ይኼም የዘመቻ
ማርቆስ አካል ነው! የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን አለቃ አያሌው ታምሩ እንደገለጿት ስንዱ እመቤት ናት፡፡ ስንዱ
እመቤት ኹሉን በየፈርጁ አዘጋጅታ ለሚፈልገው ሰው ኹሉ የሚፈልገውን ነገር የምታቀርብ ናት፡፡ ሊቃውንት ሞልተዋታል፡፡ ድጓውን፣ ጾመ
ድጓውን፣ ቅዳሴውን፣ አቋቋሙን፣መጽሐፉን፣ ቅኔውን ወዘተ አሰናድታ የምታቀርብ እመቤት የተሰናዳውንም የሚመገብ ሊቅ አላት፡፡ በመጽሐፍ
የተጻፈውን በተግባር ኖረው ያስተማሩ ብዙዎች ናቸው፡፡ እገሌ እገሌ ማለት ስለሚከብደኝ ዝርዝር ውስጥ አልገባም፡፡ ብዙዎች ለጠያቂዎች
መልስ ሲሰጡ ቤተክርስቲያንን ከመናፍቃን ከከሐድያን ሲጠብቁ እነርሱ እንደሻማ እየቀለጡ ለእኛ ብርሃን ድምቀት ኾነው ቤተክርስቲያንን
ያስረከቡን ናቸው፡፡ ቤተክርስቲያናችን በግብጽ ተጽዕኖ ሥር በነበረችበት ጊዜ ያን ያህል ውጣ ውረድ ወርደው እና ወጥተው መጻሕፍትን
ጠቅሰው ተከራክረው ለዛሬው የቅዱስ ሲኖዶስ መሠረት የኾኑት እነመልአከ ብርሃን አድማሱ ጀንበሬ የሚረሱ አይደሉም፡፡ እነርሱ የኖሩት
ለቤተክርስቲያን ነው የሞቱትም ለቤተክርስቲያን ነው፡፡ መናፍቃን እጃቸውን ወደ ቤተክርስቲያናችን በቀሰሩ ጊዜ በመጽሐፍ የመጣውን
ጦር በመጽሐፍ አፈር ያስጋጡት ደገኛ አባት ነበሩ፡፡ ምሥረቅ ጎጃም ሐገረ ስብከት ያፈራቻቸው የወለደቻቸው ብዙ ልጆች አሏት፡፡ ቅጥሯን
ጠብቀው ከወራሪ ጠላት መክተው ያስረከቡን ብዙዎች ናቸው፡፡ ኹለተኛውን ፓትርያርክ ብጹዕ ቅዱስ ወሰማእት አቡነ ቴዎፍሎስ ብንወስዳቸው
ለቤተክርስቲያናችን ሲሉ ራሳቸውን እንደሚታረድ በግ አሳልፈው የሰጡ ናቸው፡፡ ታላላቅ ሊቃውንትን እነ መልአከ ብርሃን አድማሱን እነ
አለቃ አያሌው ታምሩን መጥቀስ ይቻላል፡፡ እነዚህን የምጠቅሰው ማንም የሚያውቃቸው ስማቸው ሲነሣ መናፍቅ የሚሸበርላቸው ስለኾነ እንጅ
ብዙ ያልተወራላቸው ታሪካቸው ያልተነገረላቸው ሊቃውንት ሞልተዋል፡፡ እነ የንታ ዘሚካኤል ይኹኔን እነ ርእሰ ርኡሳን አባ ኃለ ኢየሱስ
ዘመርጡለ ማርያምን እነ የንታ መምህር ወልደ ኢየሱስ መቅጫ ዘዲማን ወዘተ መጥቀስም እንችላለን፡፡
እነዚህ ሊቃውንት
በሕይወት ያሉትም ኾኑ በሕይወት የተለዩን ያስተማሩን ትምህርት ዛሬ በሊቀ ጳጳስነት ተቀምጠው ካስተማሩን ከአቡነ ማርቆስ ትምህርት
ጋር ይለያያል፡፡ አቡነ ማርቆስ ቅኔ እንተማሩ እና የቅኔ መምህርም ኾነው እንደቆዩ ብዙዎች ይመሰክሩላቸዋል፡፡ ለአቡነ ማርቆስ ትምህርት
ማለት ቅኔ ብቻ ነው፡፡ ክህነት ለመሾም ሲፈልጉ ሰውን ለማሸማቀቅም ሲያምራቸው ‹‹ቅኔ ተምረሃል›› ነው ጥያቄቸው፡፡ ቅኔ ኹሉን
ትምህርት ተምሮ በተለይ መጻሕፍትን አውቆ ቢኾን ምስጢርን ከምስጢር ለማያያዝ ይመቻል፡፡ ቅኔ ስላልተማርሁ ስለማላውቅም በቅኔ እውቀታቸው
ላይ ምንም ልል አልችልም፡፡ ኾኖም ግን የእውቀት ኹሉ ጣሪያ ቅኔ ማወቅ ነው ብየ አልወስደውም፡፡ እርሳቸው መጽሐፍ ላይ ያን ያህል
ናቸው፡፡ በርግጥ መጽሐፍ ጠቅሰው ሲያስተምሩ ያየሁበት የሰማሁበት ጊዜ በጣም ጥቂት ነው፡፡ አብዛኛው ትምህርታቸው ቃለ መጠይቅ ማድረግ
ሰውን ማሳቅ ካህናትን ማሸማቀቅ የተሐድሶ መናፍቃንን ትምህርት በቀልድ መልኩ ማስገባት ነው፡፡ በተለይ አብነት ትምህርት ላይ አመለካከታቸው
ጥሩ አይደለም፡፡
አንድ ጊዜ
እዚህ ደብረ ማርቆስ ከሚገኘው ደብረ ብርሃን ሥላሴ ቤተክርስቲያን አባታችን ይመጣሉ ተብለው የአቋቋም ተማሪዎች አንድን ጳጳስ ለመቀበል
የሚደረገውን ዝግጅት አጠናቀው ይጠብቋቸዋል፡፡ ተማሪዎቹ ጠምጥመዋል፣ መቋሚያ ይዘዋል፣ ጸናጽሉ ቀርቧል፣ ከበሮው መጥቷል፣ አለባበሳቸውን
አስተካክለዋል፡፡ በዚህ ኹኔታ አባ ማርቆስ ይመጣሉ መኪናቸው በሯ ተከፍቶ ይወጣሉ፡፡ ተማሪዎችን ሲመለከቱ ‹‹እነዚህ ደግሞ እነማን
ናቸው? ምንድን ናቸው?›› ይላሉ፡፡ አንዱ ፈጠን ብሎ ‹‹አባታችን እነዚህማ እርስዎን ሊቀበሉ የተዘጋጁ የአቋቋም ተማሪዎች ናቸው››
ይላቸዋል፡፡ እርሳቸውም ‹‹ምንድን ነው አቋቋም ከተማሩ ቅኔ ነው እንጅ ዝም በሉ በላቸው›› ብለው አረፉት፡፡ በዚህ ሰዓት ተዘጋጅተው
የነበሩት ተማሪዎች እንዲህ ያሉ አባት ብለው ተናደው ትተዋቸው ሄደዋል፡፡ በቦታው የነበሩ ተማሪዎች ይህንን ካዩት አስተያየት ቢሰጡበት
ደስ ይለኛል፡፡
እርሳቸው ትንሽ
ቅኔ ላይ ስለሚሞካክሩም ቅኔ ይጠይቃሉ፡፡ ነገር ግን ‹‹ድጓ ቅኔ ተምረህ ሰው አትኾንም›› በማለት ተማሪዎችን ተስፋ ያስቆረጡበት
ትምህርትም አለ፡፡ ይህንን ትምህርታቸውን ከዚህ ጋር የተያያዘውን ቪዲዮ በመክፈት መስማት ትችላላችሁ፡፡
በነገራችን
ላይ የአቡነ ማርቆስ ቡድን በዘንድሮው የሰበካ መንፈሳዊ ጉባዔ ላይ ድል አልቀናውም፡፡ ኹለት ሥራ አስኪያጅ ያለው ብቸኛው ሀገረ
ስብከትም ኾኖ ታይቷል፡፡ የምሥራቅ ጎጃም ጉዳይ ሪፖርት ይቅረብ ሲባል ኹለት ሥራ አስኪጆች ተነሥተው ታይተዋል፡፡ አንዱ ጠቅላይ
ቤተክህነት የሚያውቃቸው አንደኛው ደግሞ በፎርጅድ ማኅተም ያለጠቅላይ ቤተክህነት እውቅና በአቡነ ማርቆስ የተሾሙ ናቸው፡፡ በዚያም
አለ በዚህ ግን የተነበበው ሪፖርት ከምእመናን ጋር ያሉት ሥራ አስኪያጅ ጠቅላይ ቤተክህነት የሚያውቃቸው ሥራአስኪያጅ የጻፉት ሪፖርት
ነው፡፡
ሲኖዶስ ስብሰባ
ላይ ምሥረቅ ጎጃም አንድ አጀንዳ መኾኑ አይቀሬ ነው፡፡ አቡነ ማርቆስም ከሳሾቼ ማኅበረ ቅዱሳን ነው ከሳሾቼ የማርቆስ ዱርዬዎች
ናቸው ይሉ ይኾን፡፡ ቀኑ ሲደርስ ካህናትን ከፊት ሲመለከቷቸው እናንተም ለቤተክርስቲያን መቆም ጀመራችሁ ማለታቸው አይቀሬ ነው፡፡
#አዊዎችስ ምን አሰባችሁ፡፡ እናንተም ተዘጋጁና ለመጨረሻ ጊዜ የተሐድሶንና የቅባትን ክንፍ እንስበረው፡፡ አባ ቶማስ እና አባ ማርቆስ
መነጋገሪያ አጀንዳዎች ኾነዋልና፡፡ ትምህርቶቻቸውም እየተገመገሙ ናቸው፡፡ የአዊው ሊቀ ጳጳስ በኢኦተቤ መስከረም 21 ያስተማሩት
ትምህርት እየተላለፈ ነው፡፡ ያ ትምህርት ራሳቸው ፓትርያርኩ ባሉበት የተሰጠ ትምህርት ነው፡፡ ተሐድሶን ለምን ትቃወማላችሁ ዓይነት
ትምህርት ነው ያስተማሩ፡፡ ያንን ትምህርት በቴሌቪዥን እንዲተላለፍ ያደረጉት ደግሞ ቀኝ እጃቸው አቡነ ማርቆስ ናቸው፡፡ ምክንያቱም
ቴሌቪዥኑ የእርሳቸው ነውና፡፡ ስለዚህ አቡነ ማርቆስ በተለይ ስብከተ ወንጌል መምሪያውን ለተማሩ ሊቃውንት እንዲለቁና ቴሌቪዥኑንም
ለቀቅ አድርገውት አብነት ትምህርት የምንማርበት እንዲኾን ኹላችንም ቅዱስ ሲኖዶስን መጠየቅ ይኖርብናል፡፡
======================
ጥቅምት
07/2011 ዓ.ም
ደብረ ማርቆስ፣
ኢትዮጵያ
No comments:
Post a Comment