===========================
[ፓትርያርኩ “ከማኅበረ ቅዱሳን ጋር አልታረቅሁም፤ እስከምሞት እረግመዋለሁ”
አሉ:: ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ አቡነ ማትያስ፣ ከማኅበረ ቅዱሳን ጋራ እንዳልታረቁና እስከሞት ድረስ እንደሚረግሙት ለቅዱስ ሲኖዶስ
ምልዓተ ጉባኤ ተናገሩ]
ይህ ዜና አባ ማትያስ ላይ ያለንን የአባትነት ስሜት ክፉኛ የሚጎዳ ነው፡፡
አባ ማትያስ ከበፊት ጀምሮ ቃላቸው ኹለት ነው፡፡ አሜሪካ እያሉ ማኅበረ ቅዱሳንን እግዚአብሔር ያስነሣችሁ ለቤተክርስቲያን እጅግ
የምታስፈልጉ ናችሁ እያሉ ሲያሰግኑ ነበር፡፡ ፓትርያርክ ኾነው አዲስ አበባ ከመጡ በኋላ ግን ነገሮች እየተቀየሩ መጡ፡፡ እርሳቸውም
ማኅበረ ቅዱሳንን እቃወመዋለሁ ቤተክርስቲያናችንን ቅኝ የገዛ ማኅበር ነው ብለው ተናገሩ፡፡
ስለሦስተኛው ፖትርያርክ አቡነ ተክለ ሃይማኖትም እንዲሁ ያለ ኹለት ምላስ
የኾኑበት አጋጣሚ ነበር፡፡ በቪኦኤ ቃለ መጠይቅ ሲደረግላቸው አቡነ ተክለሃይማኖትን ፖለቲከኛ እንደኾኑ፣ አባትነታቸው ትክክል እንዳልኾነ፣
ቤተክርስቲያንን ማስተዳደር እንደማይችሉ ወዘተ ገልጸዋል፡፡ እንዲያውም በጣም ሰድበዋቸዋል፡፡ ከተወሰኑ ዓመታት በኋላ ስለእርሳቸው
ሲጠየቁ ግን የሰጡት ምላሽ በፍጹም እርሳቸውን አልተሳደብኩም፡፡ እንዲያውም እርሳቸው ደግ መናኝ ነበሩ ወዘተ ብለው መለሱ፡፡
ከዚህ ኹሉ የምንረዳቸው አቡነ ማትያስ አእምሯቸው ትክክል እንዳልኾነ ነው፡፡
ምናልባትም ሌት ከቀን ከጎናቸው ኾኖ አቋማቸውን ሳፋ ላይ እንዳለ ውኃ እንዲዋልል የሚያደርጋቸው ኃይል ያለ ይመስለኛል፡፡
ከማኅበረ ቅዱሳን ጋር ታረቁ ተብሎ እርሳቸውም ታርቄያለሁ ብለው አቡነ ቀውስጦስም
ይህንኑ አብሥረውን የቤተክርስቲያን ችግር ተፈታ እያልን ባለንበት ጊዜ በፍጹም አልታረቅሁም ማለት ምን ማለት ነው? የጤና ይመስላችኋል
ግነ? እኔ የጤና አይመስለኝም፡፡ አንድ ፓትርያርክ እንዲህ በኹለት ምላስ ሲዋቀሩ ማየት ይከብዳል፡፡ እስከሞት ድረስ እረግመዋለሁ
ማለታቸው እርቃቸውን ለታይታ ያደረጉ መኾናቸውን የሚጠቁም ነው፡፡
በዚህ ዓይነትማ ከውጩ ሲኖዶስ ጋርም አልታረቅሁም ማለታቸው አይቀርም እኮ፡፡
አሁን የሊቃነ ጳጳሳት ምደባ ሲጀመር እገሌ አይመደብም ከውጭ የመጣ ነውና ማለታቸው አይቀርም፡፡ አባታችን ምነው ታርቀን የለምን?
ሲሏቸው ደግሞ እኔ ዶ.ር ዓቢይ ደስ እንዲለው ብየ እንጅ እስክሞት ድረስ አወግዛቸዋለሁ ማለታቸው አይቀርም፡፡
ምልዓተ ጉባዔው ግን የአባ ማትያስን ጉዳይ አይቶ ከፓትርያርክነት እስከማውረድ
ድረስ መድረስ አይችልም ወይ? እርሳቸው እኮ የማይመከሩ የማይዘከሩ እየኾኑ ነው፡፡ በመንግሥት ተጽእኖ ፓትርያርክ የኾኑ እንደኾነ
ፀሐይ የሞቀው ዓለም ያወቀው ጉዳይ ነው፡፡ ታዲያ ዛሬ ቤተክርስቲያን ነጻ ስትኾን አባ ማትያስን ማረም እንዴት ለምልዓተ ጉባዔው
ከበደ?
ከውስጥ ያለው የዘረኝነት መንፈስ ግን ብዙ ሊቃነ ጳጳሳትን እያስለቀሰ ያለ
ጉዳይ ነው፡፡ የኦሮምያ ጠቅላይ ቤተክህነት፣ የአማራ ጠቅላይ ቤተክህነት፣ የትግራይ ጠቅላይ ቤተክህነት ብለው ለመከፋፈል እየሠሩ
ያሉ ከፋፋዮችም አሉ፡፡ መንፈስ ቅዱስን አማራ፣ ኦሮሞ፣ ትግሬ ብለው ሊከፋፍሉት ይታትራሉ አሉ፡፡ ለማንኛውም እግዚአብሔር አምላክ
የጠላት ምክሩን ያፍርስልን፡፡
ትልቁን የቤተክርስቲያን ሸክም አባ ማርቆስን ካነሡልን በኋላ እያሰብን ያለነው
ማን ይመደብልን ይኾን? የሚለውን ነው፡፡ ቅዱስ ሲኖዶስ በመጀመሪያ የሃይማት ሕጸጽ ያለባቸውን ሊቃነ ጳጳሳት ለይቶ መምከር ማስተማር
ካልተመለሱም አውግዞ መለየት ይኖርበታል፡፡ ለምሳሌ፡- ከውጭ ከመጡት መካከል አባ ወልደ ትንሣኤ የአሁኑ አባ በርናባስ፣ አባ ሀብተ
ማርያም የአሁኑ አባ መልከጼዴቅ ወዘተ እነዚህን ሊቃነ ጳጳሳት በመጀመሪያ መምከር ያስፈልጋል፡፡ ወልድ አማላጅ ነው እያለ የሚሰብክን
ሰው ሊቀ ጳጳስ አድርጎ መመደብ ችግሩን ያብሰዋል፡፡
ከሀገር ውስጥ ደግሞ እነ አባ ማርቆስ፣ እነ አባ ቶማስ ወዘተ መታየት አለባቸው፡፡
ምእመናን ከቅዱስ ሲኖዶስ በላይ እንዲኾኑ መጠበቅ የለባችሁም፡፡ ቅዱስ ሲኖዶስ ልእልናውን ማስከበር አለበት፡፡
====================
ጥቅምት 14/2011 ዓ.ም
ደብረ ማርቆስ፤ ኢትዮጵያ
No comments:
Post a Comment