=====================
የምሥራቅ ጎጃም
የተዋሕዶ ልጆች ‹‹ዝ ሕዝብ አብድ ወአኮ ጠቢብ - ይህ ሕዝብ ሰነፍ ነው ጥበበኛ አይደለም›› የተባለለት ሰነፍ ሳይኾን ጥበበኛ
የኾነ ይህ ቃል ተገልብጦ የሚነገርለት ‹‹ዝ ሕዝብ ጠቢብ ወአኮ አብድ- ይህ ሕዝብ ጥበበኛ ነው ሰነፍ አይደለም›› ተብሎ የተመሰከረለት
ጠቢበ ጠቢባን ነው፡፡ ከመነሻው እስከመድረሻው ድረስ ምን ማድረግ ምን መደረግ እንዳለበት የሚያውቅ ጥበበኛ ነው፡፡
አቡነ ማርቆስ
ምሥራቅ ጎጃምን ከያዙበት ሕዳር 2004 ዓ.ም ጀምሮ እስከ ዛሬዋ ዕለት ድረስ 7 ዓመታት ተቆጥረዋል ወር ቢቀራቸውም፡፡ በእነዚህ
ሰባት ዓመታት በትዕግሥትና በጽናት ለ12ኛ ጊዜ ቅዱስ ሲኖዶስ ላይ አቤት ያለ ታጋሽ ሕዝብ ነው፡፡ ምሥራቅ ጎጃም በጀግንነቱ በላይ
ዘለቀ አለለት ልጀግን ካለ እንደ አባ ኮስትር በላይ ይጀግናል፡፡ ልታገስ ካለም እስከሞት ድረስ ራሱን አሳልፎ ይሰጣል፡፡ ለወደደው
ማር ለጠላው ኮሶ ማለት ይኸው ነው፡፡ እንዲያውም ስንክሳር ዘጎጃም የሚባል አለ አሉ፡፡ ስንክሳሩ ወበዛቲ ዕለት አእረፈ አባ ኮስትር
በላይ ይላል፡፡ ሲጨርስ ደግሞ ጀግንነቱ ወንድነቱ ይኅድር በላእሌነ ይላል አሉ፡፡ ይችን የጎጃም ስንክሳር የሰማኋት አባ ማርቆስ
እንዲነሡልን ቅዱስ ሲኖዶስን ለመጠየቅ መንበረ ፓትርያርክ በተገኘሁበት ጥቅምት 11/2011 ዓ.ም ነው፡፡
የተመለከተን
ኹሉ ‹‹ኦ ትእግሥት ዘመጠነዝ ትዕግሥት ኦ ትሕትና ዘመጠነዝ ትሕትና›› የተባለለትን ክርስቶስን መሰላችሁ እኮ ይለናል፡፡ እርሱ
እኮ ሁሉን ማድረግ እየቻለ ኹሉን ነገር ሲያደርጉበት በመታገሱ ራሱን ዝቅ በማድረጉ ነው፡፡ እኛ እኮ ኹሉን ማድረግ ስለማንችል ማድረግ
የምንችላትን ብቻ ማድረግ ስላለብን የተመላለስን ደካሞች ነን፡፡
ያም ኾነ ይህ
ቅዱስ ሲኖዶስ ስብሰባውን በጸሎት ሲከፍት የምሥራቅ ጎጃም ምእመናን በጸሎት መርኃ ግብሩ መገኘት ልማድ ነው፡፡ የቅዱስ ሲኖዶስ ዝምታ
የአቡነ ማርቆስ ወደ ልባቸው አለመመለስ የምእመናን አቤቱታ መብዛት ከዕለት ወደ ዕለት እየጨመረ እንጂ እየቀነሰ አልሄደም፡፡ ብዙዎች
ያላወቁት ነገር ያለ ይመስለኛል ይህንን ግልጽ ማድረግ ተገቢ ነው፡፡ ‹‹ለአንድ መነኩሴ ዐሥራ ኹለት ጊዜ ለምን ትደክማላችሁ? ቅዱስ
ሲኖዶስ መልስ ይሰጠናል ብላችሁ መጠበቃችሁ በራሱ ሞኝነት ነው›› የሚሉን አሉ፡፡ ታዲያ ምን ማድረግ ነበረብን? ብለን ስንጠይቃቸው
የጎጃም ጀግንነት የት ገባ? ብለው መልሰው ይጠይቁናል፡፡ ለእኛ ጀግንነት ትእግስት ነው፤ ጀግንነት ትሕትና ነው፤ ጀግንነት ሥርዓትን
ማክበር ሕግን መጠበቅ ነው፤ ጀግንነት የአባቶቻችንን ድምጽ መስማት ነው፡፡ ለዚህም ነው የቅዱስ ሲኖዶሱን ልእልና የአባ ማርቆስን
ክብር ጠብቀን በ7 ዓመት ውስጥ 12 ጊዜ የተመላለስን የደከምን የወጣን የወረድን፡፡ አባ ማርቆስን ከመድረክ ጎትቶ ማውረድ ቀላል
ነው፡፡ አባ ማርቆስን ጎጃምን እንዳይረግጧት ማድረግ ቀላል ነው፡፡ በእርሳቸው ላይ ጥቃት ማድረስም ቀላል ነው፡፡ ይህ ኹሉ ግን
እምነታችን የሚፈቅደው አይደለምና ትዕግስትን እና ቻይነትን ተመልተን ይኸው ዛሬም የቅዱስ ሲኖዶሱን ውሳኔ በመጠባበቅ ላይ እንገኛለን፡፡
በአንድ አቅጣጫ ማሰብ ጥሩ አይደለም፡፡ ዛሬ የምንሠራው ጥፋትም ልማትም የነገ ታሪክ ነው፡፡ ዛሬ ጎትተን ብናወርዳቸው ነገ ጥሩ
አባት ቢመጡም በተቃራኒው ጎራ ያሉ ሰዎች ጎትተን እናውርድ ማለታቸው አይቀርም ምክንያቱም ታሪክ ኾኖ ይቀመጣልና፡፡ መንፈስ ቅዱስ
ይመራዋል የምንለውን ሲኖዶስም ማሳዘን ማስቀየም አንፈልግም፡፡ ለበረከት ብለን መቅሰፍትንም አንሻም፡፡ አቡነ ማርቆስን ከመድረክ
ጎትቶ ለማውረድ ብዙ ምቹ ጊዜ ነበረን ግን አላደረግነውም አናደርገውምም፡፡ ምንም ይኹኑ ምን የያዙት ስም የጨበጡት በትረ ሙሴ የደፉት
ቆብ የተቀመጡበት መንበር ክብር አለው፡፡ እርሳቸው ግን ያንን ክብራቸውን አዋርደዋል፡፡ ያዋረዱት ሰው በመኾናቸው ነውና እርሳቸውን
እንደሰውነታቸው ወድደን አፍቅረን እንደማዕርጋቸውም አባ አቡነ ብፁዕ ብለን ሥራቸውንና ተግባራቸውን የያዙትን የጥፋት መንገድ ግን
እጅጉን እንቃወማቸዋለን፡፡ ደጋፊዎቻቸውም ያልገባቸው ይኸው ነው፡፡ እነርሱ ደጀን ላይ ግፍ ፈጽመዋል፡፡ ጌታቸው ተፈሪ የተባለውን
ወንድማችንን መምህራችንን አፍነው ወስደው በፈላ ውኃ ሲገሽሩት በብርጭቆ ሲላጨጩት ውለዋል፡፡ ድግምት መተታቸውን መትተውበታል፡፡
በፀበል ቢድንም፡፡ ይህ ክርስቲያናዊ ሥነ ምግባር አይደለም፡፡ ንግባዕኬ ኀበ ጥንተ ነገር እንዳለ ወደ ጥንተ ነገራችን ተመልሰን
የ12ኛውን ጉዟችንን እንናገር፡፡
ቀኑ 11 ዕለቱ
እሁድ ሰዓቱ 9 ሰዓት ነበር ኩንትራት ወደ ተያዙት መኪኖች መግባት የጀመርነው፡፡ ኾኖም ግን ማኅሌት ያደሩ አባቶች ወንድሞች እህቶች
ስለነበሩና ከሩቅም የሚመጡ ብዙዎች ስለኾኑ እነርሱን በመጠበቅ ሰዓታት አልፈዋል፡፡ ኹሉም አውቶቡሶች በተመሳሳይ ሰዓት እንዲነሡ
ለማድረግ ሲባል መጠባበቅ ስለነበረብን ከደብረ ማርቆስ የተነሣነው ከ10 በኋላ ነበር፡፡ ከደጀን እና ከብቸናም እንደዚሁ ከዚህ ሰዓት
በኋላ ተነሥተዋል፡፡ ከደብረ ማርቆስ 5 አገር አቋራጭ አውቶቡሶች እያንዳንዳቸው ከ60 ሰዎች በላይ ጭነው፣ ከደጀን አንድ ከብቸና
ኹለት አይሱዙ ቅጥቅጦች በተጨማሪነት አብረው ተጉዘዋል፡፡ ጉዟችን የቤተክርስቲያንን ችግሮች እንዲፈቱልን ለመጠየቅ የተደረገ እንደመኾኑ
መጠን የጉዟችን መጀመሪያ የነበረው ጸሎት ነበር፡፡ ጸሎት አድርገን ጉዟችንን ጀመርነው፡፡
የአቡኑ ደጋፊዎች
ደግሞ በሚኒ ባስ ተጭነው በረዋል፡፡ የደብረ ማርቆስ አካባቢ ደጋፊዎች ደግሞ በአንድ አይሱዙ ቅጥቅጥ ተጭነዋል፡፡ የጎንቻዎቹ በሚኒባስ
ናቸው፡፡ ደጀን ላይ ኹላችንም ከትመናል፡፡ ኹሉም መኪኖቻችን ቆመዋል፡፡ ምክንያቱ ምንድን ነው? ለምን አንሄድም? ረፈደብን እኮ
የሚሉ ድምጾች ተስተጋቡ፡፡ የቆምንበትን ምክንያት ግን የተረዳ አልነበረም፡፡ አንዳንዶች ከዐሥራ ኹለት ሰዓት በፊት መሄድ ስለማይቻል
ነው የቀረን አምስት ደቂቃ ነው እንንቀሳቀሳለን ይላሉ፡፡ አንዳንዶች ኬላ ላይ ፍተሻ ስላለ ነው ፍተሻው ሲያልቅ እንሄዳለን ይላሉ፡፡
እኛም ጠበቅን ወዲያውኑ የአባ ማርቆስ ደጋፊዎች ሚኒባሳቸውን ወደ ከተማ አዙረው መብረር ጀመሩ፡፡ ምንድን ናቸው? ምንድን ናቸው?
ያዛቸው ያዛቸው የሚል ድምጽ ከየአቅጣጫው ተሰማ፡፡ ያኔ ነበር የአባ ማርቆስ ደጋፊዎች መኾናቸውን የተረዳነው፡፡ 6ቱም ሚኒባሶች
ወደ ፖሊስ ጣቢያ እንዲገቡ ተደረጉ፡፡ ምክንያቱ ደግሞ ሕገ ወጥ ናችሁ በሚል ነው፡፡ ሚኒባሶች ከጎንቻ ሲነሡ መውጫ አልቆረጡም ነበር፡፡
ደጀን ላይ ተይዘው መውጫ አምጡ ሲባሉ የላቸውም፡፡ ከሌላችሁ ወደ ፖሊስ ጣቢያ ዙሩ ተብለው እያንዳንዳቸው 5ሽህ 5ሽህ ብር ተቀጥተው
ተለቀቁ፡፡ በጠቅላላው 30ሺህ ብር መኾኑ ነው ቅጣታቸው ብቻ፡፡ ከደብረ ማርቆስ የተነሣው የአይሱዙ ቅጥቅጥ ግን አልተቀጣባቸውም፡፡
ኹላችንም ደጀን ኬላ ላይ ያለውን ማንኛውንም ምርመራ አልፈን የዓባይን በረኃ አሐዱ ብለን ተያያዝነው፡፡
ስንቀድም ስንቀደም
ስንከተል ስናስከትል ቆይተን ቁርስ ለመብላት እንጦጦ ጫካ ላይ ሰፈርን፡፡ ኢየሱስ ክርስቶስ በ5 እንጀራ እና በ2 ዓሣ 5ሺህ ሕዝብ
ሲመግብ ያስቀመጣቸው ለምለም ሣር ካለበት ቦታ ነበር፡፡ እኛም ልክ ያንን መስሎ እስኪታየን ድረስ ኹሉም ተጓዦች ቁርሳቸውን ቀመሱ፡፡
ውኃ ታደሉ፡፡ ከምሳ በኋላ አሁንም ጉዟችንን ቀጠልን፡፡ በዚህ ምክንያት የደጋፊዎች መኪና ደጀን ላይ ከተያዙት ሕገወጥ ሚኒባሶች
በስተቀር ሌሎች ቀድመውናል፡፡
እንጦጦ ኬላ
ላይ ጥብቅ ቁጥጥር ይደረግ ስለነበር በመኪና ከመሄድ ይልቅ በእግር መጓዝ የተሻለ ፍጥነት ነበረው፡፡ አንድ ነገር ትዝ ብሎኛል ምን
መሰላችሁ አንድ ሰው ዓባይ በረሃ ላይ ኮንቴነር የጫነ መኪናን ወደ ደጀን ውሰደኝ ብሎ ይለምነዋል፡፡ ከዚያ ሹፌሩም ሰውየው ስላሳዘነው
ይጭነዋል፡፡ ከዚያ መጓዝ ይጀምራል፡፡ ደጀን እገባበታለሁ ብሎ ያሰበው ሰዓት እና የመኪናው ፍጥነት አልመጣጠንለት ይላል፡፡ ከዚያ
ሰውየው ሹፌሩን ጋሸ አመሰግናለሁ በጣም ስለምቸኩል አውርደኝና በእግሬ ልሂድ አለው ይባላል፡፡ እንጦጦ ላይ የገጠመን ነገር ልክ
እንደዚያ ነው የኾነብን፡፡
የደጋፊዎች
አንድ ሚኒባስና አይሱዙ ቅጥቅጥ ቦታ ይዘው ቆመዋል፡፡ የእኛ አውቶቡሶችም እንዲሁ ማለፍ አትችሉም ተብለው ተሰልፈዋል፡፡ አዊዎችም
በአንድ አገር አቋራጭ አውቶቡስ አለፍ ብለው ቆመዋል፡፡ ፖሊሶች በመገናኛቸው በፍጥነት በፍጥነት ይነጋገራሉ፡፡ ከዚያ ተወካዮች ከየመኪኖች
ውረዱ እንነጋገር ተባለ፡፡ እኛ እስከዛሬ ድረስ ተመላልሰናል ደብዳቤ ካላጻፋችሁ አትገቡም ተብለን አናውቅም አሉ ተወካዮቻችን፡፡
ፖሊስም አሁን ያለው የአዲስ አበባ የጸጥታ ጉዳይ ከባድ ስለኾነ ችግር ልትፈጥሩ ትችላላችሁና የመጣችሁበት ቦታ ደብዳቤ መጻፍ ነበረበት
አለ፡፡ መፍትሔው ምንድን ነው ሲባል መኪናችሁን አዙራችሁ ወደ መጣችሁበት ተመለሱ የሚል ኾነ፡፡ በዚህ ውሳኔ አባ ማርቆስ ደጋፊዎች
የተሰማቸው ከልክ ያለፈ ደስታ የሳቅ ሲቃ ኾናቸው፡፡ ልባቸው ሐሴትን ተመላች፡፡ ምክንያቱም በዚያ ሰዓት ከደጋፊዎቻቸው መካከል አንድ
ሚኒባስና አንድ አይሱዙ ቅጥቅጥ ብቻ ነበሩና፡፡ ሌሎች ደጀን ላይ በነበረው ኹኔታ ገና ዓባይ በረሃ ውስጥ ነበሩ፡፡ የእነርሱ መመለስ
ሳይኾን የእኛ አውቶቡሶች መመለሳቸውና ገንዘባችን በከንቱ መባከኑ ነበር ያስደሰታቸው፡፡ እነርሱ በአንድ ብጣሽ ወረቀት 50 ሺህ
ብር አውጥተው ነውና የሚጓዙት ቢመለሱም የሚከስረው የወረዳ ቤተክህነቱ ገንዘብ እንጅ የእነርሱ ስላልነበር ደስታቸው እጅግ ትልቅ
ነበር፡፡
አንድ ከእኛ
ጋር የነበረች እና ወርዳ ከፖሊሱ ላይ ጮኸችበት፡፡ ይች እናት በአባ ማርቆስ ዘንድ እብድ በእግዚአብሔር ዘንድ ግን ውድ ናት፡፡
ለሃይማኖቷ አእምሮዋን ትስታለች፡፡ ጣቷን ወደ ላይ አቅንታ እግዚአብሔር ኾይ ፍረድ ብላ አለቀሰች፡፡ ፖሊሱ ልቡ ራራ በጣም በርኅራኄ
ዓይን ተመለከታት፡፡ እኛ እኮ ስለሃይማኖታችን ነው እንዲህ የምንኾነው ለኦርቶዶክስ ተዋህዶ ግን መቼ ነው ነጻነት የሚሰጣት ብላ
ማተቧን አሳየችው፡፡ እንባዋን ስታፈስ ፖሊሱ ትኩረቱ እርሷ ላይ ኾነ፡፡ ከዚያም አማራጭ ተፈለገ፡፡ ክልሉንም ዞኑንም ቢጠይቁ እነርሱ
ሰላምን ለማውረድ የመጡ ናቸው፡፡ ይለፉ ተባለ በዚህ ተፈቀደልን፡፡ ከዚያም ጉዟችንን ከሰዓታት መንገላታት በኋላ ጀመርነው፡፡
ፖሊሶቹ ያሰቡት
ደጋፊዎችና ተቃዋሚዎች አንድ መድረክ ላይ ሲገናኙ ጠብ ይፈጥራሉ የሚል ነው፡፡ እኛ ደግሞ ለሰላም ነው እንጅ ለጠብ ከጎጃም ድረስ
መጥተን አዲስ አበባ እንዴት እንጣላለን የሚል ነው፡፡ ሰው ለመጣላት አዲስ አበባን አይመርጥም፡፡ ጎረቤታሞች ኾነን በሰላም እየኖርን
ያለን ሰዎች ዕለት ዕለት የምንገናኝ ሰዎች እንዴት አዲስ አበባን ለጥል እንመርጣታለን፡፡ ለመጣላት ለመጣላትማ ማርቆስ ምን አለን፡፡
ለጥል ለጥላቻማ ከኾነ ይህን ያህል ብር ከምናወጣ ለአንድ ወንበዴ ሽፍታ መወዳጀት ይበቃ አልነበረምን?
አሁንም ሄድን
ተጓዝን ከተማ ውስጥ ገባን፡፡ ኬላ ላይ አስቁመውን የነበሩ ፖሊሶች አራዳ ክፍለ ከተማ ስንደርስ ደግሞ አስቆሙን፡፡ ፍተሻ ሳናደርግ
ስላሳለፍናችሁ ልንፈትሻችሁ ነው አሉ ፈትሹን አልን፡፡ እነርሱም እርስ በርሳችሁ ተፈታተሹ አሉ፡፡ እርስ በእርሳችን ተፈታተሽን፡፡
ጨረሳችሁ? አለን፡፡ አዎ ጨረስን አልነው፡፡ ምን አገኛችሁ? አለን፡፡ ምንም አላገኘንም አልነው፡፡ መስቀልም አላገኛችሁም? መስቀል
ኃይላችን ነው አለና በሰላም ግቡ ብሎ ወጣ፡፡ እኛም ወደ መንበረ ፓትርያርክ ቅድስተ ቅዱሳን ማርያም ገዳም አመራን፡፡ ከመኪናችን
ወርደን ወደ ቤተክርስቲያን ስንገባ የአርሲ ሀገረ ስብከት፣ የአዊ ሀገረ ስብከት የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት በተለይ የሰአሊተ ምሕረት
የተዋሕዶ ልጆች ባነራቸውን ይዘው አገኘናቸው፡፡ እኛ በተለያዩ ቦታዎች ላይ በነበረው ፈተና ተቀድመናል፡፡ የአባ ማርቆስ ደጋፊዎችም
ቦታቸውን ይዘው ቆመዋል፡፡ እኛም ገባንና ቦታችንን ይዘን ቆምን፡፡ እነርሱ ለጥፋት እኛ ለቤተክርስቲያን ሰላም ስንል በአንድ ቦታ
ከተምን፡፡ ብፁዕ አቡነ ማርቆስ ከምሥራቅ ጎጃም ይነሡልን የምትለዋ ወረቀት ከአባ ማርቆስ ደጋፊዎች በስተቀር ኹሉም ከፍ አድርጎ
አነሣት፡፡ አዊዎችም፣ አርሲዎችም፣ ሰአሊተ ምሕረቶችም እኛም ከፍ አድርገን አነሣናት፡፡ ሞንታርቮ ይዘን ስለነበር፡፡ በሞንታርቮ
አባ ማርቆስ ይነሡልን፣ ቅዱስ ሲኖዶስ የምሥራቅ ጎጃም ሀገረ ስብከትን ችግር ይፍታልን፤ ቅብዓት ይወገድልን ወዘተ የሚል ድምጽ በቅብብል
ተዜመ፡፡ ቅብዓቶች ደግሞ በተራቸው ማኅበረ ቅዱሳን ይወገዝልን፣ በአባ ማርቆስ ስብከት የሚደነግጠው ሰይጣን ብቻ ነው ወዘተ እያሉ
መጮኽ ጀመሩ፡፡ ቅባቶች በብዛት ከአዲስ አበባ የመጡ እግር መንገደኞች ናቸው፡፡ ከዚህ ከጎንቻና ከደብረ ማርቆስ አካባቢ የመጡት
ደግሞ አበል ስላላቸው አበሉን ፈልገው የሄዱ ናቸው፡፡ ሻሽ አስጠምጥመው ካህን አስመስለው ከኋላቸው አስቁመዋል፡፡ ካህን ያልኾኑ
ካህናትን ሰብስበዋል፡፡ እንዲያውም ትምህርታቸውን እውቀታቸውን ማንነታቸውን የሚያውቁ መጋቤ አእላፍ ጥበቡ የእኛ ስህተት አንድ ጣቃ
ሻሽ ገዝተን ይህን ኹሉ ሕዝብ ሻሽ አለማስጠምጠማችን ነው፡፡ እነርሱ ላይ እኮ ሻሽ የጠመጠሙት ሰዎች ምንም ያልተማሩ ናቸው ብለዋል፡፡
በጥቅም ተሳስረው በዓላማ እና በሃይማኖት አንድ ኾነው ቅብዓትን ለማስፋፋት የሚታትሩ የአበል ተጓዦች በዋናነት ከጎንቻ 6 ሚኒባሶች
እና ከደብረ ማርቆስ 1 አይሱዙ ቅጥቅጥ ነው፡፡ ከዚያ ውጭ ያለው ኹሉ ከመንገድ ተለቅሞ የገባ ነው፡፡
በዚህም መሠረት፡-
ከደብረ ማርቆስ
አካባቢ
1ኛ. ለዓለም…
የደ/ማ ወ/ቤ/ክ ሥራ አስኪጅ፡፡ ይህ ሰው በአይሱዙ ቅጥቅጥ ከየመንገዱ ለቅሞ ያስገባቸውን ሰዎች ሙሉ ወጭ ከወረዳ ቤተክህነቱ ወጭ
አድርጎ የከፈለ ነው፡፡ የተከፈለው ገንዘብ መጠን በትክክል ባይታወቅም ከ20 እስከ 50 ሽህ ብር ባለው መካከል ሊኾን እንደሚችል
ጉዳዩን የያዙት የሀገረ ስብከቱ ኦዲተር አረጋግጠውልናል፡፡
2ኛ. ተስፋ
(ንዑስ)… ይህ ሰው ጎንቻ እያለ የማኅበረ ቅዱሳን ሰብሳቢ የነበረ እና ፎቶ በማንሣት ይተዳደር የነበረ ነው፡፡ ቅብዓትን እቃወማለሁ
የሚል ነገር ግን ቅብዓትን ደግፎ አዲስ አበባ ድረስ የሄደ ነው፡፡
3ኛ. መምህር
ጳውሎስ…ከወደ ረቡዕ ገበያ አምጥተው የሾሙት ነው፡፡ ሰንበት ትምህርት ቤትን ለመበተን በጣም የሚሠራ ነው፡፡
4ኛ. መምህር
ዓምደ ወርቅ--- አሁን የሚገኘው ቁይ ሲሆን ትምህርቱን የተማረው ግን ዲማ ነው፡፡ የዲማ አረም ማለት ይኸው ነው፡፡ ከመንገድ ተጠብቆ
አብሮ ተጭኖ የሄደ ሰው ነው፡፡
ከብቸና አካባቢ
ደግፈው የሄዱ ደግሞ
1ኛ. መልአከ
ምህረት ድረስ አሰፋ… የወረዳ ቤተክህነቱ ሥራ አስኪያጅ
2ኛ. ሊቀ
ጠበብት አብርሃም ካሰ
3ኛ. ቄስ
ደምሴ ይድነቃቸው
4ኛ. ቄስ
ውበቴ ወንድሜነህ
6ኛ. መ/ር
ናሁ ሠናይ ውበት
7ኛ. ቄስ
ይዘንጋው ደጀን
8ኛ. ቄስ
ላመስግን ጌቴ
9ኛ. ቄስ
ደባስ ተረፈ
10ኛ. መ/ጌታ
አመናረ ዋለ
11ኛ. ላእከማርያም
መኩሪያው ናቸው፡፡
እነዚህ ሰዎች
መልአከ ብርሃን አድማሱ ጀንበሬ አለቃ አያሌው ታምሩ መምህር ዘሚካኤል ይኹኔ በኖሩበት ቦታ የሚኖሩ ዲማን መጫወቻቸው ያደረጉ ሰዎች
ናቸው፡፡ በተለይ ላእከ ማርያም በሕይወቴ የማፍርበት ሰው እርሱ ነው፡፡ መምህር ዘሚካኤል ይኹኔ ያስተማሩት በእርሳቸው ወንበር ላይም
እንዲቀመጥ ተመድቦ የነበረ እርሱ ግን የመምህሩን ሚስት የደፈረ ነውረኛ ነው፡፡ ዲማ ላይ ተመድቦ ዲማን እንደ ዓሣ መቁሎ ማመስ
የሚፈልግ ነው፡፡ አባ ማርቆስ ደብዳቤ ጽፈው የመደቡት ቢኾንም ከፍተኛ ችግር በመፈጠሩ እንዲነሣ የተደረገ ነው፡፡ ከእርሱ ጋር የተማሩት
እን መጋቤ ብሉይ አእምሮ ዘውዴ፣ እነ ሊቀ ሊቃውንት ስምዐ ኮነ መልአክ የት እንዳሉ ቢረዳ በተሻለው ነበር፡፡
ጎንቻዎች ከየአጥቢያው
ጥቅመኞች እና ሃይማኖታቸው ቅብዓት እንደኾነ የተረጋገጠላቸው ሰዎች ናቸው ሌሎች ደጋፊዎች፡፡ ዲማ የተማሩ ሰዎች ወልድ ፍጡር ከሚሉ
ሰዎች ጋር ኅብረት መፍጠራቸው በእውነቱ አርዮሳዊነታቸውን አጉልቶ ከሚያሳይባቸው በቀር ሌላ ምን ሊኾን ይችላል?
የኾነው ኾኖ
እነርሱም እኛም ተሰልፈናል፡፡ እኛ ይነሡልን እነርሱ አይነሡብን፣ እኛ ተዋሕዶ ሃይማኖታችን ትጽናለን እነርሱ ቅብዓት ይጽናልን፤
እኛ እውነትን እነርሱ ሐሰትን ይዘን በየምቅዋማችን ቆመናል፡፡ አጠገባቸው ሆነን አባ ማርቆስ ይነሡልን የምትለዋን ወረቀት እያሳየን
ስናቃጥላቸው እንደነበር ፊታቸው ላይ የሚነበበው ነገር ያረጋግጥልናል፡፡ አጠገባቸው ቆሜ ሳለሁ በአባ ማርቆስ ስብከት የሚደነግጠው
ሰይጣን ብቻ ነው የሚለውን ባነር አነበብኩና ሰኔ ጎልጎታን ልብ ወለድ ነው የሚሉ ሰው በእውነት የሚያስደነግጡት በየትኛው ወንጌላቸው
ነው? አልኩ፡፡ አንዱ ያልሰማ በእውነት እንደዚህ ብለዋል አለ፡፡ አዎ አልኩት፡፡ የተቀረጸ አለ? አለኝ አዎ ራሳችን የቀረጽነው
ቪዲዮ አለ አልኩት፡፡ በጣም ያሳዝናል ብሎ የሀዘን ፊት አሳየኝ፡፡ አንዱ ደጋፊያቸው ጠጋ ብሎ ዝም ብሎ ነው ፌስቡክ ላይ ያለውን
አይቶ ነው እንጅ አለ፡፡ እርሱን ተወው አልኩት፡፡
አንዱ ከሉማሜ
አካባቢ የሄደ ጥቁር ልጅ ሱፍ የለበሰ ነው፡፡ ማኅበረ ቅዱሳንማ ወወገዝ
አለበት አለ፡፡ ማኅበረ ቅዱሳን ወልደ አብ መሰለህ እንዴ የሚወገዘው አልኩት፡፡ ጎጃምን ዳግም እያጠመቀ መወገዝ አለበት አለኝ፡፡
ጎጃምን ማን ዳግም ተጠመቅ አለ ቅብዓትን እንጂ አልኩት፡፡ እርሱን ተወው ቅብዓት ተዋሕዶ ብሎ ማንሣት አይገባም ቅብዓት የሚባል
ነገር አናውቅም አለ፡፡ አንተ ራስህ ቅብዓት ኾነህ እኮ ነው ደግፈህ የመጣህ አልኩት፡፡ ቅብዓት የሚባል ነገር የለም አለ፡፡ ታዲያ
ወልደ አብ የተባለውን መጽሐፍ ማን ጻፈው እኛ የጻፍነው ይመስልሃልን? አልኩት፡፡ እንግዲያውስ ግባና ቀድስ አለኝ፡፡ ታዲያ እንዴት
የማልቀድስ እኔም እኮ ዲያቆን ነኝ መቀደስን ማን ይከለክለኛል አልኩት፡፡ ኤዲያ ዝም ብላችሁ ነው አለኝ፡፡ እንፈተን እና ቢያንስ
እንዳንተ ካልመለስኩ ልወቀስ አልኩት፡፡ ዝም አለ፡፡ እኔም ትቼው አባ ማርቆስ ይነሡልን የምትለዋን ወረቀቴን ከፍ አደረግኋት፡፡
ከ50 የማይበልጡ
ደጋፊዎች ቢጮኹ ቢጮኹ አልሰማ ስላሉ ባነራቸውን ከፍ አድርገው ለዝናብ መከላከያ ብለው በያዙት ጥላ አንጠለጠሉት፡፡ ነፋስ አላዘረጋ
አላሲዝ አላቸው፡፡ ከዚያ ከዛፍ ላይ አሰሩት፡፡
ሊቃነ ጳጳሳት
ወደ ቤተክርቲያን እየገቡ ነው፡፡ የምሥራቅ ጎጃም ካህናትና ምእመናን በመዝሙር ወረቀታቸውን ከፍ እያደረጉ ፈጣሪን መለመን ጀመሩ፡፡
አባቶች ገብተው ሲጨርሱ ጸሎቱ ተጀመረ፡፡ ቅዱስ ፓትርያርኩ በሚመሩት በዚህ ጸሎት ላይ የምሥራቅ ጎጃም ካህናት ተሰጥዎውን በመቀበል
ድምጻቸውን ከፍ አድርገው ፈጣሪን ተማጸኑ፡፡ ከአባ ማርቆስ ደጋፊዎች በኩል አንድም ተሰጥዎ የሚቀበል ሰው አልሰማሁም፡፡ ምናልባት
ምን ይባል እንደነበር ስላልሰሙት ካልኾነ በቀር ሻሽ የጠመጠሙ ብዙ ሰዎችን ይዘው ነበር፡፡
ጸሎቱ አለቀ፡፡
በእንባቸው የሚታወቁት አቡነ ቀውስጦስ ትምህርት እንዲሰጡ ተጋበዙ፡፡ አቡነ ቅስጦስ በእንባ የኹለቱን ቅዱስ ሲኖዶስ አንድ መኾን
ተናገሩ፡፡ ድንቅ ታሪክ በመሠራቱም ፈጣሪን አመሰገኑ፡፡ ጊዜው አልኾን ብሎ ስለነበር ነው እንጅ ጥጃ ከእናቱ ሰይፍ ከፎቱ መገናኘቱ
አይቀርም፡፡ ለዚህ ነው ከ27 ዓመታት በኋላ በአንድነት በእናታችን ቤት የተገናኘን አሉ፡፡ የማኅበረ ቅዱሳን ልጆቻችን ሲያለቅሱ
ሲያዝኑ እንባቸውን ሲያፈሱ ኖረዋል፡፡ አሁን ግን ከቅዱስ ፓትርያኩ ጋር ተስማምተው ስለአንዲት ቅድስት ቤተክርስቲያን ሊሠሩ አንድ
ኾነዋል አሉ፡፡ በዚህ ጊዜ በሙሉ አጨበጨበ፡፡ ለማጨብጨብ እጃቸው የታሠረው ግን የአባ ማርቆስ ደጋፊዎች ብቻ ነበሩ፡፡ በደጋፊዎች
በኩል ከነበሩት ጥቂት ወንድሞችና አባቶች በቀር ያጨበጨበ አልነበረም፡፡ እነዚህም ያጨበጨቡ ምናልባትም ሌላው ሲያጨበጭብ ስለሰሙ
ሊኾን ይችላል፡፡
አቡነ ቀውስጦስ
እንባቸውን እያፈሰሱ ያስተማሩትን ትምህርት ጨረሱ፡፡ አቡነ ማትያስም ቃለ ምእዳን ሰጥተው ከቤተክርቲያኑ ወደ መድረክ መጡ፡፡ አቡነ
ዲዎስቆሮስ የጠቅላይ ቤተክህነት ሥራ አስኪያጅ፣ አቡነ ሳዊሮስ የቅዱስ ሲኖዶስ ፀሐፊ እና ሌሎች ሊቃነ ጳጰሳት አሉ፡፡ የአዊ ሀገረ
ስብከት ተወካዮች ጥያቄያቸውን በንባብ አሰሙ፡፡ አቡነ ዲዎስቆሮስ ይበቃናል፡፡ የጻፋችሁትን ለቅዱስ ሲኖዶስ ፀሐፊ ስጡ እኛ እንወያይበታለን
አሉ፡፡ አቤቱታ አቅራቢዎች ግን ኹሉም ይነበብ አለ፡፡ ኾኖም ግን አቡነ ዲዎስቆሮስ ከፈለጋችሁ የተወሰኑ ተወካዮችን ስብሰባ ስንጀምር
እንዲያስረዱ መወከል ትችላላችሁ፡፡ ጥያቄያችሁን እንመለከተዋለን አሉ፡፡ በዚህ ተስማምተን እሺ ብለን የተጻፈውን ወረቀት አስገባን፡፡
ይህ ኹሉ ሲኾን አቡነ ማርቆስን ማዬት አልቻልኩም ነበር፡፡ ብዙ ፈልጌ አገኘኋቸው፡፡ ከመድረኩ ወርደው ከሊቃነ ጳጳሳት ተለይተው
ለብቻቸው ከታች ቆመዋል፡፡ በቆባቸው ላይ ጥቁሩን ፎጣቸውን ከላይ ደርበው ተሸፋፍነዋል፡፡ ይህ አብውነቱ መሸማቀቅ ካልኾነ በቀር
ምን ሊባል ይችላል? ዐሥራ ኹለት ጊዜ ሙሉ ተሸማቀው ለእርሳቸውስ ጥሩ ይኾናል ወይ?
የዘንድሮው
ጉዟችን ልዩ የሚያደርገው የመጀመሪያው ደጋፊዎችም አብረውን የሄዱ መኾኑ ነው፡፡ ኹለተኛው ደግሞ የመጨረሻችን ይኾናል ብለን ተስፋ
የምናደርገው መኾኑ ነው፡፡ ሌላኛው ደግሞ አቡነ ማትያስም ከፖለቲካው እሥራት የተፈቱ መኾናቸው ነው፡፡ በእነዚህ ጉዳዮች ልዩ ያደርገዋል፡፡
ከዚህ በኋላ ሊቃነ ጳጳሳት ወደመኖሪያ ቤታቸው አቀኑ፡፡ እኛም በጭብጨባና በእልልታ ሸነናቸው፡፡
የሰንበት ትምህርት
ቤት ወጣቶች በመዝሙር እግዚአብሔርን ማመስገን ጀመሩ፡፡ በዚህ ሰዓት ቅብዓቶች ደግሞ ለብቻቸው ቆመው ማኅበረ ቅዱሳን ይወገዝልን
በማለት መጮኽ ጀመሩ፡፡ አንድ ሽማግሌ አባት ሰሟቸውና በጣም ተናደዱ፡፡ ደንቆሮዎች አቡነ ቀውስጦስ ቅድም ሲያስተምሩ አልሰማችሁም
እንዴ? ማኅበረ ቅዱሳን እኮ ከፓትርያርኩ ጋር ተስማምተዋል፡፡ አትጩኹ አሏቸው፡፡
ከዚህ በኋላ
ወደ ውጭ በሰላም መውጣት ዓላማችን ስለነበር መውጣት ጀመርን፡፡ ደጋፊዎች ግን ከሊቃነ ጳጳሳት መኖሪያ ቤት መግቢያ ላይ ቆመው መጮኽ
ጀመሩ፡፡ በዚያ ሄደው መጮኽ ያስፈለጋቸው በፊት ድምጻቸው ተውጦ የቆየ ስለነበር ነው፡፡ ማኅበረ ቅዱሳን ይወገዝልን ይላሉ አሁንም፡፡
አቡነ ማርቆስ አይነሡብን ይላሉ አሁንም፡፡ ግን ማንም አይሰማቸውም ነበር፡፡ ጠብ ለመፍጠርም የሞከሩ ነበሩ ኾኖም ግን በትእግስት
አልፈነዋል፡፡
እኛም ወጥተን
ወደ መኪኖቻችን አቀናን፡፡ ቀኑን ሙሉ አቤቱታ ለማሰማት ቆመው የዋሉት ሰአሊተ ምሕረቶች ማረፊያ ቦታ አዘጋጅተንላችኋልና ወደዚያ
እንሂድ አሉን፡፡ የቤተክርቲያን አንድነት ማለት ይኸው ነው፡፡ ከማርቆስ የመጡ አውቶቡሶች በሙሉ ጉዟቸውን ወደ ሰአሊተ ምሕረት አደረጉ፡፡
ከብቸና እና ከደጀን የመጡት አውቶቡሶች ደግሞ ጉዟቸውን ወደ ጎጃም አድርገዋል፡፡ የአዊዎች ጉዳይ ግን እንዴት እንደነበር ሳላረጋግጥ
መቅረቴ ያሳዝነኛል፡፡ ደጀኖች ሌሊት 7 ሰዓት ብቸናዎች ደግሞ ሌሊት 9 ሰዓት ወደ ቤታቸው በሰላም ገቡ፡፡ እኛ ደግሞ በተጨናነቀው
የትራፊክ እንቅስቃሴ ታጅበን ወደ ሰአሊተ ምሕረት ገባን፡፡
ሰአሊተ ምሕረት
በምእመናን የምትጠበቅ አስተዳዳሪ የሌላት ቤተክርቲያን ናት፡፡ የሙስና ሰዎች ሲመሯት ስለነበር እስከ ሞት ድረስ ጸንተው ቤተክርስቲያናቸውን
ነጻ ያደረጉ የተዋሕዶ አናብስት ያሉባት ቦታ ናት፡፡ አቡነ ማትያስ ፈቅደው በአባ ኃይለማርም በአሁኑ አቡነ አረጋዊ ቀቢነትና ተቀቢነት
ከፕሮቴስታንቶች ጋር የተቀባቡባትም ቦታ ናት፡፡ በዚህም የተነሣ ምእመናን እጅጉን ተቆጥተው ቤተክርስቲያናቸውን ከሌቦች እና ከወንበዴዎች
መንጋጋ የታደጉ ናቸው፡፡ ዛሬም አብረውን አቤቱታቸውን ሲያሰሙ የዋሉ ናቸው፡፡
ሰአሊተ ምሕረት
ደረስን፡፡ ድንኳን ተጥሏል፡፡ የእግር መታጠቢያ ውኃ እና ሳፋ ተዘጋጅቷል፡፡ ከጎጃም ሄደን እንግዳ መቀበልን ከአዲስ አበባ የተማርንበት
ነው፡፡ እንግዳ ተቀብለን እናውቅ ይኾናል፤ የተራበን አብልተን የተጠማንም አጠጥተን እናውቅ ይኾናል እንደ ሰአሊተ ምሕረቶች ያለ
እንግዳ አቀባበል ግን አላየሁም፡፡ ቤተክርስቲያን ሄደን አቡነ ብለን ተመለስን፡፡
ወንድሞቼ ኑ
እግራችሁን እንጠባችሁ ተባልን፡፡ እንግዳ አይደለን መቼስ እንግዳ ባናጥብም እኛ ግን እንግዶች ነንና እንድንታጠብ ተቀመጥን፡፡ ታጠብን፡፡
አመስግነን ወደ ድንኳናችን ገባን፡፡ በዚያች ድንኳን ውስጥ ኹላችንም ተቀመጥን፡፡ ምግብ መጣ፡፡ የፍስኩም የጾሙም ምግብ በየዓይነቱ
ቀረበልን፡፡ ለሚጾመው ምስር ወጥ ለማይጾመው ደግሞ ቀይ ወጥ ሥጋ ፍርፍር ወዘተ ቀረበ፡፡ ዳቦ ተጨመረ፡፡ በላን፤ ውኃ ቀረበልን
ጠጣን፡፡ ከሚገባው በላይ ተስተናገድን፡፡ ስንጨርስም ስብሐት ተባለ አባቶችም መረቁ፡፡ አስተናጋጆቻችንም ቆመው ምረቃውን ተቀበሉ፡፡
ከዚያ ስለማደሪያችን ገለጻ አደረጉልንና ወደ አዳራሹ አቀናን፡፡ ለአባቶች ለእህቶች ለምእመናን ቦታዎች ተለይተው ተዘጋጅተዋል፡፡
በዚያ ከተንጣለለው አዳራሽ ላይ በቀይ ምንጣፍ ላይ በሰላም አሳድረን ብለን ጎናችንን አሳረፍን፡፡ ስለአጠቃላይ ውሏችን አጭር ውይይት
አድርገን ሌሊት 9 ሰዓት እንደምንነሣ ማሳሰቢያ ተሰጥቶ ተኛን፡፡ ሽንት ቤት አጠቃቀማችን፣ ድንኳን ውስጥ በነበረው መስተንግዶ ጮኸንባችሁ
አስቀይመናችሁ፤ እግር ስታጥቡን ትሕትናን አላሳያችሁ ብለን ከኾነ፣ ማደሪያችን ላይ ጥፋት ሠርተን ከኾነ ይቅርታ እንጠይቃችኋለን፡፡
ኹላችንም ጥሩ ልንኾን አንችልምና ጥፋት ፈጽመን ሊኾን ስለሚችል፡፡
ሌሊት 8፡30
አካባቢ ተነሣን፡፡ ጸሎት የሚያደርሰው ጸሎቱን አደረሰ፡፡ ወደ ቤተክርስቲያን አምርተን አቡነ አልንና ወደ መኪናችን አቀናን፡፡ ሌሊት
9 ሰዓት ኾኗል፡፡ መኪናችን መንቀሳቀስ ጀመረ:: የማይቀረውን ጉዟችንን ተያያዝነው፡፡ ደጀን ስንደርስ እረፍት አደረግን፡፡ ከዚያም
አምበርን ለውይይት መርጠን እዚያ እንድንቆም ተነጋግረን ሄድን፡፡ ነገር ግን ቦታውን አልፎ የቆመ መኪና ስለነበር ደብረ ማርቆስ
ልንገባ ስንል እንነጋገራለን ብለን ወደዚያው አመራን፡፡
ከዚያም ስለነበረን
አጠቃላይ ኹኔታ ተነጋገርን፡፡ ወደፊት ምን ማድረግ ይገባናል? ስለሚለውም ተነጋገርን፡፡ በዚህም ውይይት ጎልቶ የተሰማው የደብረ
ማርቆስ ወረዳ ቤተክህነት ለአንድ አይሱዙ ቅጥቅጥ የኮንትራት ክፍያ ወጭ አድርጎ የከፈለ ስለኾነ ተጣርቶ ክስ እስኪመሠረት ድረስ
ጽ/ቤቱ መታሸግ አለበት የሚለው ነበር፡፡ መረጃ እንዳያሸሹ መታሸግ እንዳለበት ተስማማን፡፡ ስናሽግ ግን የመንግሥት አካላትም ማወቅ
አለባቸውና እነርሱንም እናሳውቅ በሚለው ስምምነት ላይ ደርሰን፡፡ ቃለ ጉባዔ ይዘን ኹሉንም ፊርማ እንዲፈርሙ አድርገን ወደ ደብረ
ማርቆስ አመራን፡፡ ተክለ ሃይማኖት አደባባ አባ ማርቆስ ይነሡልን የሚል ወረቀት የተለጠፈባቸው አውቶቡሶች ከባጃጆች መካከል ከፍ
ብለው ቆሙ፡፡ ሰው ኹሉ ዓይኑን ወደእነዚህ አውቶቡሶች አደረገ፡፡ ተወካዮች የመንግሥት አካላትን ለማሳወቅ ሄዱ፡፡ እኛም ወረዳ ቤተክህነቱ
ወደሚገኝበት ወደ ቅዱስ ማርቆስ ቤተክርስቲያን አቀናን፡፡ ሰዓቱ 8 ሰዓት አካባቢ ኾኖ ነበር፡፡ ተወካዮች ለመንግሥት አካላት አሳውቀው
እስኪመጡ ድረስ በትዕግሥት ፀሐይ ላይ ቆመን ጠበቅን፡፡ በመጨረሻም ተወካዮቻችን አሳውቀው መጡ፡፡ ከዚያም ኹሉም ጉዟችንን ወደ ወረዳ
ቤተክህነቱ አደረግን፡፡ የደብረ ማርቆስ ወረዳ ቤተክህነት ከምሥራቅ ጎጃም ሀገረ ስብከት ጽ/ቤት ግቢ ውስጥ የሚገኝ ነው፡፡ ወደዚያ
ስንገባ ሥራ አስኪጁም ሌሎችም ሠራተኞች የሉም፡፡ ሥራ አስኪያጁ 7፡33 አካባቢ ከቢሮ ወጥተው ሲመለሱ ዓይተናል፡፡ ከቢሮ የወጡት
ሊታሸግ እንደኾነ የነገራቸው አብሮን የነበረ ሰው ስላለ ነው፡፡ ወደ ቢሮው ስናቀና በሙሉ ዝግ ነው፡፡ የሀገረ ስብከቱ አስተዳድር
ጉባዔ አባላት የተወሰኑት 4 የሚኾኑት ቢሯቸውን ከፍተው በመሥራት ላይ ነበሩ፡፡ አራቱም እንዲወጡና እንዲያናግሩን አደረግን፡፡ እኛ
ሥራ አስኪያጁን ነው የምንጠብቅ፡፡ ኦዲተሩም ተናገሩ፡፡ ወረዳ ቤተክህነቱ በትክክል ገንዘብ አውጥቷል፡፡ ከዚህ ወጭ በተደረገ ገንዘብ
ከብቸና ከቁይ ከሉማሜ ከደብረ ማርቆስ አካባቢ ያሉ ሰዎችን ሰብስቦ
ሄዷል፡፡ እናንተ ይነሡልን ብላችሁ ሄዳችሁ እርሱ ደግሞ ከእናንተ በተሰበሰበ ገንዘብ ጠላት ኾኖ ሄዷል አሉ፡፡ ስለዚህ ማሸግ ትችላላችሁ፡፡
የገንዘብ እንቅስቃሴም እንዳይደረግ ሥራ አስኪጁ ከመጡልን ደብዳቤ ጽፈን የሂሳብ ደብተሩን እናስቆመዋለን ብለዋል፡፡ የወጣው ገንዘብ
መጠን ግን በወሬ ደረጃ 20ም 30ም 50ም ሺህ ነው ይላሉ እኛ እያረጋገጥን ነው ብለውናል፡፡ እኛም ጽ/ቤቱን አሽገን ለሀገረ ስብከቱ
ዘበኞች እና ለአስተዳድር ጉባዔ አባላት አስጠብቀን ወጣን፡፡ ችግር የሚፈጥሩ ከኾነ አሳውቁን ብለን ወደየቤታችን አመራን፡፡
አባ ማርቆስ
ይነሡልን የምንለው፡-
. ከምሥራቅ
ጎጃም ሐገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስነት
. ከስብከተ
ወንጌል እና ሐዋርያዊ መምሪያ ኃላፊነት
. ከቴሌቪዥን
የቦርድ ሰብሳቢነት ጭምር ነው፡፡
ይህን የምንለውም
እምነታቸው ትምህርታቸው ችግር ስላለበት ነው፡፡ ከእነዚህ የስህተት ትምህርቶቻቸው እና ከሠሩት በደል መካከል የሚከተሉት ይገኙበታል፡፡
. ሰኔ ጎልጎታን
ልብ ወለድ ነው ያሉ፡፡
. ተዝካርን
ምዋርት ነው ያሉ፡፡
. በዘመነ
ዮሐንስ ልደት ታኅሣሥ 28 መከበር የለበትም ያሉ፡፡
. ተዋሕዶ፣
ቅባት፣ ካራ፣ ጸጋ የሚባል ነገር የለም ያሉ፡፡
. ሐገረ ስብከቱን
ለቅብዓትና ለተሐድሶ አሳልፈው የሰጡ፡፡
. ደመወዛቸውን
ከ10ሺህ ወደ 17 ሺህ በር ያሳደጉ፡፡
. ድጓ፣ ቅኔ
ተምረህ ሰው አትኾንም ያሉ፡፡
. የጽጌ ጾምን
ያመጣብን ሰንበት ትምህርት ቤት ነው ያሉ፡፡
. የከሳ የሚወፍረው
በጽጌ ጾም ነው ሥጋና ቅቤ ስለሚበላ ያሉ፡፡
የአባ ማርቆስ
ደጋፊዎች እነዚህን ትምህርቶች የሚቀበሉ ናቸው፡፡ ለዚህም ነው የጥፋት ተባባሪዎች ናችሁና አንፈልጋችሁም ተብለው በመባረር ላይ የሚገኙት፡፡
ከዚህ በኋላ ለዓለም፣ ተስፋ(ንዑስ)፤ ጳውሎስ እና ሌሎችም ተባባሪዎች አባ ማርቆስ በሰጧቸው ሥራ አይቀጥሉም፡፡ የሚከፈላቸው የሕዝብ
እንጅ የአባ ማርቆስ ገንዘብ አይደለምና ደመወዝ ለጠላት አንከፍልም ይህ የምእመናን ውሳኔ ነው፡፡
እነዚህ ደጋፊዎች
ከማርቆስ የተነሡት ሌሊት ሲጓዙ አድረው ማርቆስ የገቡትም ሌሊት ነው፡፡ የተወሰኑት ከጎንቻ የሄዱት የቅርብ ዘመዶቻቸው ግን ጠቅላይ
ቤተክህነት በሰጣቸው ቤታቸው ላይ አሳድረዋቸዋል፡፡ ማታ አካባቢ ያገኟቸው አንድ ካህን አብደዋል እርሳቸው በጣም ተናደዋል አሉኝ፡፡
በተዋሕዶ ሃይማኖት ላይ ጦርን ለመስበቅ ሲመክሩ እንዳደሩ ይታወቃል፡፡ ቅዱስ ሲኖዶስ እንዲያውቅልን የምንፈልገው ነገር እነዚህ አባ
ማርቆስ ደጋፊዎች በብዛት ቅብዐቶች መኾናቸውን ነው፡፡ ወልደ አብ አይወገዝ ብለው ጮኸዋል ተብሏል፡፡ ይህ እውነት ከኾነ ቅዱስ ሲኖዶስ
አይቶ ያወገዘውን መጽሐፍ አይወገዝ ብሎ ቅዱስ ሲኖዶስን የሚሞግት የእርሳቸው ደጋፊ ከኾነ እርሳቸው ማን እንደኾኑ ለመረዳት ቀላል
ነው፡፡ ‹‹ማኅበረ መሢሕ›› በሚል የመሠረቱት ማኅበር በጀቱ ማን ነው እርሳቸው አይደሉምን? ምሥራቅ ጎጃም ላይ ያለው ሁኔታ ጥሩ
አይደለም፡፡ ምእመናን ደም ከመፋሰሳቸው በፊት ካህናት ከመተራረዳቸው በፊት ቅዱስ ሲኖዶስ መላ ሊያበጅለት ይገባል፡፡ ቅብዓቶች በግልጽ
እንለይ እያሉ ያሉበት ጊዜ ነው፡፡ ጉዳዩን ሸፋፍነን ደባብቀን ማለፍ አይገባንም፡፡ ነገ እኮ ይህ የእኔ ነው ይህ የእኔ ነው ብለው
ቤተክርስቲያናችንንም ሊከፍሏት ነው፡፡ በወልደ አብ መናፍቅ አፈረ፣ እናምናለን ምስጢረ ቅብዓትን ወዘተ የሚሉ ዘማርያንን እኮ ናቸው
ትናንትና አባ ማርቆስ አይነሡብን ብለው የቆሙት፡፡ ታዲያ ቅዱስ ሲኖዶስ እርምጃ ለመውሰድ እርሳቸውንም እምነታቸውን ጠይቆ ለምን
አይለያቸውም? ራሳችን ገንዘባችንን እየከፈልን እስከ መቼ ነው ምንፍቅና ሲያሳትሙ ዝም የምንላቸው፡፡ አባ ማርቆስ ደጋፊዎቻቸውን
በቤታቸው አሳረው ጠዋት ላይ ሸኝተዋቸዋል፡፡ ደጀን ሲደርሱ ወደ ፖሊስ ጣቢያ ቀርበው የከፈልነው ገንዘብ ይመለስልን ተገቢ አይደለም
ብለው ከቢሮ ቢሮ ተንከራትተዋል፡፡ ፖሊሶች ግን ምንም እንደማያገኙ ነግረዋቸዋል፡፡ ይህንንም አምነውበት ተቀብለው ወደ ጎንቻ አምርተዋል፡፡
ጎንቻዎች መኪና ውስጥ ተከፋፍለው ሊደባደቡም እንደነበር ሰምተናል፡፡ ከዚህ በፊት መኪናቸው እየተጋጨ መኪናቸው እየተገለበጠ ተአምር
ሲያዩ ኖረዋል፡፡ ዘንድሮ ግን መጨረሻቸው ስለኾነ ከጠብ እና ከቅጣት ውጭ ሌላ ነገር አልገጠማቸውም፡፡ የጠባቸው ምክንያት መረጃ
የምትሰጡ ሰዎች አላችሁ በሚል እንደኾነ ለማወቅ ችለናል፡፡ መረጃችን አቡነ ማርቆስ ናቸው፡፡ እርሳቸው ጋር ደውለን ኹሉን ነገር
ማረጋገጥ እንችላለን፡፡
‹‹ወነሰተ
ምክሮ ለጸላዒ›› ማለት ይኸው ነው፡፡ ጎንቻዎች ለቅጣት 30 ሺህ ብር እና ለመኪኖች የትራንስፖርት ክፍያ የፈጸሙት ከአጥቢያዎች
እንደኾነ ሰምተናል፡፡ ይህንን አረጋግጣችሁ መረጃውን ላኩልን ያለምንም ድርድር ውሳኔ እንዲሰጥ እናስደርጋለን፡፡ ገንዘባችንን ለጠላት
መስጠት ስለማንሻ፡፡
==========
ጥቅምት
13/2011 ዓ.ም
ደብረ ማርቆስ፣
ኢትዮጵያ
No comments:
Post a Comment