Saturday, October 20, 2018

ወልደ አብ ለምን ተወገዘ?



================
አቡነ ማርቆስን ደግፈው አዲስ አበባ ሊሄዱ የተዘጋጁ የቅብዓት እምነት ተከታዮች በተለያዩ ጊዜያት ሰፊ ውይይት አድርገዋል፡፡ ጎንቻ ላይ ያለው ቡድን ለኹለት የተከፈለ ይመስላል፡፡ አንደኛው ቡድን አቡነ ማርቆስ ቅብዓት እምነትን እንዲያስቀጥሉልን ከፈለግን ወልደ አብ ለምን ተወዘገ? ልንል አይገባንም፡፡ ከዚህ በተጨማሪም ቅብዓት የሚባል ነገር በጭራሽ መነሣት የለበትም፡፡ ሙያ በልብ ነውና በማለት በጠንካራው ሞግቷል፡፡ ኹለተኛው ቡድን ደግሞ ያበጠው ይፈንዳ እስከመቼ ድረስ ተሸማቀን እንኖራለን፡፡ ቅዱስ ሲኖዶስም ይወቀው፡፡ ቅብዓት እምነታችን ነው ወልደ አብም መጽሐፋችን ነው፡፡ ለምን ተወገዘ? ብለን መጠየቅ አለብን፡፡ እስከመቼ ድረስ ነው አንገታችንን ደፍተን የምንኖረው፡፡ ኹሉ ነገር መገለጥ አለበት ብለዋል፡፡
በእነዚህ ሃሳቦች ላይ በሰፊው ተወያይተዋል፡፡ ሙያ በልብ ነው የሚሉ ሰዎች ከቆጋ ገዳም መነኮሳትን በጭራሽ ይዘን አንሄድም እነርሱን ይዘን ከሄድን ጉዳያችን ቅብዓት ይመስላቸውና ሲኖዶስም አይፈርድልንም ያሉ ሲኾን ያበጠው ይፈንዳ የሚለው ቡድን ግን ወልደ አብ ለምን ተወገዘ? የሚል ትልቅ ባነር እንደሚይዙም ተናግረዋል፡፡
በእውነት አደንቃችኋለሁ ወልደ አብ ለምን ተወገዘ? የሚል ባነር ይዛችሁ ከመጣችሁ በጣም አደንቃችኋለሁ፡፡ ይህን ባነር ይዛችሁ የሊቃውንት ጉባዔን መሞገት ከቻላችሁ እውነትም ሊቅ ናችሁ፡፡ እስኪ ባነሩን አሠሩት፡፡ እናንተ በወልደ አብ መወገዝ ብቻ አትገረሙ ገና ቀሪ ኹለቱ መጽሐፎቻችሁም አብረው ይወገዛሉ፡፡ አሁን ወልደ አብ ለምን ተወገዘ? ብላችሁ መጠየቅ ካልቻላችሁ የቀሪዎቹን መወገዝም ትሰማላችሁ፡፡ ሊቃውንት ካሏችሁ ‹‹በወልደ አብ መናፍቅ አፈረ›› ብላችሁ ጭፈራ አይሉት መዝሙር ከምትጮኹ እስኪ በአደባባይ እንያችሁ፡፡ እስኪ የሊቃውንት ጉባዔን ሞግቱ፡፡
‹‹አቡነ ማርቆስ የልማት እና የወንጌል አባት ናቸው›› የሚል ባነር አሠርታችሁ ግን እንዳታሳፍሩን፡፡ ዓለም ያወቀውን ፀሐይ የሞቀውን ጉዳይ አንሥታችሁ እንዳታፍሩ፡፡
======================
ጥቅምት 10/2011 ዓ.ም
ደብረ ማርቆስ፣ ኢትዮጵያ

No comments:

Post a Comment