============================
በፊት ሕዝቡ
በአንድ ጎን ሲሄድ ካህናት ደግሞ ከሥራ ያግዱናል በሚል ፍርሐት በሌላ ጎን ሳይወዱ አባ ማርቆስን ደግፈው ሲቆሙ ቆይተዋል፡፡
በዘንድሮው
የቅዱስ ሲኖዶስ ስብሰባ ላይ ግን ከየትም ቦታ ካህናት እንደማይደግፏቸው ስላወቁ ጎንቻዎችን እና መርጡለማርያሞችን ተነሡ እያሉ ነው፡፡
ሙሉው የጎንቻ እና የመርጡለ ማርያም ካህናት የአባ ማርቆስ ደጋፊዎች ናቸው ባይባልም አብዛኞቹ ግን እንባረራለን በሚል ፍርሐት ደግፈው
መሄዳቸው አይቀርም፡፡ ዓይነኩሉ እና ዕዝራ እንዲያስተባብሩ ኃላፊነት የተሰጣቸው ሲኾን የደርሶ መልስ ጉዞውንም ከቤተክርስቲያን ገንዘብ
ወጭ አድርገው እንደሚጓዙ ራሳቸው ተናግረዋል፡፡ ጎንቻ እና መርጡለ ማርያም ላይ ያሉ ካህናት በቁጥር አነስተኛ ቢሆኑም እንኳ አዲስ
አበባ የሚኖሩ የሚያውቋቸውን ካህናት በገንዘብ ገዝተውም ቢኾን እኔም ደጋፊ አለኝ ማለታቸው አይቀርም፡፡ ያለቀለትን የሞተውን ነገር
ነፍስ ሊዘሩበት ግን አይችሉም፡፡
አሁን የሚደረገው
የካህናትና የምእመናን ጉዞ 12ኛ ይኾናል፡፡ በዚህ 12ኛው ጉዞ አቡነ ማርቆስ እንደሚነሡ ብዙዎች ተስፋ የሰጡ ቢኾንም ደብዳቤው
እስካልተጻፈ ድረስ ማመን ሞኝነት ነው፡፡ የምሥራቅ ጎጃም ጉዳይ እንደ አንድ አጀንዳ ተይዟል የተባለው ጉዳይም ቅዱስ ሲኖዶስ ስብሰባውን
ጀምሮ የመወያያ አጀንዳዎች እስኪጸድቁ ድረስ ብንታገስ መልካም ነው፡፡ አምናም አጀንዳው ተይዟል ተብለን ተመልሰን ነው አጀንዳው
ሳይጸድቅ ቀርቶ የምሥራቅ ጎጃም ጉዳይ በድፍኑ የታለፈው፡፡
የዘንድሮው
ጉዞ ግን ልዩ የሚያደርገው፡-
1ኛ. የየደብሩ
እና ገዳማቱ አስተዳዳሪዎችን ጨምሮ በርካታ ካህናት እና ዲያቆናት የሚሳተፉበት መኾኑ፡፡
2ኛ. ቅዱስ
ሲኖዶስ እንዲነሡ ወሰነም አልወሰነም አቡነ ማርቆስ ዳግም ወደ ምሥራቅ ጎጃም ሊመጡ እንደማይችሉ አቋም የተያዘበት መኾኑ ነው፡፡
3ኛ. እርሳቸውን
ደግፈው የሚሄዱ ካህናት ያለመኖራቸው፡፡ ደብረ ማርቆስ ላይ ከሦስት የማይበልጡ ሥልጣን ፈላጊዎች እርሳቸውን ደግፈው እንደሚሄዱ ይጠበቃል፡፡
የተቀረው ግን ከጎንቻ እና ከመርጡለ ማርያም ሊሄዱ እንደሚችሉ ይጠበቃል፡፡ ከብቸናም ሥራ አስኪያጁ እሄዳለሁ እያሉ ነው ተብሏል፡፡
የመልአከ ብርሃን አድማሱ፣ የአለቃ አያሌው ሀገር ብቸና እርሳቸውን መክራችሁ ዘክራችሁ አስቀሯቸው፡፡ ባለቀ ነገር ላይ ትዝብት አታትርፉ
በሏቸው፡፡
ከጎንቻ አስተባባሪዎች
እንደተነገረው ከኾነ ከአንድ ደብር አንድ መኪና ሞልተው እንደሚሄዱና ለኹሉም ካህናት አበልና ለትራንስፖርት ወጭ ከቤተክርስቲያን
አንድ ጊዜ ታዝዞ እንደሚወጣ ተናግረዋል፡፡ መርጡለ ማርያም ላይ ጥቂት የሚባሉ ሥልጣን ፈላጊዎች እንደሚሄዱ ይጠበቃል፡፡ መርጡለ
ማርያሞች ከአቡነ ማርቆስ ጋር ግንኙነታቸው ያን ያህል ነው፡፡ ኾኖም ግን አዲስ እየተሠራ ያለውን ካቴድራል እንደምክንያት በማስቀመጥ
እርሳቸው ከተነሡ ግንባታው ይቋረጣል በሚል የሞኝነት ብሒል ሳይወዱ እየተከተሉ ናቸው፡፡ ሕንጻው እየተገነባ ያለው በመርጡለ ማርያም
ሕዝብ ነው፡፡ አዲስ አበባ ላይ ያሉ የሕንጻ ግንባታ አስተባባሪዎችም ቢኾኑ ከአቡነ ማርቆስ አምስት ሳንቲም እንዳላገኙ ይታወቃል፡፡
ስለዚህ በዚህ ስም አትረበሹ፡፡
ጎንቻና መርጡለ
ማርያም ላይ መሠራት ያለበት አንድ ነገር አለ እርሱም ማንኛውም ቤተክርስቲያን ወጭ አድርጎ ገንዘብ እንዳይከፍል ነው፡፡ ደግፎ መሄድ
የሚፈልግ ኹሉ ከራሱ ኪስ በተከፈለ ገንዘብ ነው መሄድ ያለበት፡፡ ይህንንም ለሚመለከተው ሕጋዊ አካል ማሳወቅ ያስፈልጋል፡፡ ገንዘቡ
የቤተክርስቲያን ከሕዝቡ የተሰበሰበ እስከኾነ ድረስ ለዚህ አገልግሎት ሲውል በአበል ስም ገንዘቧ ሲመዘበር ዝም ማለት አያስፈልግም፡፡
ከዞን ጋር
መገናኘት የምትችሉ አካላትም ይህንን ነገር አሳውቁ፡፡ ገንዘቡ ከቤተክርስቲያን ወጭ እንደሚደረግ አስተባባሪው ዓይነኩሉ የነገረን
ሙሉ ማስረጃ በድምጽ ስላለ እርሱን ለሚመለከተው አካል ማቅረብ ስለምንችል ለመንግሥት አካላት እናሳውቅ፡፡ መሄድ ካለባቸው እንኳ
በራሳቸው ገንዘብ ይሂዱ እንጅ ቤተክርስቲያን ልትመዘበር አይገባትም፡፡ መርጡለ ማርያምና ጎንቻ ላይ ያሉ የወረዳ ቤተክህነት ኃላፊዎችም
ይህንን እያወቁ ተባባሪ ከኾኑ ካልከለከሉ ሕጋዊ ክስ ሊመሠረትባቸው ይገባል፡፡ ማንኛውም የቤተክርስቲያን ጉዳይ ያገባኛል ያለ አካል
ኹሉ ይህንን ክስ መመሥረት ይችላል፡፡
ጎንቻና መርጡለ
ማርያም ሰው የለውም ሲባል መስማት ያማል፡፡ የሊቃውንቱ መፍለቂያ፣ የቅኔው፣ የትርጓሜው ማማ ቤተክርስቲያኑ ስትደፈር ገንዘቧ ስትመዘበር
ዝም ካለ ነገሩ ከባድ ነው፡፡ ያስወቅሳል፡፡
======================
ጥቅምት
09/2011 ዓ.ም
ደብረ ማርቆስ፣
ኢትዮጵያ
No comments:
Post a Comment