Sunday, October 14, 2018

ዘመቻ ማርቆስ!



==========
ዘመቻችንን የምንጀምረው ዛሬ ይኾናል፡፡ ብጹእነታቸው አቡነ ማርቆስ ምሥራቅ ጎጃም ሐገረ ስብከትን ለተሐድሶ መናፍቃንና ለቅባት እምነት አሳልፈው የሰጡ ናቸው፡፡ ሐገረ ስብከቱን ከነፍስ ኄር ብጹእ አቡነ ጴጥሮስ ከተቀበሉበት 2004 ዓ.ም ጀምሮ ሰላም እንዲያጣ ያደረጉ ናቸው፡፡ ሐገረ ስብከቱን የዘመድ አዝማድ መሠብሰቢያ ያደረጉት ብጹእነታቸው ምእመናንን በእጅጉ አስለቅሰዋል፡፡ የአቡነ ማርቆስን የጥፋት ሥራዎች ከዚህ በፊት ያቀረብን ቢኾንም ነገ የሚጀምረውን 37ኛ የሰበካ መንፈሳዊ ጉባዔ ምክንያት በማድረግ እርሳቸው እና የግብር ልጆቻቸው እንዲመከሩበት እና ከኃላፊነታቸውም እንዲነሡ ጉባዔውን ለማሳሰብ እና ለቅዱስ ሲኖዶስ ስብሰባም እንደ አጀንዳ እንዲያዝ ለማሳሰብ በድጋሜ እና ተቸማሪ መረጃዎችን እናካፍላለን፡፡
ስለዚህ ዘመቻችንን አሐዱ ብለን ዛሬ ጀምረናል፡፡ ከተመቻችሁ ይህን ፎቶ ፕሮፋይል ፒክቸር በማድረግ አቡነ ማርቆስ ከያዟቸው ሦስት ቁልፍ ቦታዎች እንዲነሡ እንጠይቅ፡፡ለዘመቻችን አጋር መኾንዎንም ያረጋግጡ፡፡
                     አባ ማርቆስ
. ከምሥራቅ ጎጃም ሐገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስነት
. ከስብከተ ወንጌል ኃላፊነት
. ከቴሌቪዥን የቦርድ ሰብሳቢነት እንዲነሡ ቅዱስ ሲኖዶስን እንጠይቃለን፡፡
. ሰኔ ጎልጎታን ልብ ወለድ ነው ያሉ፡፡
. ተዝካርን ምዋርት ነው ያሉ፡፡
. በዘመነ ዮሐንስ ልደት ታኅሣሥ 28 መከበር የለበትም ያሉ፡፡
. ተዋሕዶ፣ ቅባት፣ ካራ፣ ጸጋ የሚባል ነገር የለም ያሉ፡፡
. ሐገረ ስብከቱን ለቅብዓትና ለተሐድሶ አሳልፈው የሰጡ፡፡
. ደመወዛቸውን ከ10ሺህ ወደ 17 ሺህ በር ያሳደጉ፡፡
. ድጓ፣ ቅኔ ተምረህ ሰው አትኾንም ያሉ፡፡
. የጽጌ ጾምን ያመጣብን ሰንበት ትምህርት ቤት ነው ያሉ፡፡
. የከሳ የሚወፍረው በጽጌ ጾም ነው ሥጋና ቅቤ ስለሚበላ ያሉ፡፡
==========
ጥቅምት 04/2011 ዓ.ም
ደብረ ማርቆስ፣ ኢትዮጵያ

No comments:

Post a Comment