሰንዱናት ለዘተንሥአ እሙታን በመንክር ኪን - ሃሌ ሉያ ዮሴፍና ኒቆዲሞስ ድንቅ በሚኾን ጥበብ
ከሙታን ተለይቶ የተነሣ ኢየሱስን በበፍታ ገነዙት» እያልን እናዜማለንና ውግዘቱን ከራሳችን ላይ የምናነሣው በእነዚህ ሃምሳ ቀናት
ብቻ ነው ማለት ነው።
የቀደሙት ቅዱሳን አባቶቻችን ቀድሰው ሲያቆርቡ ፀሐይ ትጠልቅባቸው ስለነበር
ፀሐይን እየገዘቱ ወደ ማደሪያዋ እንዳትገባ ያደርጉ የነበረው አስቀዳሹ ኹሉ ይቆርብ ስለነበር ነው። ክርስቲያን ተብሎ የማያስቀድስ
አስቀድሶ ደግሞ የማይቆርብ የለም ነበር። ቤተክርስቲያን በምታዝዘው መሠረት ኹሉም ምንባባት እና ቅዳሴያት በዜማ እና በንባብ ተጨማሪ
ጸሎትም በምንባብና በዜማ ይደርስ ስለነበር ይኼ ቀን የምንለው ዐሥራ ኹለት ሰዓት በቂ አልነበረም። ለዚህ ነው በመላእክት ሥርዓት
ሃያ አራቱን ሰዓት በሙሉ ሲያመሰግኑ የሚያድሩት። ዛሬ ዛሬ ስንፍናችን ከፍ ያለ ስለኾነ ጀንበር እስትጠልቅ ድረስ የሚያቆይ አገልግሎት
የለንም። በሥርዓቱ መሠረት ብንሄድ ቅዳሴው ሲቀደስ ስንት ሰዓት ይፈጅ? ሰዓታቱ ኪዳኑ ሲደርስ ስንት ሰዓት ይፈጅ? ማኅሌቱ ስንት
ሰዓት ይፈጅ? ለማቁረብ ስንት ሰዓት ይወስድ ይመስላችኋል?በተለይ በገጠሪቱ የሀገራችን ክፍሎች ላይ ቅዳሴ ከአርባ ደቂቃ በላይ አይፈጅም።
ሌሎች አገልግሎቶችም እንደዚሁ በጥድፊያ ነው የሚፈጸሙት። በርግጥ መድረስ የሚገባው ነገር ሳይደርስ አይቀርን አንድኛውን የታጎለ
ካልኾነ በቀር። ኾኖም ግን በአንድ አገልግሎት ላይ አምስቱም ልዑካን የየግል ድርሻቸውን ፈጽመው ጨረስኩ ጨረስኩ የሚባባሉበት ውድድር
መኾን የለበትም። ዲያቆኑ ተንሥኡ ለጸሎት እያለ ተሰጥዎውን ሳይቀበሉ ካህኑ ሰላም ለኩልክሙ ይላል። በዚህ ሰዓት ምእመኑ የዲያቆኑን
እግዚኦ ተሣሃለነን ወይስ የቄሱም ምስለ መንፈስከን ይመልስ። ዲያቆኑ መልእክታትን አንብቦ ሳይጨርስ ካህኑ ግብር ሐዋርያትን አንብቦ
ይጨርሳል። ዲያቆኑ የዕለቱን ምስባክ ሳይሰብክ ካህኑ ወንጌልን አንብቦ ይጨርሳል። እንዲህ ኾኖ ተቀድሶ ነው በአርባ ደቂቃ የሚፈጸመው።
አባቶቻችን ግን ፀሐይ እስክትገባ ድረስ ቀድሰው ያቆርቡ ነበር። ሥርዓት አትዛነፍባቸውም ነበር። የዛሬ እኛዎች ግን በጣም ሰነፎች
ነን።
በቅዳሴ ሥርዓት ላይ እንዲህ ነገር ማብዛታችን የሥርዓታችን ኹሉ የመጨረሻ
መደምደሚያ የኾነው ሥጋና ደም የሚገኘው በቅዳሴ ስለኾነ ነው። ንስሐ ብንገባ፣ ተክሊል ብንፈጽም፣ ክርስትና ብንነሣ (ብንጠመቅ)፤
ያለቅዳሴው ሥጋና ደሙን ከየት እናገኘዋለን? ሥጋና ደሙን ካልተቀበልን ደግሞ ንስሐም፣ ተክሊልም፣ ጥምቀትም የለንም። ሥርዓት ከመጣስ
ስላልቦዘንን ነው እንጂ ሥርዓት እንዳይጣስም መጠበቅ ድርሻችን ነው። የቀደሙ አባቶቻችንን እስኪ እንጠይቃቸው። ለቤተክርስቲያን የነበረውን
ክብር እስኪ እናስታውሰው። ገና ከቅጽሩ በር ጀምሮ ጫማ ተወልቆ ነበር እኮ የሚገባው። እግዚአብሔር ሙሴን ዘፀ ፫÷፭ ላይ ሙሴን፡-
«የቆምክባት ምድር የተቀደሰች ናትና ጫማህን አውልቅ» ማለቱን እንዴት እንዘነጋዋለን? አባቶቻችን ይህንን ሲተረጒሙ የመለኮት እና
የትስብእት ነገር (ምስጢረ ተዋሕዶ) በሚነገርበት ቦታ ኹሉ ጫማን ማውለቅ ይገባል ብለው አስተምረውናል። ታዲያ ቤተክርስቲያናችን
ምስጢረ ተዋሕዶን የማታስተምር ይመስል ከነጫማችን ዘው ብለን መግባታችን ስለምንድን ነው? ጫማ ኃጢአት ነው እንጂ የእግራችን ጫማ
አይደለም ብላችኹ እንደምታስቡ እገምታለሁ። የኃጢአትን ጫማ ማውለቅ ግድ ይለናል የእግራችንንም እንደዚያው ማለት ነው። ዛሬ ግን
በአንድ እግራችን ቅኔ ማኅሌቱ ላይ ቆመን ነው የኹለተኛ እግራችንን ጫማ የምናወልቀው። ምክንያቱም አፈር ይነካናላ! አቤት ክብር
አቤት ብልጽግና! በእውነት ከአፈር ተሠርተን አፈርን እንጠየፍ ዘንድ እኛ እነማን ነን? በዚያውስ ላይ የቤተክርስቲያኗ አፈር በረከት
እንጂ መርገም ያደርስ ይመስል የምንጠየፈው ስለምንድን ነው? አፈርን የሚጠየፍ አፈር (ሸክላ) እኛ ነን። ይህ ኹሉ የእምነታችን
መቀጨጭ የወለደው ክፉ በሽታ ነው።
※※※※※※※※³ ※※※※※※※※
‹‹መጥፎውን ሽሹ መልካሙን ሹ››
ኢሜይል፡- melkamubeyene60@gmail.com
ፌስቡክ ላይክ ገጽ፡-facebook.com/melkamubeyeneB
No comments:
Post a Comment